ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ስለ እውነተኛ ጾም፤ የሰውን ሥጋ ከመብላት በላይ ክፉ ስለ ኾነው ሐሜት በተናገረበት ድርሳኑ እንዲህ አለ፦
ወዳጄ ሆይ! ሰው አስፈራርቶሃልን? በሰማያት ወዳለው ጌታ ተፋጠን፤ ምንም ክፉ ነገርም አይደርስብህም፡፡ እንዲህ በማድረጋቸው የቀደሙ ሰዎች ከመከራቸው ሊድኑ ችለዋል፤ ወንዶች ብቻ አይደሉም፤ ሴቶችም ጭምር እንጂ፡፡ አስቴር የምትባል አንዲት ዕብራዊት ሴት ነበረች፡፡ ይህቺ አስቴርሊጠፉ ሲሉ በዚሁ ዘዴ መላው እስራኤላውያንን ታድጋቸዋለች፡፡ የፋርስ ንጉሥ ኹሉም እስራኤላውያን በአስቸኳይ እንዲገደሉ ትእዛዝ ባስተላለፈና በቊጣው ፊት ሊቆም የሚችል ማንም ባልነበረበት ጊዜ+ ይህቺ ሴት የደስታ ልብሷን አውልቃ የኀዘን ልብሷን ስትለብስ፣ በራሷ ላይ ዐመድና ትቢያ ስትነሰንስ፣ ወደ ንጉሡ ስትኼድ ጊዜ ቸሩ እግዚአብሔር ከእርሷ ጋር እንዲኾን ስትማጸን፤ ጸሎቷንም ስታቀርብ የተናገረቻቸው ቃላት እነዚህ ነበሩ “ጌታ ሆይ! ቃሎቼ በአንተ ዘንድ የተወደዱ ይኹኑ፣ በአንደበቴም በጎ ነገርን አድርግ" (አስቴ.4፡17)፡፡ ስለ መምህራችን ወደ እግዚአብሔር የምናቀርበው የእኛ ጸሎትም ይህ ሊኾን ይገባል፡፡ አንዲት ሴት ስለ እስራኤላውያን ስለ ጸለየች የአረማውያንን ንጉሥ ቊጣ ካበረደችው ከዚህ ታላቅ ቤተ ክርስቲያን ጋር ኾኖ ስለ ታላቂቱ ከተማ የሚለምነው መምህራችንም ከዚህ በበለጠ መልኩ ትሑቱንና ርኅሩኁን ንጉሥ ማሳመን ይችላል፡፡
እግዚአብሔርን በመበደል የተሠሩትን ኃጢአቶች የመፍታት ሥልጣን ካለው ሰውን [ንጉሡን] የበደሉትን ደግሞ ይበልጥ ሊፈታቸውና ከቊጣው ሊስውራቸው ይቻሏል፡፡ እርሱ ራሱም ገዢ ነው! ገዢነቱም ከሌላው [ኹሉ] የከበረ ነው፡፡ ምክንያቱም በንጉሡ ላይ ተፈጻሚ የሚኾኑ ቅዱሳት ሕጎችም ቢኾኑ ተፈጻሚ የሚኾኑት በእርሱ ነውና፡፡ ከላይ ከአርያም በጎ ነገርን ሲፈልግ ንጉሡ ወደ ካህኑ ይኼድ ዘንድ አለው፤ ካህኑ ግን ይህን ፈልጎ ወደ ንጉሡ አይኼድም፡፡ [እንዴት ያልከኝ እንደ ኾነም እንዲህ ብዬ እመልስልሃለሁ] እርሱም ጥሩር አለውና ይኸውም የጽድቅ ጥሩር ነው፡፡ መታጠቂያ [ቀበቶ] አለው፤ እርሱም የእውነት መታጠቂያ ነው፡፡ እጅግ የተከበረ ጫማ አለው፤ እርሱም የሰላም ወንጌል ነው፡፡ ሰይፍ አለው፤ ከብረት የተሠራ ግን አይደለም፤ ከመንፈስ እንጂ፡፡ ዳግመኛም በራሱ ላይ ቁር አለው፡፡ ይህ የትጥቅ ልብስ እጅግ ግርማ ሞገስ ያለው ነው፡፡ የጦር ዕቃዎቹ እጅግ ውብ ናቸው (ኤፌ.6፡11-17)። የንግግር ችሎታው ታላቅ እንደዚሁም ኃይልን lots የተሞላ ነው፡፡ ስለዚህ ከሥልጣኑ ከፍተኛነት፣ ከሰውነቱ ታላቅነት፣ ከኹሉም በላይ ደግሞ በእግዚአብሔር ባለው ተስፋ ንጉሡን በነጻነትና በማስተዋል ያናግሯል፡፡
ስለዚህ እንጸልይ፤ ልመናችንን እናቅርብ፤ እንማጸን፤ ወደ ሰማያዊው ንጉሥም ብዙ ዕንባን የተመላ መልእክተኛችንን እንላክ እንጂ ስለ ደኅንነታችን አንሥጋ! ይህን በጎ ምልጃ በምናደርግበት ጊዜ እንደ ወዳጅና ረዳት ኾኖ የሚደግፈንም ይህ ጾም አለልን፡፡
ክረምት አልፎ በጋ ሲመጣ ነጋዴው መርከቡን ወደ ባሕሩ ያስገባል፣ ወታደር የጦር መሣሪያውን ይሰነግላል የውጊያ ፈረሱንም ለጦርነቱ ያዘጋጃል! ገበሬው ማጭዱን ይስላል መንገደኛው በድፍረት ረጅም መንገድን ይጓዛል፤ አርበኛው (wrestler) ልብሱን አወላልቆ ለትግሉ ይዘጋጃል፡፡ እኛም ልክ እንደዚሁ ጾም ሲመጣ መንፈሳዊ በጋ እንደ ገባ በማሰብ እንደ ወታደሩ የጦር ዕቃ መሣሪያዎቻችንን እንሰንግላቸው፤ እንደ ገበሬው ማጭዳችንን እንሳል! እንደ ነጋዴዎቹ አሳቦቻችን ከልክ በላይ በኾኑ የፍላጎቶቻችን ሞገዶች ላይ እንዘዛቸው፤ እንደ መንገድ ተጓዦቹ ወደ መንግሥተ ሰማያት የምትወስደውን መንገድ እንጀምር፣ እንደ አርበኛውም ለተጋድሎው እንዘጋጅ፡፡ ክርስቲያን በአንድ ጊዜ ገበሬም፣ ነጋዴም፣ ወታደርም፣ አርበኛም ተጓዥም ነውና፡፡ እንዲህም ስለ ኾነ ቅዱስ ጳውሎስ እንዲህ አለ፡- "መጋደላችን ከሥጋና ከደም ጋር አይደለምና ከአለቆችና ከሥልጣናት ጋር ነው እንጂ፡፡ ስለዚህ የእግዚአብሔርዕቃ ጦር ኹሉ ልበሱ" (ኤፌ.6፡12)፡፡ አርበኛ ሰው አይተሃልን? ወታደርስ ተመለክተሃልን? እንኪያስ አንተም አርበኛ ከኾንክ ለትግሉ ተዘጋጅተህ ዕራቁትህን ልትኾን ያስፈልግሃል፡፡ ወታደር ከኾንክም ኹለንተናህን ታጥቀህ በውጊያው መስመር ላይ ልትሰለፍ ይገባ'ሃል፡፡ “እነዚህ ኹለቱ ነገሮችስ ማለትም ዕራቁት መኾንም ትጥቅ መልበስም በአንድ ጊዜ እንዴት ሊኾኑ ይችላሉ?" የሚል ጥያቄ በአእምሮህ ይመላለስ ይኾናል፤ ግድ የለም እኔ እነግርሃለሁ፡፡
ከዚህ ዓለም አሳብ ራስህን አውጣ፤ ያን ጊዜ አርበኛ ትኾናለህ፡፡ መንፈሳዊዉን የጦር ዕቃ ልበስ፤ ያን ጊዜም ወታደር ትኾናለህ፡፡ ወቅቱ አርበኛ ኾነህ የምትታገልበት ወቅት ነውና የዚህ ዓለም ፍላጎቶችህን አውልቀህ ጣል፡፡ ከአጋንንት ጋር የምናደርገው ጽነ ፍልሚያም አለንና መንፈሳዊ ትጥቅህን ልበስ፡፡ ስለዚህ ዲያብሎስ ከእኛ ጋር ትግል በሚገጥምበት ጊዜ የሚይዘውን እንዲያጣ ዕራቁት መኾን አስፈላጊ ነው፤ ድል የሚያደርግበትን ምት እንዳይመታንም በኹሉም አቅጣጫ በደንብ መታጠቅ ይኖርብናል፡፡
ሰውነትህን ኮትኩተው፡፡ እሾኾቹን መንጥራቸው፡፡ የመልካምነት ዘር ቃልም ዝራበት፡፡ እውነተኞቹን መንፈሳውያን ጥበባትን በታላቅ ጥንቃቄ ኾነህ አፍላቸው፤ ተንከባከባቸውም፤ ይህን ያደረግህ እንደኾነም እውነተኛ ገበሬ ትኾናለህ፡፡ ይህን ስታደርግም ተወዳጅ ጳውሎስ እንዲህ ይልሃል፡-“የሚደክመው ገበሬ ፍሬውን ከሚበሉት መጀመሪያ እንዲኾን ይገባዋል" (2ኛ ጢሞ.2፡6)፡፡ እርሱ ራሱ ይህን ዘዴ ይጠቀምበት ነበር፡፡ በመኾኑም ለቆሮንቶስ ክርስቲያኖች ሲጽፍላቸው እንዲህ አለ፡- “እኔ ተከልሁ፤ አጵሎስም አጠጣ፤ ነገር ግን እግዚአብሔር ያሳድግ ነበር" (1ኛ ቆሮ.3፡6)፡፡
በሆዳምነትህ የደነዘው ማጭድህን በጾም ሳለው፡፡ ወደ መንግሥተ ሰማያት የምትወስደውን መንገድ ተመልከታት፡፡ ውጣ ውረድ ያለባት፣ ጠባብና መከራ የበዛባት መኾኗን አስተውለህ በእርሷ ኺድ፡፡ እነዚህን ነገሮችስ እንዴት አድርገህ ልታደርጋቸው ትችላለህ? ሰውነትህን በመግዛትና [በጾም] በመቆንጠጥ! መንገዱ ጠባብ ስለኾነ ከሆዳምነቱ የተነሣ የወፈረ ሊያልፍባት አይቻለውምና፡፡
ገደብ የለሽ የፍላጎቶችህ ሞገዶችን ቀንሳቸው፡፡ የክፉ አሳቦች ፈተናን ከአንተ አርቅ፡፡ የንግድ መርከብህን ጠብቃት፤ ጥንቃቄ የተሞላበት ክኅሎትህን ተጠቀም፤ ያን ጊዜም የመርከብ አለቃ ትባላለህ፡፡ በእነዚህ ኹሉም ነገሮች ላይ ግን እንደ መሠረትና እንደ መሪ ጾምን ልንይዝ ግድ ይላል፡፡
ይቀጥላል...
(ትምህርት በእንተ ምክንያተ ሐውልታት፣ በቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ፣ ገጽ 79-96 ገብረ እግዚአብሔር ኪደ የተረጎመው)