ማንነትህን የቀየረው ማን ነው ? ብባል ሳላንገራግር ሽፈራው ነው የምለው ...ሽፈራው ማነው ? ብባል
ዘጠነኛ ክፍል ኮከበ ፅብሃ ስማር ትምህርት ቤታችን በር ላይ ሩጬ አስፋልት ስሻገር በመኪና የገጨኝ ሹፌር ነው እላልሁ .....
እስከዘጠነኛ ክፍል ቆሌ አልነበረኝም ብርር ብርር፣ ጥድፍ ጥድፍ፣ ቅልጥፍ ፣ቅልል፣ ቅልቅል ያልኩኝ ነበርኩ ሽፈራው በሚኪናው እስኪያንከባልለኝ ....
ኳስ ከሚጫወቱ ጋር፣ ጆተኒ ከሚጫወቱ ጋ፣ ሩጫ ከሚሮጡ ጋ፣ ከሚታገሉ ጋ ፣ ዋና ከሚለማመዱም ፣ከሚዋኙም ጋ በየቦታው ነበርኩ
በየቦታው ሰላም የማልለው የለም የሁሉም ጓደኛ ነበርኩ የሁሉም ...
ሽፈራው አስፋልት ስሻገር በመኪናው ገጨኝ
እስከዛሬ ሰው በጣም አሞኛል ሲለኝ ፤ተሰቃየው ፤ ከባድ ነበር ፤ ልሞት ነበር እያለ ሲያብራራ ልቤ ወደ ዘጠነኛ ክፍል ኮከበ ፅባህ ትምህርት ቤት መኪናው ሲገጨኝ ተሸክመውኝ ሲሄዱ ሃኪም ጋ ስሄድ ያለውን መንፈስ ነው የማስተውሰው ...
የሁሉም ጓደኛ ስለሆንኩ በመገጨቴ ዜና ሆነ ...ምንሊክ ሆስፒታል የትምህርት ቤታችን ልብስ የለበሱ ልጆች፣የሰፈር ልጆችም ሳምንቱን ሙሉ ሞሉት
የግራ እግሬ ተሰብሮ ነበር ጀሶ ተጠቀለለልኝ ከሆስፒታል ወጣሁ እቤት የተወሰኑ ጓደኞቼ እየመጡ ጠየቁኝ ...
ጓደኞቼ ጠብ ጠብ እያሉ ጠፉ ። የሁሉም ጓደኛ መሆን ለካ የማንም ጓደኛ አለመሆን ነው የሚለው ጥቅስ ገባኝ ...
ለእናት እና አባቴ ብቸኛ ልጅ ነኝ ሰራተኛ የለንም ሁለቱም ስራ ይውላሉ
ጓደኞቼ ትምህርት ቤት ነው የሚውሉት
ቤት ውስጥ ቀን ብቻዬን እውላለሁ ። ብቻዬን ከራሴ ጋ ተፋጠጥን ....
ረጋ አልኩ ....
ረጋ ብሎ የሆነ ቦታ ቁጭ ማለት ..ሳያወሩ መዋል ..ነገሮችን ረጅም ሰዓት ሃሳብ ሳይሰጡ ማየት ለመድኩ
ቀስስ ብዬ ቴክስት ቡኮችን ለመረዳት ማንበብ ጀመርኩ ...አባቴ የሚያነባቸውን መፅሃፍ ማንበብ ጀመርኩ .....
እግሬ ሙሉ ለሙሉ ስላልዳነ ስራመድ ረጋ አልኩ ...ትንሽ ሳውቅ የማወቅ ፍላጎቴ ዳበረ
እራሴን ተለማመድኩት .... ስለሚደብረኝ የምሄድባቸው ስፍራዎች ቀረው ...
የሆነ የተረጋጋ ልጅ ፦
የሆነ ብቻ መሆን የማይፈራ ልጅ ፦
የሆነ ተረጋግቶ ለመረዳት የሚጥር ልጅ ሆንኩ
ከጓደኞቼ አንድ አመት በትምህርት ዘግይቼ ግን ሲገጭ ከነበረው ልጅ በፍፁም የተለየ ልጅ ሆኜ ዘጠኛ ክፍል ደግሜ ጀመርኩ ...
ትምህርት ጎበዝ የሆነ ልጅ ፣ቧንቧ ሲሰራ ኤሌትርኪ ሲሰራ ፣ፊዚክስ ሲብራራ ፣በትኩረት ሳልሰለች የማይ ልጅ ሆንኩ ...
የወደድኩት የህይወት Turning point የጀመረው ሽፈራው በመኪናው ያንከባለለኝ እለት ይመስለኛል ...
እግር ነስቶ ክንፍ የሚሰጥ መንከባለልም አለ ብንል ላንታመን እንችላለን አለመታመናችን እውነትነቱን አይነጥቀንም እንጂ።
© Adhanom Mitiku