፮
ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ስለ እውነተኛ ጾም፤ ስለ ሐሜት...በተናገረበት ድርሳኑ እንዲህ አለ፦
ተወዳጆች ሆይ! እንግዲያውስ እንሽሽ፤ ዋናው የሰይጣን ጕድጓድና ወጥመዶቹን ዘርግቶ አድብቶ የሚቀመጥበት ሥፍራ እንደ ኾነ በማወቅ ሐሜትን እንሽሽ! በራሳችን ጉዳይ ላይ ቸልተኞች እንድንኾንና ከዚህም የተነሣ የሚያገኘን ወቀሳ እጅግ ጽኑ እንዲኾን ሽቶ ዲያብሎስ ወደ እንደዚህ ዓይነት ልማድ ይመራናልና፡፡ ከዚህም በላይ ግን፥ ነገሩን እጅግ ከባድ የሚያደርገው ከዚህ በፊት በተናገርነው ነገር መልስ ስለምንሰጥበት ብቻ ሳይኾን በእነዚህ ነገሮች አማካኝነት ወቀሳችን እንዲከብድ በማድረጋችን ራሳችንን ከየትኛውም ዓይነት ይቅርታ ውጪ ስለምናደርገውም ጭምር ነው፡፡ የሌሎች ስዎች ጠባይ መራራነትን የሚመረምር ሰው እርሱ ራሱ ለፈጸማቸው ኃጢአቶች በፍጹም ይቅርታን አያገኝምና፡፡ ምክንያቱም እግዚአብሔር ፍርድን የሚፈርደው ከመተላለፎቻችን አንጻር ብቻ ሳይኾን አንተ በሌሎች ሰዎች ላይ ባስተላለፍከው ፍርድም ጭምር ተነሥቶ ነው፡፡
“እንዳይፈረድባችሁ አትፍረዱ" ብሎ ተግሣጹን የሰጠውም ለዚህ ነው (ማቴ.7፥1)፡፡ [የዚያን ጊዜ ላይ] የበደልከው ማንኛውም ዓይነት በደል ብቻዉን ሳይኾን በዚሁ [በደልህ ላይ] በባልንጀሮችህ ላይ የፈረድከው ፍርድም ተጨምሮበት ታላቅና ይቅር የማይባል ኾኖ ይገለጣልና፡፡ ርኅሩኅ፣ ቸርና ይቅር ባይ ሰው እርሱ የኃጢአቶቹን ክምር ቆርጦ ይጥላቸዋልና፡፡
መራራ፣ ጨካኝና በጥላቻ የተሞላ ሰው ደግሞ በደሎቹን በላይ በላይ እየጨመረ ያበዛቸዋልና፡፡ እንግዲያውስ ከእርሱ ካልራቅን በቀር ምግባችን ዐመድ ቢኾንም እንኳን ይህ ምንም እንደማይጠቅመን በማወቅ ሐሜትን ኹሉ ከአንደበታችን እናርቅ፡፡ “ወደ አፍ የሚገባ ኹሉ ወደ ሆድ አልፎ ወደ እዳሪ እንዲጣል አትመለከቱምን? ከአፍ የሚወጣ ግን ከልብ ይወጣል፤ ሰውንም የሚያረክሰው ያ ነው" (ማቴ.15፥17-18)፡፡ በመንገድ እያለፍህ ሳለ አንድ ሰው የሰውን ሰገራ ሲቆሰቁስ ብትመለከተው ይህን በማድረጉ አትገሥጸውምን? በሐሜተኞች ላይም እንደዚህ አድርግ፡፡ በእጅ የተቆሰቆሰው የሰው ሰገራ በሐሜት የሌሎች ሰዎችን ኃጢአት የመቆስቆስና ንጹህ ያልኾነ ሕይወታቸውን የማጋለጥ ያህል ሽታ የለውምና፤ ውስጥንም ኾነ ነፍስን አይጎዳምና፡፡ ስለዚህ ራሳችንን ከሐሜትና ከአሉባልታ ከነቀፋም እናርቅ፤ ባልንጀራችንም ኾነ እግዚአብሔርን አንማ!
ምክንያቱም ብዙ ሐሜተኞቻችን ወደ እንደዚህ ዓይነት ዕብደት እየተንደረደሩ ነው፤ ምላሳቸውን ከባልንጀሮቻቸው አልፈው በአምላካቸው ላይእያላቀቁ ነው፡፡ ይህ ምን ያህል ታላቅ ክፋት እንደ ኾነም አሁን ካጋጠመን ነገር መረዳት ትችላላችሁ፡፡
ሰው [ንጉሡ] ተሰድቧል፤ እነሆ በዚህ ወንጀል የተባበሩትም ኾኑ በዚህ ግብር ላይ ምንም እጃቸው እንደሌለ የሚያውቁትም እየፈራን እየተንቀጠቀጥንም ነው! እግዚአብሔር ግን ዕለት ዕለት ይሰደባል! ምን ዕለት ዕለት ብቻ በየሰዓቱ በባለጸጋውም በድኻውም፣ መከራ ባልደረሰባቸውም በደረሰባቸውም፣ በሐሜተኞችም ሐሜተኛ ባልኾኑ ሰዎችም ይሰደባል፡፡ ነገር ግን [አሁን] እንደዚህ ያለ [የሚያስፈራና የሚያርድ የሚያንቀጠቅጥ] ቃልን የሚሰማ ማንም የለም! በመኾኑም እንደ እኛ አገልጋይ የኾነ ሰው [ንጉሡ] ይሰደብ ዘንድ ፈቃዱ ኾነ፤ ይኸውም ይህ ስድብ በመድረሱ ምክንያት እንደ ምን ያለ መከራን እንዳመጣና በአንጻሩም የእግዚአብሔር ርኅራኄ እንደ ምን የበዛ እንደ ኾነ እንድናውቅ ነው፡፡ ምንም እንኳን ይህ የመጀመሪያችንና ብቸኛው ዓመጻችን ቢኾንም ይህ ስለ ኾነ ተብሎ የሚደረግልን ይቅርታም ኾነ ምሕረት ግን የለም፡፡ እግዚአብሔርን ግን በየቀኑ እናስቈጣዋለን! ይህን አድርገን ስናበቃ እንኳን ወደ እርሱ የመመለስ አዝማሚያ አናሳይም፤ ነገር ግን እርሱ ከታላቅ ትዕግሥቱ የተነሣ አሁንም ዝም ብሎናል! እንግዲህ የእግዚአብሔር ቸርነት እንደ ምን ታላቅ እንደ ኾነ ታያለህን? በአሁኑ ዓመጽ ላይ ተሳታፊ የነበሩ ስዎች ተወስደዋል፤ ወደ ወኅኒ ተጨምረዋል፤ ቅጣትም ተላልፎባቸዋል፡፡ እኛ ግን አሁንም ፍርሐት ላይ አለን፡፡ የተሰደበው ሰው እስከ አሁን ድረስ ምን እንደ ተደረገ ገና አልሰማምናº ውሳኔም አላስተላለፈምና እስከ አሁን ድረስ በረዓድ ተይዘናል፡፡ እግዚአብሔር ግን ይህን ስድብ በየቀኑ ይሰማል፤ ይህንን ግን ማንም ልብ አይለውም፤ እግዚአብሔር ቸርና ስውን ወዳጅ ነውና፡፡ በእርሱ ዘንድ ኃጢአትን መናዘዝ ብቻ በቂ ነው፤ ይህን ካደረጉም ያደረጉት ኃጢአት ኹሉ ይሰረዛልና፡፡ በሰው ዘንድ ግን ሙሉ ለሙሉ የዚህ ግልባጭ ነው፡፡ እነዚያ የበደሉ ሰዎች በደላቸውን ሲናዘዙ ቅጣታቸው ይበልጥ ይበረታል፤ ይኸውም ልክ አሁን እንደ ኾነው ማለት ነው፡፡
ዳግመኛም አንዳንዶቹ በስይፍ ጠፍተዋል፤ አንዳንዶቹ በእሳት ተቃጥለዋል፤ ለበረኻ አውሬዎች የተስጡም አሉ፡፡ ዐዋቂ ስዎች ብቻ አይደሉም፤ ሕፃናትም ጭምር እንጂ፡፡ ይህ የዕድሜአቸው ጨቅላነት፤ የሕዝቡ ጩኸት፣ እነዚህን ግብራት ሲፈጽሙ አጋንንት ያደሩባቸው መኾናቸው፣ ሊከፈል ያለው ግብር እንደማይቻል አድርገው ማሰባቸው፣ ድኽነታቸው ወይም ኹሉም ስው ስላመጸ እነርሱም አብረው ማመጻቸው፣ ከእንግዲህ ወዲህ እንደዚህ ያለ ተግባርን ደግመው እንደማይፈጽመ ቃል መግባታቸው ወይም ሌላ ይህን የመሰለ ምክንያት በፍጹም ሊያድናቸው አልቻለም፡፡ ከዚህ ይልቅ ያለ ምንም ጊዜያዊ እፎይታ ማንም እንዳያመልጥ ኾነው በታጠቁ ኃይሎች ተከብበው እየተመሩና እየተጠበቁ ተወስደው፣ ፍርሐት ኀዘናቸውን አስረስቶአቸዋልና ረዓድም ወርሮአቸዋልና እናቶቻቸው ከኋላ ኾነው ቢከተሉአቸውም ዳግመኛም ልጆቻቸው አንገታቸው እየተቈረጠ ሳለ እያዩ ኀዘናቸውን ለመግለጽ ሳያለቅሱ ወደ ጉድጓድ ተጣሉ እንጂ! እነዚህ ወንጀለኞች በሚቀጡበት ሥፍራ የነበሩ ሰዎችም በጥልቅ ኀዘን ተይዘው ነበር፤ ነገር ግን መቅረብና ከስጥመት ሊያድኑአቸው አልተቻላቸውም፡፡ ሌሎች ስዎች ብቻ ሳይኾኑ የገዛ እናቶቻቸው እንኳን ወታደሮቹን ከመፍራታቸው የተነሣ መቅረብ አልተቻላቸውም፡፡ መቅረብና ልጆቻቸውን ማዳንስ ይቅርና እንባቸውን እንኳን ማፍሰስ ይፈሩ ነበር!
ይቀጥላል....
(ትምህርት በእንተ ምክንያተ ሐውልታት፣ በቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ፣ ገጽ 79-96 በገብረ እግዚአብሔር ኪደ የተተረጎመ)