ካይኔ እንደገባህ ካይንህ ለመግባት ስል
ቀመሬን ስጀምር ገና ሳብሰለስል
ቅርፅና ቀለሜን ባንተ ልክ ቀይሬ
መዋል መመሳሰል እንድውል አብሬህ
ጉዞዬን ጀመርኩኝ ወደልብህ ዛሬ
ዉሎ አኗኗርህን ካጠናው በሗላ
የዘራሁት ፍሬ መስሎኝ የሚበላ
የበረሀ አትክልት ሳጠጣ ሳጠጣ
በለሱ ተንሳፎ አመጣብኝ ጣጣ
በልክህ ባይሰራኝ እግዜር ለኔ አስቦ
ልቤ አልሰማ ብሎ ተጨንቆ ተጠቦ
ባልተሰራለት በር ለመግባት ሲሞክር
እንቢታህ ሲጠና እኔ ዙሩን ሳከር
አንዲት ግድ ሳይሰጥህ እኔው እንደዳከርኩ
ያልሆንኩትን ስሆን የሆንኩትን ከሰርኩ
ሳስበው አፈርኩኝ
ያንተ እንቢ ማለት የኔ ካልሰጠኹኝ
ፍቅሩ ወደ እልህ ሲቀየር ባንድ አፍታ
ተራዬ እንዲደርሰ እኔም ድል ልመታ
ሌላ ፋብሪካ ውስጥ ሌላ ቀለም ሆኜ
አዲስ ቅርፄን ይዤ ወጣሁ ተቀጥቅጬ
ያችኛዋ ፍቅር ይቺ በቀል አምጡ
ተለያዮ ቢባል ካንተ አላመለጡ
እንዲቆጭህ ብዬ ያሴርኩትን ሴራ
ያልሆንኩትን ስሆን አሁንም ኪሳራ
ቀመሬን ስጀምር ገና ሳብሰለስል
ቅርፅና ቀለሜን ባንተ ልክ ቀይሬ
መዋል መመሳሰል እንድውል አብሬህ
ጉዞዬን ጀመርኩኝ ወደልብህ ዛሬ
ዉሎ አኗኗርህን ካጠናው በሗላ
የዘራሁት ፍሬ መስሎኝ የሚበላ
የበረሀ አትክልት ሳጠጣ ሳጠጣ
በለሱ ተንሳፎ አመጣብኝ ጣጣ
በልክህ ባይሰራኝ እግዜር ለኔ አስቦ
ልቤ አልሰማ ብሎ ተጨንቆ ተጠቦ
ባልተሰራለት በር ለመግባት ሲሞክር
እንቢታህ ሲጠና እኔ ዙሩን ሳከር
አንዲት ግድ ሳይሰጥህ እኔው እንደዳከርኩ
ያልሆንኩትን ስሆን የሆንኩትን ከሰርኩ
ሳስበው አፈርኩኝ
ያንተ እንቢ ማለት የኔ ካልሰጠኹኝ
ፍቅሩ ወደ እልህ ሲቀየር ባንድ አፍታ
ተራዬ እንዲደርሰ እኔም ድል ልመታ
ሌላ ፋብሪካ ውስጥ ሌላ ቀለም ሆኜ
አዲስ ቅርፄን ይዤ ወጣሁ ተቀጥቅጬ
ያችኛዋ ፍቅር ይቺ በቀል አምጡ
ተለያዮ ቢባል ካንተ አላመለጡ
እንዲቆጭህ ብዬ ያሴርኩትን ሴራ
ያልሆንኩትን ስሆን አሁንም ኪሳራ