የነሃቢ ዌብሳይት ግንባታ ውድድር ምዝገባ ተጠናቀቀ
በአሸዋ ቴክኖሎጂ ሶሉሽን የሚዘጋጀው እና በመቶዎች የሚቆጠሩ ተወዳዳሪዎችን የሚያሳትፈው የነሃቢ ድረ-ገጽ ግንባታ ውድድር ምዝገባ በትናንትናው ዕለት ፍጻሜውን አግኝቷል፡፡ የዚህን ውድድር ምዝገባ መጨረሻ መቃረብ አስመልክቶ ባለፉት ሁለት ቀናት በ አዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ እንዲሁም በአዲስ አበባ 5ኪሎ ካምፓስ ዩኒቨርሲቲዎች የሚገኙ የቴክኖሎጂ ተማሪዎችን ያሳተፈ የምዝገባ ዝግጅት ተደርጓል፡፡
በውድድሩ ላይ የሚሳተፉ ተማሪዎች እና ሌሎች ዴቨሎፐሮች
👉 አሸናፊዎች እስከ መቶ ሺህ ብር ድረስ ይሸለማሉ
👉 ከትምህርት ዓለም ውጭ መሬት ላይ ያለውን የስራ ሁኔታ ይረዳሉ
👉 ያላቸውን ብቃት እና ክህሎት ያወጣሉ
👉 በዘርፉ ላይ ከሚገኙ ባለሙያዎች ጋር የመገናኘት ዕድል ያገኛሉ
👉 የፈጠራ ችሎታቸውን ያሳድጋሉ
ማስታወሻ፦ ለየት ያሉ እና ከ ሰው ሰራሽ ልህቀት(AI) ጋር የተገናኙ ፌቸሮችን የሚያካትቱ ተወዳዳሪዎች የተሸላሚነት ዕድላቸው ከፍተኛ ነው፡፡
ከ ዩኒቨርሲቲዎቹ ጋር የተፈጠረው ትብብር ለወደፊቷ ኢትዮጵያ የቴክኖሎጂ ፈጣሪዎች ምቹ ሁኔታን ከመፍጠሩ ባሻገር ይህ ውድድር ተማሪዎች፣ዴቨሎፐሮች እና የቴክኖሎጂ ባለሙያዎች አዳዲስ ሃሳቦችን የማፍለቅ፣ክህሎታቸውን የማዳበር እና በዘርፉ ካሉ ዕውቅ ባለሙያዎች ጋር የሚኖራቸውን መተባበር ያሳድጋል ተብሏል፡፡