መሬት የወደቀው ቅጠል ንፋሱን ሰደበው
"የጣልኸኝ አንተ ነህ"
ንፋሱም መለሰ
"እኔ ድንገት ሳልፍ ነው እኮ አንተ የወቅኸው።
ግንዱን እየው አልወደቀም
ቅርንጫፍህን እየው አልተሰበረም"
ቅጠሉ
"አንተ ባትገፋኝ ባታወዛውዘኝ አልወድቅም ነበር" አለው
ንፋስ ሳቀ።
" ሁሉም ራሱን ቢያጠነክር ይድን ነበር። ያለፈ ያገደመ የሚጥለህ ራስህን ስለጣልክ ስላቀለልክ ነው።
አየህ
የወደቁ ሁሉ ሁሉ የተገፉ አደሉም! "
ኤልያስ ሽታኹን
"የጣልኸኝ አንተ ነህ"
ንፋሱም መለሰ
"እኔ ድንገት ሳልፍ ነው እኮ አንተ የወቅኸው።
ግንዱን እየው አልወደቀም
ቅርንጫፍህን እየው አልተሰበረም"
ቅጠሉ
"አንተ ባትገፋኝ ባታወዛውዘኝ አልወድቅም ነበር" አለው
ንፋስ ሳቀ።
" ሁሉም ራሱን ቢያጠነክር ይድን ነበር። ያለፈ ያገደመ የሚጥለህ ራስህን ስለጣልክ ስላቀለልክ ነው።
አየህ
የወደቁ ሁሉ ሁሉ የተገፉ አደሉም! "
ኤልያስ ሽታኹን