Ayu Zehabesha-Official አዩዘሀበሻ


Kanal geosi va tili: Efiopiya, Inglizcha


Join our channel for fast and real information. Inbox👉 https://t.me/ayulaw

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Kanal geosi va tili
Efiopiya, Inglizcha
Statistika
Postlar filtri


አሜሪካ በኢትዮጵያ ላይ ጥላው የነበረውን ማዕቀብ አራዘመች‼️
ፕሬዝዳንት ባይደን የሰሜን ኢትዮጵያ ሁኔታ የአሜሪካንን ብሔራዊ ጥቅም የሚጎዳ ነው ብለዋል‼️
አሜሪካ ከሶስት ዓመት በፊት የተቀሰቃሰው የሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት የአሜሪካንን የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ ይጎዳል በሚል ነበር ጦርነቱ እንዲቆም ጫና ስታደርግ የቆየችው፡፡
ይህ ጦርነት በአፍሪካ ህብረት አደራዳሪነት በደቡብ አፍሪካ ፕሪቶሪያ በተደረገ የሰላም ስምምነት ቢቆምም የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች ግን እንደቀጠሉ ናቸው በሚል ማዕቀቡ ተራዝሟል፡፡
በዋሸንግተን ከተወሰዱ እርምጃዎች መካከል በኢትዮጵያ ላይ ብሔራዊ የአስቸኳይ ጊዜ ማዕቀብ የሚባል ሲሆን በፈረንጆቹ መስከረም 2021 ላይ ለሁለት ዓመት የሚቆይ ማዕቀብ ተጥሎ ነበር፡፡
ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ይህ ማዕቀብ ከአንድ ዓመት በፊት ለተጨማሪ አንድ ዓመት እንዲራዘም መፈረማቸው አይዘነጋም፡፡
ፕሬዝዳንቱ ፈርመውበት የነበረው ይህ ማዕቀብ ሊጠናቀቅ 10 ቀናት እየቀሩት ለተጨማሪ አንድ ዓመት ማለትም እስከ መስከረም 2025 ድረስ እንዲራም በፊርማቸው ማጽደቃቸውን ዋት ሀውስ በድረገጹ ላይ ይፋ አድርጓል፡፡
ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን በፈረሙበት ደብዳቤ ላይ እንደተገለጸው በሰሜን ኢትዮጵያ ያለው ሁኔታ አሁንም አለመለወጡን ጉዳዩም ከኢትዮጵያ በተጨማሪ ለምስራቅ አፍሪካ እና ለአሜሪካ የውጭ ጉዳዮች ፖሊሲ ስጋት ነው ተብሏል፡፡
ኢትዮጵያ ከማዕቀቡ በፊት በየዓመቱ ምርቶቿን ከቀረጽ ነጻ በሆነ መንገድ ወደ አሜሪካ ከተሞች በመላክ ከ100 ሚሊዮን ዶላር በላይ ገቢ በማግኘት ላይ ነበረች።
አልአይን
======================
ተጨማሪ ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘትjoin በማድረግ ይከታተሉ👇👇
https://t.me/+Vl6V8k9V3YNEOp2s
https://t.me/+Vl6V8k9V3YNEOp2s


🔥ለአጭር ጊዜ የሚቆይ ታላቅ ቅናሽ👉 ሴኩሪቲ ካሜራ እና አደገኛ አጥር ሽያጭና ገጠማ
በደህንነት ካሜራ እና በአደገኛ የኤሌክትሪክ አጥር 24 ሰዓት ቤትዎንና ድርጅትዎን ይከታተሉ።
       👉የደህንነት ካሜራው
✅በስልክ ይገናኛል
✅live (ቀጥታ) ይቀርፃል
✅እየቀረፀ ያስቀምጣል
✅ በ Ip(ineternet protocol)እና በዲጂታል አማራጭ  
       👉 አደገኛ የኤሌክትሪክ አጥሩ
✅ሲቆረጥ ይጮሃል
✅ ሲነካ ይነዝራል
✅ ሲታገሉት ይጮሃል
✅መብራት ቢጠፋ የራሱ ባትሪ ስላለው ያለማቋረጥ ይሰራል
👉እርስዎ ስራዎት ላይ እና ጤናዎ ላይ ያተኩሩ ደህንነትዎን ለእኛ ተውት
በተመጣጣኝ ዋጋ፣ በታማኝነት በፍጥነት ያሉበት መጥተን እንገጥማለን።
ከነፃ ማማከር ጋር
#ደህንነትዎን እና ቢዝነሶን ይጠብቁ
+251987272201
+251925180598
አድራሻ 👉ብስራተ ገብርዔል ሆም ዲፖ ፊት ለፊት ፒዛ ሀት ያለበት ህንፃ 2ኛ ፎቅ
rel='nofollow'>Https://t.me/Gechtech


የሶማሊያው ፕሬዚደንት ከአብይ አህመድ ጋር አልገናኝም አሉ‼️
ሐሰን ሼይክ ሞሐመድ በቻይና ቤይጂንግ በነበራቸው ቆይታ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ጋር ለመገናኘት ፈቃደኛ እንዳልሆኑ ገልጸዋል።
ጋሮዌ ኦን ላይን ከምንጮቸ አገኘሁት ብሎ እንደዘገበው ይህ የፕሬዚደንቱ ዐቢይን የማነጋገር ፍላጎት ማጣት የአፍሪካ ቀንድ ፖለቲካ መወሳሰቡን ሌላ ማሳያ ነው።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከወራት በፊት በኢትዮጵያ ሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በነበራቸው ቆይታ የሶማሊያው መሪ አገር ለአገር እየዞሩ ከሚከሷቸው ወደ አዲስ አበባ ቢመጡ እና ቢነጋገሩ ይቻል እንደነበረ መግለጻቸው ይታወሳል።
#አዩዘሀበሻ
======================
ተጨማሪ ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘትjoin በማድረግ ይከታተሉ👇👇
https://t.me/+Vl6V8k9V3YNEOp2s
https://t.me/+Vl6V8k9V3YNEOp2s


ማስታወቂያ❗
Buy, sell, or trade cars super easy on our channel.😍

Shop smarter. Live better.

👉http://T.me/EthioCarMarket


«ጦርነት አቁሙ እንኑርበት» ደብረ ሊባኖስ‼️

በኦሮሚያ ክልል ደብረ ሊባኖስ ወረዳ ጦርነት እንዲቆም ህዝቡ በዬው ተረጋግቶ እንዲኖር፣ አርሶ አደሩ አርሶ እንዲበላ፣ ተማሪዎች ትምህርታቸውን እንዲከታተሉ ሰላም ስጡን ጦርነት አቁሙ እንኑርበት በማለት ለሁለተኛ ጊዜ ሰልፍ ወጥቷል።
በሰልፉ ላይ አባ ገዳዎች፣ ሃዳ ሲንቄዎች፣ ታዳጊዎች እና ወጣቶች ተሳታፊ ሆኗል።
======================
ተጨማሪ ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘትjoin በማድረግ ይከታተሉ👇👇
https://t.me/+Vl6V8k9V3YNEOp2s
https://t.me/+Vl6V8k9V3YNEOp2s


✨ መሀል ፒያሳ ላይ ሱቅ 😱
ዓድዋ ዜሮ ዜሮ ላይ ከ አራዳ ጊወርጊስ ፊትለፊት‼️

ፈጠን ለሚሉ ደንበኞቻችን ብቻ‼️

ከ 900,000 ብር ቅድመ ክፍያ ጀምሮ::

ከground እስከ 5ኛ ፎቅ ድረስ ለሽያጭ አቅርበናል!
ቀድመው በመምጣት ጥሩ location ይውሰዱ!!

አከራይተዉ የሚያገኙበት ፣ ነግደው የሚያተርፉበት ነውና ዛሬዉኑ የግሉዎ ያድርጉ።

ለበለጠ መረጃ በ +251983638578 ይደውሉ።

Message us on WhatsApp: https://wa.me/251983638578


በ #ኢትዮጵያ ሰላም እንዲሰፍን፣ ፍትሕና ተጠያቂነት እንዲረጋገጥ 10 የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች 'የሰላም ጥሪ'አቀረቡ‼️
👉በየወሩ በአማካኝ 560 ሰዎች በግጭት ምክንያት ህይወታቸውን እንደሚያጡ ገልፀዋል።
‼️

በአዲሱ 2017 ዓ.ም. በኢትዮጵያ ሰላም እንዲሰፍን፣ ፍትሕና ተጠያቂነት እንዲረጋገጥ፤ የመብቶችና ዴሞክራሲ ዕድገት ማዕከል እና የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ተሟጋቾች ማዕከልን ጨምሮ 10 የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች፤ የሰላም ጥሪ አቀረቡ።

ድርጅቶቹ በጋራ ባወጡት የሰላም ጥሪ መግለጫ በ2016 ብቻ በመላው ኢትዮጵያ ከ1,792 በላይ የግጭት ኩነቶች የተመዘገቡ መሆኑን ገልጸው በነዚህ ግጭቶችም በጥቅሉ ከ6,164 በላይ ሰዎች መሞታቸው ተዘግቧል ብለዋል።

ይህም ማለት በግጭቶች ሳቢያ ብቻ በየወሩ በአማካይ 560 ሰዎች የተገደሉበት ዓመት እንደነበር አመላክተዋል። 

በ #አማራ ክልል፣ በ #ኦሮሚያ እና ሌሎች ክልሎችም የዘፈቀደ እስሮች፣ በከተማዎች ውስጥ እና አቅራቢያ በሚደረጉ የተኩስ ልውውጦች ሳቢያ የሚፈጠር አለመረጋጋትና መሸበር፣ እንዲሁም እነዚህን ቀውሶች ያስከተሉት የኑሮ ውድነት እና ጫና በአገሪቱ ተባብሰው ተስተውለዋል ብሏል።
======================
አስተማማኝ እና ፈጣን ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን join በማድረግ ይከታተሉ👇👇
https://t.me/+Vl6V8k9V3YNEOp2s
https://t.me/+Vl6V8k9V3YNEOp2s


🎉 እንኳን ለአዲሱ ዓመት በሰላም አደረሳችሁ! 🌼
አፍሮ ስፖርት በዓልን ምክኒያት በማድረግ በሽልማቶች ሊያንበሸብሾት ነው! 🥳 💰

አሁኑኑ ወደ ድህረ ገጻችን👉  https://bit.ly/3XbY3o7
በመሄድ በቦነሶቹ ይንበሽበሹ።

አፍሮስፖርት ማህበራዊ ገጾቻችንን Follow በማድረግ በየሳምንቱ የተለያዩ ሽልማቶችን ያሸንፉ፣ ቤተሰብ ይሁኑ። 👇
Telegram
Facebook
Instagram
TikTok
Website


በ11 ወራት ውስጥ ብቻ 15 ሺ ዜጎች ሕጋዊ ባልሆነ መንገድ እንዲወጡ ያደረጉ ኤጀንሲዎች ባለቤቶች በቁጥጥር ስር እንዲውሉ መደረጉን የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት አስታወቀ‼️
የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት እንዳስታወቀው፤ ሕገ-ወጥ የሰዎች ዝውውርን አስመልክቶ በሀገር ውስጥና በውጭ ሀገራት ወንጀሉን በመፈፀም ላይ የሚገኙ አካላትንና የትስስር ሰንሰለታቸውን ለመለየት ሰፊ ጥናትና ክትትልና ሲያደርግ ቆይቷል፡፡ ጥናቱንና ክትትሉን መነሻ በማድረግ ከኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ጋር በመቀናጀት በተከናወነው ስምሪት በድርጊቱ ሲሳተፉ ተደርሶባቸው የተጠረጠሩ የ49 ኤጀንሲዎች ባለቤቶች በቁጥጥር ስር ውለዋል፡፡
ላለፉት 11 ወራት ውስጥ ብቻ ገንዘብ በመቀበል ከ15,000 በላይ ዜጎችን በህገወጥ መንገድ ወደ ውጪ ሀገር መላካቸውን ደርሼበታለሁ ሲል የብሄራዊ መረጃ እና ደህንነት አገልግሎት አስታውቋል።
አዩዘሀበሻ
======================
አስተማማኝ እና ፈጣን ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን join በማድረግ ይከታተሉ👇👇
https://t.me/+Vl6V8k9V3YNEOp2s
https://t.me/+Vl6V8k9V3YNEOp2s


🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻

እንኳን አደረሳችሁ እያልን  የአዲስ አመት ልዮ ስጦታ !!!

እስከ አዲስ አመት ብቻ የሚቆይ  ቅናሽ
እንዳያመልጥዎ  📍

በ447,000 ብር የቤት ባለቤት  ይሁኑ ።

ቤት መግዛት አሁን ነው የምንለዎት በምክንያት ነው።

የዶላር መጨመር እንዳያሳስቦ እኛ ጋር ሽያጭ በኢትዮጲያ  ብር ነው።

                       ➡️በሲኤሚሲ ሚካኤል

                       ➡️አያት ባቡር ጣቢያ

                       ➡️ በሲኤሚሲ የተባበሩት

                       ➡️ በአያት ዞን 3

የሚገኘውን  ሳይቶቻችንን  እነሆ
ለደንበኞቻችን  ጀባ  ብለናል ።

            ✳️  ከባለ 1 መኝታ -ባለ 4 መኝታ

            ✳️  ከ70 ካሬ -150 ካሬ

✏️ ከአያት ሪልእስቴት  ቤት  ሲገዙ  ከሚያገኙት ጥቅም  በትንሹ

    ❇️     ሽያጭ በኢትዬጲያ ብር እንጂ      በዶላር አይደለም ። 
     ❇️    ነፃ የመኪና ማቆሚያ
     ❇️    ሠፊ የልጆች መዝናኛ
     ❇️    የሠርግ አዳራሽ እና የልጆች kG ት/ቤት
    

❇️ በ 8% ቅድመ ክፍያ

✅   ያስተውሉ ሽያጭ በኢትዮጲያ ብር ነው ቤትዎን እስኪረከቡ ምንም አይነት የዋጋ ጭማሪ አይደረግቦዎትም

  🕐🕑  ይፍጠኑ ቤት የመግዛት ሀሳብ ካልዎት  ለተወሠነ  ቀን  እና ለተወሠኑ ቤቶች ብቻ የሚቆይ ቅናሽ ስለሆነ  እንዳያመልጥዎት

📱 ለበለጠ መረጃ   እና ሳይት ለመጓብኘት 

በቀጥታ   📞   0920483756/0913173557 ወይም በቴሌግራም  በዋትሳፕ ይደውሉ


በበ18-6-58-16_New_compressed.pdf
14.9Mb
Update❗ተረጋግጧል👆‼️
ከመጪው መስከረም 1/2017 ዓ.ም ጀምሮ የሚተገበረው አዲሱ የደመወዝ ጭማሪ ከሰዓታት በፊት ያጋራሁት ሲሆን የሁሉም የመንግሥት ሰራተኞች የደመወዝ ጭማሪ breakdown ትክክለኛ መሆኑ ተረጋግጧል።
ይህ በፋይናንስ ሚኒስቴር እና በሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን በኩል ተጠንቶ የቀረበው የደሞዝ ጭማሪ በሚኒስትሮች ምክር ቤት እንዲፀድቅ መቅረቡም ተመላክቷል። የሚኒስትሮች ምክር ቤት ካፀደቀው በኋላ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሚቀርብ ይሆናል።
የሚዲያ ተቋማት፣ለመከላከያ ሰራዊት አባላት፣ለፌደራል ፖሊስ፣ለክልሎች፣ለብሄራዊ መረጃ እና ደህንነት....ሙሉ መረጃ የተያያዘ ሲሆን ያላያችሁ ሙሉ መረጃው ከላይ የተያያዘውን ፋይል በመክፈታ ማየት ትችላላችሁ።
#አዩዘሀበሻ
======================
አስተማማኝ እና ፈጣን ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን join በማድረግ ይከታተሉ👇👇
https://t.me/+Vl6V8k9V3YNEOp2s
https://t.me/+Vl6V8k9V3YNEOp2s


Save the date❗❗👇
የ 12ኛ ክፍል ፈተና ዉጤት የፊታችን ሰኞ ይለቀቃል‼️
የ 12ኛ ክፍል ፈተና ዉጤት የፊታችን ሰኞ ይፋ እንደሚደረግ ከትምህርት ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ ያመላክታል።
ወደተለያዩ ዩኒቨርስቲዎች በመግባት የ12ኛ ክፍል ፈተናን የወሰዱ ተማሪዎች ዉጤታቸዉ በአዲስአመት መቃረቢያ ጷግሜ 4 ቀን 2016 ዓ.ም ይለቀቃል።
#አዩዘሀበሻ #የ12ኛ #ውጤት
======================
ተጨማሪ ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘትjoin በማድረግ ይከታተሉ👇👇
https://t.me/+Vl6V8k9V3YNEOp2s
https://t.me/+Vl6V8k9V3YNEOp2s


የስልክ ጥሪ እንዲቋረጥ የተደረገባቸው አካባቢዎች‼️
ትናንት ከሰዓት ጀምሮ በኦሮሚያ ክልል ከሸገር ከተማ -እስከ ሰላሌ፣ሸኖ፣በአማራ ክልል በመተማ እና አካባቢው(ዛሬ ከሰዓት ጀምሮ)፣በሰሜን ሸዋ ዞን ሸዋሮቢት(ትናንት)፣በሰሜን ወሎ ቆቦ ዙሪያ እና በሌሎች በተመረጡ ቦታዎች የስልክ ጥሪ  አገልግሎት ተቋርጧል።
ትናንት ጀምሮ "በበርካታ ቦታዎች ድንገተኛ ፍተሻ እና ቁጥጥር እየተደረገ ነው፣ እጅግ በርካታ ቁጥር ያላቸው ሰዎች ሰው በማገት ወንጀል ጭምር የተጠረጠሩ ሰዎች እየተያዙ ነው።
ራሱን የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት ብሎ የሚጠራው ኦግ ሸኔ እና ቄሮ ቢሉሱማ ኦሮሞ የተባለ የወጣቶች ቡድን በጋራ በክልሉ ከዛሬ አርብ ጰጉሜ 1 ጀምሮ የገበያ አድማ እና የትራንስፖርት እቀባ ጥሪ ሲያተላልፉ የነበሩ ግለሰቦችን ለመያዝ ነው ተብሏል። በአማራ ክልል ሰሜን ወሎ ዞን ወልዲያ ከተማ ዙሪያ ዛሬ ጠንከር ያለ የተኩስ ልውውጥ መኖሩምን ምንጮቼ ገልፀዋል።
አዩዘበሀሻ
======================
ተጨማሪ ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘትjoin በማድረግ ይከታተሉ👇👇
https://t.me/+Vl6V8k9V3YNEOp2s
https://t.me/+Vl6V8k9V3YNEOp2s


#Newsflash‼️
የኢትዮጵያ ልማት ባንክን ላለፉት አራት አመታት በፕሬዝዳንትነት ሲመሩ የነበሩት እና ከሀገራችን ባንኮች በካፒታል ሁለተኛ እንዲሁም አሁን ለደረሰበት ስኬት ያበቁት ዶክተር ዮሐንስ አያሌው በራሳቸው ፈቃድ ለመልቀቅ ያቀረቡት ጥያቄ በቦርዱ ተቀባይነት አግኝቶ ከትናንት ነሐሴ 30/2016 ዓ.ም ጀምሮ ከፕሬዝዳንትነት ለቀዋል። እርሳቸውን ተክቶ አቶ ጌታቸው ዋቄ  በጊዜያዊነት እንዲመሩ መመደባቸውን የደረሰኝ መረጃ ያመላክታል(አዩዘበሀሻ)።
======================
ተጨማሪ ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘትjoin በማድረግ ይከታተሉ👇👇
https://t.me/+Vl6V8k9V3YNEOp2s
https://t.me/+Vl6V8k9V3YNEOp2s


የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ ሽንኩርት ከታንዛንያ ማስገባቱን አስታወቀ‼️
የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ የኮሙኒኬሽን ጉዳዮሽች ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ሰውነት አየለ ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንደተናገሩት መጪው ዘመን መለወጫ በዓል ገበያው ላይ የአቅርቦት እጥረት እንዳይፈጠር ከክሎች ባለፈም ከታንዛኒያ ሽንኩርት ማስገባታቸውን ተናግረዋል፡፡
በተለይ የእሁድ ገበያ ላይ ከሸማች ህብረት ስራ ማህበራት ጋር በተያያዘ እንቅስቃሴዎች እየተደረጉ መሆኑን እና ታንዛኒያን ጨምሮ ከተለያዩ ሀገራት ሽንኩርት ወደ ከተማዋ ማስገባት መቻላቸውን አንስተዋል።
በቅርቡ ለተፈጠረው የሽንኩርት መወደድ ምክያትም በሽንኩርት ማሳዎች ውስጥ ውሃ ተኝቶበት እንደሆነ ተናግረው ከኦሮሚያ ከሶማሌ እንዲሁም ከሌሎች ክልሎችም ጭምር ምርት መግባቱን ተናግረዋል፡፡
ቢሮው ሽንኩርትን ከውጪ ወደ ሀገር ውስጥ ለማስገባት እና ለሸማቾች ህብረት ስራ ማህበራት በጋራ ስራዎችን መሰራቱንም ገልጧል፡፡

ዳይሬክተሩ አላስፈላጊ የገበያ ጭማሪ የሚያደርጉ ነጋዴዎችን የመከታተል ስራዎች መሰራታቸውን እና በተለይ ደግሞ ንግድ ፍቃድ ኖሯቸው እየሰሩ ባሉ አካላት ላይ ከፈቃድ ማስጠንቀቂያ እስከ ፅሁፍ ማስጠንቀቂያ ድረስ እየተሰጠ መሆኑን ጨምረው ገልፀዋል፡፡

በዚህም ለበዓሉ የሽንኩርት፣ የእንቁላል፣ የዘይት፣ የዱቄት፣ የቁም እንሰሳት ፣ የቅቤ፣ የጤፍ ምርቶች ላይ ከኦሮሚያ ክልል እንዲሁም ከአዲስ አበባ የንግድ ስራዎች ድርጅትና ከህብረት ስራ ኮምሽን ጋር በመቀናጀት ተመጣጣን በሆነ ዋጋ እየቀረቡ መሆናቸው ገልጸዋል፡፡
======================
ተጨማሪ ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘትjoin በማድረግ ይከታተሉ👇👇
https://t.me/+Vl6V8k9V3YNEOp2s
https://t.me/+Vl6V8k9V3YNEOp2s


በበ18-6-58-16_New_compressed.pdf
14.9Mb
የደመወዝ ጭማሪ ጉዳይ‼️
በቅርቡ ይፀድቃል ተብሎ የሚጠበቀው አዲሱ የመንግሥት ሰራተኞች የደመወዝ ጭማሪ አዋጅ Draft ከላይ የተያያዘው ነው በሚል እየተሰራጨ ይገኛል። በዚህ ጉዳይ የሚመለከተው አካል እስካሁን በይፋ የሰጠው መረጃ የለም።
ባሳለፍነው ሰኔ ወር ጠቅላይ ሚኒስትሩ 1500 ወርሃዊ ደመወዝ ለሚከፈለው ሰው የ300% የደመወዝ ጭማሪ መደረጉን ገልፀው አጠቃላይ ለመንግሥት ሰራተኞች የሚደረገው የደመወዝ ጭማሪ ከ91 ቢሊዮን ብር በላይ ተጨማሪ በጀት ጠይቆናል ማለታቸው ይታወሳል።
አዩዘሀበሻ
======================
ተጨማሪ ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘትjoin በማድረግ ይከታተሉ👇👇
https://t.me/+Vl6V8k9V3YNEOp2s
https://t.me/+Vl6V8k9V3YNEOp2s


‘’አነቃቂ ንግግር’’ በሚል የሚሰጠው  ስልጠና ምንነትና ጠቀሜታው ሊፈተሽ እንደሚገባ እና በዚህ ረገድ የቁጥጥር ስርዓት መኖር እንዳለበት የማህበራዊ ሳይንስ ባለሞያዎች እየተናገሩ ነው፡፡

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ አንዳንዶች የስልጠና ማዕከል ከፍተው ሌሎች ደግሞ ማህበራዊ ሚዲያን ተጠቅመው አነቃቂ በሚል መልዕክቶችን ሲያስተላልፉ ይሰማል፡፡

‘’እኔ በዚህ መንገድ ሄጄ ተሳክቶልኛል፤ እናንተም እንዲሳካላችሁ በዚህ መንገድ ሂዱ’’ ሲሉ መስማት እተለመደ መጥቷል፡፡

በ’’አነቃቂ ንግግር’’ ስም የሚተላለፉ እነዚህና መሰል መልዕክቶች ስርዓት ሊበጅላቸው ይገባል ተብሏል፡፡

‘’አንዳንዶቹ መልዕክቶች በተጨባጭ መሬት ላይ ያለውን እውነታ የካዱ ከመስራት ይልቅ ሰዎችን ወደ ምኞት ዓለም የሚያስገቡ፣በአቋራጭ መንገድ ተጠቅመው የሚፈልጉበት መድረስን የሚያበረታቱ’’ መሆናቸውን እንዳስተዋሉ የማህበረሰብ ጥናት ባለሙያና አማካሪው አቶ ቴዎድሮስ አዱኛ ነግረውናል፡፡

በተጨማሪም እነዚህ አነቃቂዎች ‘’ሰዎች ለዘመናት ከኖሩበት እሳቤ ወጥተው አፈንጋጭ እንዲሆኑ የሚያደርጉ፣ የስኬት መንገድ አነቃቂዎቹ የሚሉት ብቻ እንደሆነ አድርገው የሚያስተምሩ’’ መሆናቸው እንዳሳሰባቸው አማካሪው አቶ ቴዎድሮስ ያስረዳሉ፡፡

በዚህ መንገድ የሚተላለፉ መልዕክቶች እየበረከቱ እና በአብዛኛው ከተሞች አካባቢ ያለው ማህበረሰብ እየተከተላቸው በመሆኑ የሚሰጡት ስልጠናም ይሁን ትምህርት ምንነቱ ታውቆ በመንግስት ቁጥጥር እንዲደረግበትም ጠይቀዋል፡፡

የማህበረሰቡን መስተጋብር የሚያላሉ በደመነ ነፍስ የሚነገሩ አነቃቂ ንግግሮች እንዳሉ ሁሉ የሰዎች ህይወት ላይ ትርጉም ያለው ለውጥ የሚያመጡ እንዳሉም አይዘነጋም፡፡
Sheger Fm
join በማድረግ ይከታተሉ👇👇
https://t.me/+Vl6V8k9V3YNEOp2s
https://t.me/+Vl6V8k9V3YNEOp2s


የሱዳን ጦር ከፋኖ ሀይሎች ሸሽተው ወደ ሱዳን የገቡ የኢትዮጵያ ወታደሮችን ትጥቅ ማስፈታቱ ተነገረ‼️
እንደ ሱዳን ትሪቢዩን ዘገባ የኢትዮጵያ ወታደሮች የድንበር ከተማ በሆነችው መተማ ከፋኖ ታጣቂዎች ጋር የነበረውን ውጊያ ተከትሎ ወደ ሱዳኗ ገላባት ከተማ ሸሽተዋል። የፋኖ ታጣቂዎች መልሰው የያዙትን መተማ ከተማን ሰኞ ዕለት ለአጭር ጊዜ ለቀውት እንደነበር ነው የተገለጸው። መተማ ላይ ውጊያ በሚካሄበት ጊዜም በርካታ የመንግሥት ወታደሮች እና «በመቶዎች የሚቆጠሩ ሲቪሎች» ወደ ሱዳን ግዛት ውስጥ በመግባት ተጠልለዋል። የሱዳን ወታደሮችም 77 የኢትዮጵያ ወታደሮችን ትጥቅ እንዳስፈቱ ዘገባው አመልክቷል። ሱዳንም ከረቡዕ ዕለት ጀምሮ ወደ ኢትዮጵያ የሚያሸጋግረውን የድንበሯን አካባቢ በመዝጋት ተጨማሪ ወታደሮቿን ማሰማራቷንም ሱዳን ትሪቢዩን በዘገባው ጠቅሷል። መተማ ላይ በፋኖ ታጣቂዎችና በመንግሥት ወታደሮች መካከል የሚካከል ጋብ ብሎ የነበረው ተኩስ ትናንት ከቀትር በኋላ 11 ሰዓት ገደማ ዳግም ማገርሸቱን የአካባቢው ነዋሪዎች ለዶይቸቨሌ መናገራቸው ይታወሳል።
#አዩዘሀበሻ #Ethiopia
=======≠=[=[=[[=======
ለፈጣን፣ሚዛናዊ እና አስተማማኝ ወቅታዊ መረጃዎች ቻናላችንን join በማድረግ ይከታተሉ👇👇
https://t.me/+Vl6V8k9V3YNEOp2s
https://t.me/+Vl6V8k9V3YNEOp2s

18 ta oxirgi post ko‘rsatilgan.