በአዲስ አበባ የመምህራን ሆስፒታል እየተገነባ መሆኑን ተሰማ
በአዲስ አበባ ከተማ የሚገኙ መምህራን ለከተማ መስተዳድሩ ባቀረቡት ጥያቄ መሰረት፤ ለመምህራን አገልግሎት የሚውል ሆስፒታል ግንባታ ፕሮጀክት መጀመሩን የአዲስ አበባ መምህራን ማሕበር አስታውቋል።
ፕሮጀክቱ ለመምህራን ልዩ ድጋፍ ለማድረግ ያለመ ሲሆን፤ ሆስፒታልን ጨምሮ ለንግድ ሥራ የሚውል ሁለገብ ሕንፃ በግንባታ ላይ መሆኑን የማሕበሩ የኮሙኒኬሽን ኃላፊ አቶ ሳሙኤል ሙሴ ለአሐዱ ተናግረዋል።
በአዲስ አበባ ይገነባል የተባለውን የመምህራን ሁለገብ ሕንፃ ኡራኤል አካባቢ የሚገነባ ሲሆን፤ ከአዲስአበባ ከተማ መስተዳድር 50 ሚልየን ብር ድጋፍ እንደተደረገለት አቶ ሳሙኤል ሙሴ ገልጸዋል።
ሕንፃው በ36 ሺሕ ካሬ ሜትር መሬት ላይ ያረፈ ስለመሆኑም ተናግረዋል።
የመምህራን ሆስፒታሉ ማስገንብያ መዋእለ ንዋይ ከህብረተሰቡና ከደጋፊ ተቋማት ለማሰባሰብ ውጥን የተያዘለት መሆኑን አሐዱ ከኮሙኒኬሽን ኃላፊው መረዳት ችሏል።
ለመምህራን የቤት ግንባታ አበዳሪ የፋይናንስ ተቋምና አነስተኛ ወለድ የሚያገኙበት ባንክ በማፈላለግ ላይ መሆኑንም ማሕበሩ ገልጿል።
ከመምህራን የሚነሱ ጥያቄዎችን ለመፍታት ማሕበሩ በብርቱ እየተንቀሳቀሰ መሆኑን የገለጹት የኮሚኬሽን ኃላፊው፤ ከዚህ በተጨማሪም የመምህራን ባንክ ለማቋቋም ውጥን መያዙንም አንስተዋል።
በአዲስ አበባ ከተማ መምህራን ማሕበር በሥሩ ወደ 33 ሺሕ የሚጠጉ አባላት ያለው መሆኑንና፤ በየጊዜው ከመምህራን የሚነሱ ጥያቄዎችን ለመፍታት እየሰራ መሆኑን የኮሙኒኬሽን ኃላፊው ገልጸዋል።
በኢትዮጵያ ተቋቁመው ሥራ ላይ ከሚገኙ የሙያ ማሕበራት መካከል የአዲስ አበባ ከተማ መምህራን ማሕበር ግንባር ቀደሙ ተጠቃሽ መሆኑን ይታወቃል።
⬇️⬇️⬇️⬇️⬇️👇👇👇👇⬇️⬇️
የቴሌግራም ቻናላችንን join በማድረግ ወቅታዊ መረጃዎችን በቀላሉ ይከታተሉ፣ሊንክ👇
https://t.me/+Vl6V8k9V3YNEOp2s