ናሁ ተፈጸመ ማህሌተ ጽጌ
ማህሌተ ጽጌ
ኢየኃፍር ቀዊመ ቅድመ ስእልኪ ወርኃ ጽጌረዳ አመ ኃልቀ፤ዘኢየኃልቅ ስብሐተኪ እንዘ እሴብሐኪ ጥቀ፤ተአምርኪ ማርያም ከመ አጠየቀ፤ጸውዖ ስምኪ ያነሥእ ዘወድቀ፤ኃጥአኒ ይሬሲ ጻድቀ፡፡
👉ትርጉም
እጅግ ብዙ የማያልቅ ምስጋናሽን እያመሰገንኩኝ : የጽጌረዳ ወራት ባለቀ ጊዜ በስዕልሽ ፊት መቆምን አላፍርም : ማርያም ተዓምርሽ እንዳስረዳ ስምሽን መጥራት የወደቀን ያነሳል : ኃጥኡንም ጻድቅ ያደርጋል ።
👉ምስጢር
የጽጌረዳ ወራት ባለቀ ጊዜ በሥዕልሽ ፊት መቆምን አላፍርም ማለቱ ከመስከረም 26 - ኅዳር 5 የቆየው የጽጌ ወቅት ቢያልፍም እኔ ግን ምስጋናሽን አላቋርጥም ይላል የዚህ ክፍል ጥንተ ነገሩ ዘካርያስ የሚባል ሰው የእመቤታችንን ሥዕል ያገኛል ፤ በጣም ተደሰተ ፤ የእመቤታችን ፍቅር አደረበትና ምን ላድርግላት ብሎ ተጨነቀ ።
ወቅቱ የጽጌ ነበርና እለት እለት 50 አበባ ለሥዕሏ አደርጋለሁ አለ ። እንዳለውም በየቀኑ ሀምሳ ጽጌሬዳ እየቆረጠ ለሥዕሏ ያደርግ ነበር ። በኋላ የአበባ ጊዜ ሲያልፍ አበቦችን ማግኘት ስለማይችል ምን ላድርግ ብሎ አሰበ ፤ በአበቦቹ ፈንታ ሀምሳ ጊዜ በሰላመ ቅዱስን አደርሳለሁ ብሎ ማድረስ ጀመረ ።
ከእለታት በአንዱ ቀን ወደ ሌላ ሀገር ሲሄድ መንገድ ላይ ሽፍታዎቹ አግኝተውት እርሱ በሰላመ ቅዱስ ገብርኤል መልአክ እያለ ይጸልያል ፤ እመቤታችን ለሽፍቶች ተገልጣ አንድ በሰላመ ቅዱስ ሲል አንድ አበባ ስትቀበል ይመለከታሉ ፤ ሀምሳውን ሲጨርስ ሀምሳ አበባ ።
የዚህን ጊዜ ሽፍታዎቹ በግንባራቸው ተደፍተው ሰገዱለት ፤ በኋላም አምነው መነኮሳት ሆነዋል ። እናም ይህ የጽጌ ምሥጋና ቢያልቅም የእመቤታችን ምሥጋና እንደማይቋረጥ ሲገልጽ ነው ፤ በውዳሴ ማርያም ፣ አርጋኖን ፣ ማኅሌት ፣ ሰዓታቱ ትመሰገናለችና ።
ስምሽን መጥራት የወደቀን ያነሣል ማለቱ አንድ እመቤታችን የሚወድ ሰው ነበር ፤ ከተወደደ ልጇ ጋር ሥዕሏን ስሎ በመሰላል ወጥቶ ዲያቢሎስ በሲኦል ነፍሳትን መከራ ሲያጸናባቸው እየሣለ እያለ ዲያቢሎስ ተናድዶ መሰላሉን መትቶ ሊጥለው ወደ ታች ሊወድቅ ሲሄድ ከሳላት ሥዕል የእመቤታችን እጅ ወጥቶ ይዞ አድኖታል ።
ኃጥኡንም ጻድቅ ያደርጋል ሲል በቃልኪዳኗ ልጄ ወዳጄ ማርልኝ ብላ ስትለምን ስለ እናትነቷ ይምራልና ኃጥኡንም ጻድቅ ያደርጋል ብሏል ።
ማህሌተ ጽጌ
ለንጉሠ ነገሥት ሰሎሞን ከመ ተፈሥሐ ልቡ፤በዕለተ ወፃእኪ መርዓት ለአንበሳ ትንቢት እምግቡ፤ማዕከለ ማኅበር ፍሡሓን ተአምረኪ ዘይነቡ፤እዜምር ለኪ ጽጌ ሐና ወፍኖተ ነፈርዓፅ እሌቡ፤ከመ ጣዕዋ ሐሊበ ዘይጠቡ።
ትርጉም
የሀና አበባ ሆይ!ሐሴትን በተመሉ ( ማኅበረ ጻድቃን)ማኅበር መካከል ተአምርሽን የሚናገር የነገሥታት ንጉሥ ሰሎሞን ሙሽሪት ከአንበሳዉ ትንቢት ዋሻ በወጣሽ ጊዜ ልቡ ሐሴት እንዳደረገ እንደ ሚጠባ እንቦሳ የመፈርጠጫ ቦታየን አስተውላለሁ፤ እዘምርልሽም አለሁ።
ማኅሌተ ጽጌ
ኅብረ ሐመልሚል ቀይሕ ወፀዓድዒድ አርአያ ኰሰኰስ ዘብሩር ተአምርኪ ንጹሕ በአምሳለ ወርቅ ግቡር ተፈጸመ ናሁ ማኅሌተ ጽጌ ሥሙር አስምኪ ቦቱ ንግሥተ ሰማይ ወምድር ከመ በሕፅንኪ ያስምክ ፍቁር ።
ትርጉም
የሚያብረቀርቅ ቀይነ ነጭ ቀለም ያለው አርአያው የብር ዝንጉርጉር የሆነ ንጹሕ ተዓምርሽ በወርቅ አምሳል የተሰራ ነው ፤ እነሆ የተወደደ መልካም ማኅሌተ ጽጌ ተፈጸመ ፤ የሰማይና የምድር ንግሥት ማርያም ሆይ የተወደደ ልጅሽ በእቅፍሽ እንዲጠጋ (እንዲንተራስ ) በእርሱ አማጽኝ ።
ምስጢር
ቀይና ነጭ ቀለም ያለው ማለቱ ቀይ በትስብእቱ ነጭ በመለኮቱ ማለትም ፍጹም ሰው ፍጹም አምላክ ዝንጉርጉርም ያለው ሰው እና አምላክነቱን ነው ( እንዘ ተኃቅፊዮ ላይ በሰፊው አይተናል )
ተአምርሽ በወርቅ አምሳል የተሰራ ነው ሲል ወርቅ የንጽሕና ምሳሌ ነውና እመቤታችንም ንጽሕተ ንጹሐን ናትና ። | ኵለንታሃ ወርቅ |
ወርኀ ጽጌ አልቋል ሲል ተፈጸመ ማኅሌተ ጽጌ ስሙር አለ የሰማይና የምድር ንግሥት ( መዝ 44 )
ስብሐት ለእግዚአብሔር
ወለወላዲቱ ድንግል
ወለመስቀሉ ክቡር ... አሜን !
ከሌላ ቻናል ትማሩበት ዘንድ የተላከ
@yetewahedofera