🌷ነገረ ክርስቶስ 🌷ምዕራፍ ፭ 🌷ክፍል ፩
ሃይማኖት
ስለ ነገረ ክርስቶስ ለመነጋገር መሠረታችን የፈጣሪ መኖር ነው። በፈጣሪ ህልውና ዙሪያ ብዙ አስተያየቶች አሉ። ጠቅለል ስናደርጋቸው ግን ሦስት ናቸው። እነዚህም:-
1) ፈጣሪ የሚባል የለም
2) ፈጣሪ ሊኖርም ላይኖርም ይችላል
3) ፈጣሪ አለ
የሚሉት ናቸው። ቁጥር 1 እና 2 ላይ የተጠቀሰውን የሚደግፉ የራሳቸውን አመለካከት ለመደገፍ የሚያቀርቡት የየራሳቸው አመክንዮ አላቸው። የአመክንዮአቸው ጥንካሬ ግን ደካማ ሆኖ ይገኛል። Full of fallacy ሆኖ ይገኛል። አንዳንዶች ለድምዳሜያቸው መነሻ ያደረጉት ሐሳብ (premise) የተሳሳተ ስለሆነ ወደ ተሳሳተ ድምዳሜ (Conclusion) አድርሷቸዋል። አንዳንዶች ደግሞ መነሻ ሐሳቦቻቸው ትክክል ቢሆኑም የተሳሳተ ቅደም ተከተልን (Wrong arrangement) መሠረት አድርገው ከተሳሳተ ድምዳሜ ይደርሳሉ። በእርግጥ የትክክለኝነት መለኪያው ምንድን ነው? የሚለውም ለብቻው በስፋት የሚታይ ነው።
አንድን ነገር አለ ወይም የለም ለማለት የሚያበቃን አእምሯችን ነው። አእምሮ ደግሞ ዕውቀትን በተፈጥሮ ካገኘው በተጨማሪ በስሜት ሕዋሳት አማካኝነት ከተፈጥሮ ጋር ባለው ግንኙነት የሚያውቃቸው ዕውቀቶች አሉት። እነዚህ ዕውቀቶች ግን አንድን ነገር በትክክል ይገልጻሉ ወይንስ አይገልጹም? የስሜት ሕዋሳቶቻችን ለአእምሯችን የሚያስተላልፉት መልእክትስ ትክክለኛነቱ በምን ይረጋገጣል? ለምሳሌ አንድ ቀጥ ያለን ዱላ በውኃ ውስጥ ስንመለከተው ጠመም ያለ ይመስላል። በዓይናችን አማካኝነት አእምሯችን የተረዳው ነገር ቢኖር ጠመም ያለ እንደሆነ ነው። ከውሃ ወጥቶ ሲያዩት ደግሞ ቀጥ ያለ ነገር እንደሆነ ይረዳል። ታዲያ ስለዱላው ትክክለኛው ነገር ምንድን ነው? አንዳንዱ ዱላው ቀጥ ያለ ነው ጠመም ያለ የመሰለን በውኃው ምክንያት ነው የሚል ሊኖር ይችላል። ነገር ግን ከውኃው ሲወጣም ከሌሎች ተጽእኖ ምሳሌ አየር፣ ሙቀትና ከመሳሰሉት ነጻ ስላልወጣ ቀጥ ያለ ነው ለማለት ከእነዚህ ነገሮች ነጻ የወጣ መሆን አለበት። ይህን ሁሉ የምንለው አእምሮ ራሱ አንድን ነገር ለመበየንና የበየነው ነገር ቋሚ ትክክል (Always true) የሆነ ነገር ሳይሆን እንደሚገኝ በጥቂቱ ለማመልከት ነው።
አእምሮ ከስሜት ሕዋሳት መረዳት በላይ የሆኑ ጉዳዮችን እንደሌሉ ሊበይን ይችላል። scientifically ጆሮ የሌላቸው ሌሎች የስሜት ሕዋሳቶች ግን ምሳሌ ዓይን አፍንጫና የመሳሰሉት ያላቸው ፍጥረታት እንዳሉ ይነገራል። ጆሮ ለሌለው ፍጥረት ዓለም በጩኸት ቢደበላለቅ የድምፅ ህልውና ለእርሱ ውሸት ሊመስለው ይችላል። በእርግጥ እግዚአብሔርም ባሉን የስሜት ሕዋሳቶቻችን ሁሉ የማይረዳ ከስሜት ሕዋሳቶቻችን ሁሉ በላይ ነው። ሊቅ ባስልዮስ "ለእመ ተጋብኡ ኅቡረ መላእክት ወሊቃነ መላእክት በበዘመዶሙ ዘምስለ ኵሎሙ ፍጡራን አሐተኔ ኢይክሉ ይርከቡ ኅዳጠ እምአእምሮተ ህላዌሁ ለእግዚአብሔር" እንዳለ በሃይማኖተ አበው እንኳንስ እኛ ቅዱሳን መላእክት ሁሉ በአንድነት ሆነው ቢመረምሩት ባሕርይው ከመመርመር በላይ ነው። በስሜት ሕዋሳት ካልተረዳነው የሚባል አይደለም። ፈጣሪ የለም የሚሉ አካላት ፈጣሪን ምን ዓይነት አድርገው ፈልገው አጡት??? እግዚአብሔርን የለም ለማለት በማንነቱ ፈልጎ ማጣት አይቀድምም ወይ? ረቂቅ ነኝ እያለ ግዙፍ ነገር ፈልገው ካጡት መጀመሪያውንም የፈለጉት እግዚአብሔርን ሳይሆን በኅሊናቸው ራሳቸው የፈጠሩትን ፈጣሪ ነው። አልታይም፣ አልዳሰስም እያለ የሚታይ የሚዳሰስ ነገር ፈልገው ካጡ ችግሩ የራሳቸው ነው። ፈጣሪ ሊኖርም ላይኖርም ይችላል የሚሉት አካላት ደግሞ አለ እንዳንል በየትኛውም የስሜት ሕዋሳቶቻችን አልተረዳነውም። የለምም እንዳንል የስሜት ሕዋሳቶቻች ወሰን አለባቸው የሚሉ ማዕከላውያን ናቸው። በዚህ ዙሪያ በተለይም በTheoretical Philosophy ክፍሎች ማለትም በMetaphysics እና በGnosiology የሚነሱ የተለያዩ ሀሳቦች አሉ። ሁሉንም ሐሳቦች ግን በተሰጠን አእምሮ ስንመረምራቸው እዚህ ግባ የሚባል አሳማኝ ነገር የላቸውም። በእርግጥ ሳይመረምር ሳያላምጥ የሚውጥን ሰው በቀላሉ ሊማርኩት ይችላሉ። የኦሾ ተራ ፍልስፍና የሚያንበረክከው ትውልድ እነዚህ በጣም ሊከብዱት ይችላሉ። እያንዳንዳቸውን እየሞገትን እስከ ፍጻሜው ለማየት እንሞክራለን።
እኛስ እግዚአብሔር አለ የምንለው ምንን መሠረት አድርገን ነው? የሚለውን ማወቅ ግን ከሁላችንም ይጠበቃል። ፈጣሪ አለ ያልነው በስሜት ሕዋሳቶቻችን መርምረን ደርሰንበት አይደለም። ከስሜት ሕዋሳት በላይ ነውና። ነገር ግን ለስሜት ሕዋሳቶቻችን ቅርብ በሆነ መንገድ በዘፈቀደ በዘንክል (እርሱ በወደደው እኛ ልናየው በምንችለው መጠን) በተለያየ አምሳል ተገልጾ አምላካዊ ሥራዎችን ሠርቶ በማሳየት ተገልጦልናል። ይህ ብቻ አይደለም ሰው ሆኖ አምላካዊ ሥራዎችን እየሠራ ዓለም አየው። እነዚህን ማስረጃዎች ይዘን የፈጣሪን መኖር እናምናለን። ሰው ሆኖ ክርስቶስ የተባለው ዓለምን ቀድሞ የፈጠረው ነው። ለዛሬ ይችን ብቻ ገልጨ ልለፍ። ይህ ነገረ ክርስቶስ ምዕራፍ ፭ በዋናነት በፍልስፍና መነሻነት ክርስቶስን ለሚክዱ ምላሽ የሚሰጥ ነው። በውስጡም 120 ክፍሎች ይኖሩታል። ከዚያ ምዕራፍ ፮ ብሉይ ኪዳንን መሠረት አድርገን 300 ክፍሎችን እናያለን። ምዕራፍ ፯ መጻሕፍተ ሊቃውንትንና መጻሕፍተ መነኮሳትን መሠረት አድርገን ከተማማርን በኋላ ወደ ሌላ የትምህርት ርእሰ ጉዳይ እንገባለን። ምዕራፍ ፩ ሐዲስ ኪዳንን መሠረት አድርገን 343 ክፍሎችን ተማምረናል። እርሱን በPDF በቴሌግራም ቻናሌ ታገኙታላችሁ። በዓመት ውስጥ ለመጨረስ እንዲያመቸን በቀን ብዙ ክፍሎችን ልለቅ እችላለሁ።
በነገራችን ላይ የክርስትና ትምህርት ፍልስፍናን የሚያንበረክክ እንጂ ከፍልስፍና ያነሰ አይደለም። በአመክንዮ ለሚያጣጥሉን ሰዎች ከእነርሱ አመክንዮ በላይ የሆነ አመክንዮ አለን። ይህ ብቻ አይደለም ከእነርሱ በተሻለ አመክንዮ ለማይመልሳቸው ጥያቄዎች በቂ ምላሽ የሚሰጥ እምነትም አለን። አእምሮ ሊመረምረው የማይቻለውን ጉዳይ በእምነት እንመረምረዋለን። ከኅሊና በላይ ያሉ ጉዳዮችን በሃይማኖተ ሰሚእ ጸንተን በሃይማኖተ ርእይ እናረጋግጣለን። ነገረ ሃይማኖትን ከአመክንዮ ባሻገር በእምነት የበለጠ እያወቅነው እንሄዳለን። ሊቁ ቅዱስ ያሬድ በድጓው "ወአንተሰ ለእመ ትፈቅድ ታእምር ኅድግ ኅሊና ዘበምድር ወዕድዎሙ ለከዋክብት። እምዝንቱ ኵሉ ተልዒለከ በልቡናከ ሐሊ አሐደ ሥሉስ ዘኢይሴደቅ" ብሎ እንደተናገረው ከምድራዊ ሐሳብ ወጥተን ከከዋክብት በላይ ማሰብን (ሰማያዊ ሐሳብን) ይጠይቃል። ይህንን በደንብ እንመለከታለን።
© በትረማርያም አበባው
ምዕራፍ ፭ ክፍል ፪ ይቀጥላል
🌹የዩቲዩብ ቻናሌ:- ንሕነ ዘክርስቶስ @edenawizechristos?si=6V4y-73OM3LTzhAf' rel='nofollow'>https://youtube.com/@edenawizechristos?si=6V4y-73OM3LTzhAf ነው።