፩
የቅዱስ ኤፍሬም ድርሳን ስለ ጾም ስለ ጸሎትና ንስሓ
ቅዱስ ኤፍሬም ስለ ጾም ስለ ጸሎትና ስለ ንስሓ የተናገረው ድርሳን ይህ ነው።
ቅዱስ ኤፍሬም መልካሙን ክፉ ክፉውን መልካም ለሚሉ ወዮላቸው አለ፡፡ ጾምን የሚንቁ መጾም መልካም አይደለም ለሚሉ ወዮላቸው፡፡ ርስት ትሆነው ዘንድ አዳም በጾምና በጸሎት ወደ ገነት ገብቷልና፡፡ ዳግመኛም ሙሴ በጾምና በጸሎት ከእግዚአብሔር ጋር ይነጋገር ዘንድ ባለሟልነትን ተቀበለ፡፡
ዳግመኛም ኤልያስም በጾምና በጸሎት ወደ ሰማይ ዐረገ፤ ከሞትም ዳነ፡፡ በጾምና በጸሎት የነቢዩ የዳዊት ኃጢአት ይቅር ተባለለት፡፡ ከጻድቃን ጋርም ተቆጠረ፡፡ የነነዌ ሰዎች በጾምና በጸሎት ከጥፋት ዳኑ፡፡ ለሕይወትም የተገቡ ሆኑ። በጾምና በጸሎት ዳንኤል ነቢይ ከተራቡ አናብስት አፍ ዳነ፡፡ ስለ ክርስቶስም ትንቢት ተናገረ፡፡
በጾም በጸሎት ኤርምያስ በሚገባ ስለ ክርስቶስ ስቅለት ትንቢት ተናገረ፡፡ በጾም በጸሎት ነቢዩ ሕዝቅኤል እግዚአብሔር በጌትነቱ ሥልጣን ሁኖ በሠረገላ ተመለከተ፡፡ የጥምቀትን በር ይገልጥ ዘንድ በጾምና በጸሎት ለዮሐንስ ተሰጠው፡፡ በትሕትናው ብዛትም ከሴቶች ከተወለዱት ሁሉ ከፍ ያለ ሆነ፡፡ በጾምና በጸሎት እግዚአብሔር የንጉሡን የሕዝቅያስን ልመና ሰማ፡፡ በዕድሜው ላይም ዓሥራ ዐምስት ዓመት ጨመረለት፡፡
በጾምና በጸሎት እግዚአብሔር ምናሴን ከጋለው የብረት ምስል አዳነው፡፡ ከችግሩም ታደገው:: ያዕቆብ በፍኖተ ሎዛ ተኛ፡፡ በጾምም እስከ ሰማይ የሚደርስ መሰላልን ዐየ፡፡ ጌታችን ዐርባ ቀን ጹሞ ሰይጣንን አሳፈረው፡፡ ሰይጣንም ከፊቱ ሸሸ፡፡ የክርስቶስ ደቀመዛሙርትም በጾም ከትንሣኤ በኋላ አምላካቸውን ክርስቶስን ለማየት በቁ፡፡
ይቀጥላል....
(ቅዱስ ኤፍሬም ድርሳን በእንተ ጾም ወጸሎት ወንስሓ ➛ በድርሳነ ሠለስቱ ሊቃውንት መጽሐፍ ገጽ 189-199 በመምህር ቃለጽድቅ ሕግነህ የተተረጎመ)