💙💙 የጥያቄዎች መልስ ክፍል 140 💙💙
▶️፩. መዝ.77፥25 ላይ "የመላእክትንም እንጀራ የሰው ልጆች በሉ" ሲል ምንን ለማመልከት ነው?
✔️መልስ፦ የመላእክት እንጀራ የሚባለው ምስጋና ነው። መላእክት ረቂቃን በመሆናቸው ሥጋዊ ምግብ አያስፈልጋቸውም። ምግባቸው ምስጋናቸው ነውና። ስለዚህ የመላእክትን እንጀራ የሰው ልጆች በሉ ማለት ሰዎች የመላእክትን ምስጋና አመሰገኑ ማለት ነው።
▶️፪. መዝ.73፥14 ላይ "አንተም የዘንዶውን ራሶች ቀጠቀጥህ። ለኢትዮጵያ ሰዎች ምግባቸውን ሰጠሃቸው" ይላል። ምን ማለት ነው?
✔️መልስ፦ የዘንዶውን ራስ ቀጠቀጥህ የተባለ ብሔሞት ነው። ብሔሞት ዓለም ላይ ካሉ ፍጥረታት እጅግ በጣም ግዙፉ ደማዊ ፍጥረት ነው። እና ብሔሞት የሚኖረው በናጌብና በአድማስ መካከል ተወስኖ ነው። ስለዚህ የዘንዶውን ራስ ቀጠቀጥክ ማለት ዘንዶ ራሱ ከተቀጠቀጠ እንደማይንቀሳቀስ ሁሉ ብሔሞትንም ከናጌብና ከአድማስ መካከል ውጭ እንዳይንቀሳቀስ አደረግኸው ማለት ነው። ለኢትዮጵያ ሰዎች ምግባቸውን ሰጠኻቸው ማለት እግዚአብሔር መጋቢ እንደመሆኑ ሰዎችን መገብካቸው ማለቱ ነው። ይኸውም በኢትዮጵያ የዓለሙን ሁሉ መናገር ነው።
▶️፫. መዝ.77፥65 ላይ "እግዚአብሔርም ከእንቅልፍ እንደሚነቃ ተነሣ። የወይን ስካር እንደ ተወው እንደ ኀያልም ሰው" ይላል። ይህ ክፍለ ንባብ ስለ ጌታችን አምላካችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ትንሣኤ እንደሆነ ይተረጎማል። ታዲያ "የወይን ስካር እንደተወው እንደ ኅያልም ሰው" ሲል ምን ማለቱ ነው?
✔️መልስ፦ የወይን ስካር ያለፈለት ኃያል ሰው ፈጥኖ እንደሚነሣ ሁሉ በወይን ስካር በተመሰለ ሞት የሞተ ክርስቶስ ፈጥኖ ከሙታን ተነሣ ማለት ነው። የወይን ስካር ያጋጠመው ኃያል ያንቀላፋል እንጂ አይሞትም። ክርስቶስንም በሥጋው ሞተ ብንለው በመለኮቱ ሕያው ነው እንለዋለንና በዚህ አንጻር የተነገረ ነው። ሐዋርያው ቅዱስ ጴጥሮስ ሞተ በሥጋ ወሐይወ በመንፈስ እንዳለ።
▶️፬. መዝ.71፥9 ላይ "በፊቱም ኢትዮጵያ ይሰግዳሉ። ጠላቶቹም ዐፈር ይልሳሉ" ይላል። ሐሳቡ ምን ለማለት ነው?
✔️መልስ፦ ይህ መዝሙር ስለሰሎሞን የተነገረ ነው። በፊቱ ኢትዮጵያ ይሰግዳሉ ማለትም የኢትዮጵያ ሰዎች እነ ማክዳ ለሰሎሞን እጅ መንሻ ይዘው ይቀርባሉ ማለት ነው። ጠላቶቹም አመድ ይመገባሉ ማለት የሰሎሞን ጠላቶች ይዋረዳሉ ማለት ነው።
▶️፭. "ከግብጽ የወይን ግንድ አመጣህ። አሕዛብን አባረርህ እርሷንም ተከልህ" ይላል (መዝ.79፥8)። የወይን ግንድ የተባለው ማን ነው?
✔️መልስ፦ ከዚህ የወይን ግንድ የተባሉ እስራኤላውያን ናቸው። ሙሉ ትርጉሙም እስራኤላውያንን ከግብጽ ባርነት ነጻ አውጥተህ ወደ ከነዓን አመጣሀቸው ማለት ነው።
▶️፮. "ሥጋን እንደ ዐፈር፣ የሚበሩትንም ወፎች እንደ ባሕር አሸዋ አዘነበላቸው" ይላል (መዝ.77፥27)። የሚበሩት ወፎች የተባሉ ምንድን ናቸው?
✔️መልስ፦ የሚበሩት ወፎች የተባሉት የሚበሉ የአዕዋፍ ዝርያዎችን ቆቅን፣ ዥግራን የመሳሰሉትን እግዚአብሔር ለእስራኤላውያን አብዝቶ አዘነመላቸው ማለት ነው።
▶️፯. "አንተ በዘለዓለም ተራራዎች ሆነህ በድንቅ ታበራለህ" ይላል (መዝ.75፥4)። ተራራዎች የተባሉት እነማን ናቸው?
✔️መልስ፦ የዘለዓለም ተራራዎች የተባሉ ቅዱሳን አበው ናቸው። በቅዱሳን አበው አድረህ እግዚአብሔር ሆይ በተአምራት ረድኤትህን ትሰጣለህ ማለት ነው።
▶️፰. "ተራራዎችና ኰረብታዎች ለሕዝብህ ሰላምን ይቀበሉ" ይላል (መዝ.71፥3)። ተራራዎችና ኮረብታዎች የተባሉት መልክአ ምድሩን ነው ወይስ ሌላ ምሥጢር አለው?
✔️መልስ፦ ከዚህ ላይ ተራራ ኮረብታ እያለ የተናገረው ስለመሬት መልክአ ምድር አይደለም። በተራራ የተመሰሉ ነገሥታት ሲሆኑ በኮረብታ የተመሰሉት ደግሞ መኳንንት ናቸው።
▶️፱. መዝ.77፥54 ላይ "ወደ መቅደሱ ተራራ ወሰዳቸው። ቀኙ ወደ ፈጠረችው ተራራ" ይላል። ቀኙ ወደ ፈጠረችው ሲል ምን ለማለት ነው?
✔️መልስ፦ ለእግዚአብሔር ቀኝ ሲነገር ሥልጣን ተብሎ ይተረጎማል። ስለዚህ በሥልጣኑ ወደ ፈጠረው ተራራ ማለት ነው።
▶️፲. መዝ.71፥5 ላይ "ፀሐይ በሚኖርበት ዘመን ሁሉ በጨረቃም ፊት ለልጅ ይኑር" ሲል ምን ማለት ነው?
✔️መልስ፦ ይህ ስለሰሎሞን ንግሥና የተነገረ ምረቃ ነው። ብዙ ዘመን ያኑርህ ለማለት ፀሐይ ሳታልፍ ወይም ጨረቃ ሳታልፍ አትለፍ ብሎታል። ንጉሥ ሆይ ሺ ዓመት ያንግሥህ እንደሚለው ነው።
▶️፲፩. "በፊቱም ኢትዮጵያ ይሰግዳሉ ጠላቶቹም ዐፈር ይልሳሉ" ይላል (መዝ.71፥9)። ኢትዮጵያ ተብላ የተጠራችው የአሁኗን ግዛት ብቻ የሚያጠቃልል ነው ወይስ ሌሎችም ካሉ ቢነግሩን።
✔️መልስ፦ በዚያ ዘመን የኢትዮጵያ ግዛት ከምን እስከምን እንደነበረ መጽሐፍ ቅዱሱ ወሰኑን አላስቀመጠልንም። ስለዚህ አለማወቅ ይገድበናል። በታሪክ ግን የኢትዮጵያ ግዛት ሰፊ እንደነበር ይነገራል።
▶️፲፪. "ዐይናቸው ስብ ስለ ሆነ ወጣ። ልባቸውም ከምኞታቸው ይልቅ አገኘ" ይላል (መዝ.72፥7)። ምን ማለት ነው?
✔️መልስ፦ ከዐይን ጉድፍ እንደሚወጣ ሁሉ ክፉ ሐሳብን ከልቡናቸው አወጡ ማለት ነው። ልባቸውም ከምኞታቸው ይልቅ አገኘ ማለት ከትዕቢት ወደ ትዕቢት ተሽጋገሩ ማለት ነው።
▶️፲፫. "ጽዋ በእግዚአብሔር እጅ ነውና ያልተቀላቀለ የወይን ጠጅ ሞላበት ከዚህ ወደዚያ አገላበጠው ነገር ግን አተላው አልፈሰሰም የምድር ኀጢአተኛዎች ሁሉ ይጠጡታል" ይላል (መዝ.74፥8)። ትርጉሙ ይብራራልን።
✔️መልስ፦ ጽዋዕ በእግዚአብሔር እጅ ነው ማለት በእግዚአብሔር እጅ መዓት አለ ማለት ነው። ያልተቀላቀለ የወይን ጠጅ ሞላበት ማለት ምሕረት የሌለው መዓትን አመጣ ማለት ነው። አተላው አልፈሰሰም ማለት ሁሉም መከራውን ተቀበሉ ከመከራው ያመለጠ የለም ማለት ነው። ይህ ስለእነ ሰናክሬም የተነገረ ነው።
▶️፲፬. "ስፍራው በሳሌም ማደሪያውም በጽዮን ነው" ይላል (መዝ.75፥2)። ይብራራልን።
✔️መልስ፦ ሳሌም ማለት ሰላም ፍቅር ማለት ነው። ስለዚህ ስፍራው በሳሌም ነው ማለት ሀገሪቱ በሰላም በፍቅር ኖረች ማለት ነው። ማደሪያውም በጽዮን ነው ማለት እግዚአብሔር ረድኤቱን በኢየሩሳሌም አደረገ ማለት ነው።
▶️፲፭. "ዝንቦችንም በላያቸው ሰደደባቸው በሏቸውም በጓጕንቸርም አጠፋቸው" ይላል (መዝ.77፥45)። ጓጒንቸር የሚባለው ምንድን ነው?
✔️መልስ፦ ጓጉንቸር የሚባለው እንቁራሪት ወይም ጉርጥ በመባል የሚታወቀው ነው። በውሃ ውስጥም በየብስም መኖር የሚችል ፍጥረት ነው።
▶️፲፮. "ፍሬያቸውን ለኵብኵባ ሥራቸውንም ለአንበጣ ሰጠ" ይላል (መዝ.77፥46)። ኲብኲባና አንበጣ ልዩነቱ ምንድን ነው?
✔️መልስ፦ ኩብኩባ የሚባለው ትንሹ ሲሆን አንበጣ የሚባለው ደግሞ ትልቁ ነው። ፌንጣ የመሰለ እህልን የሚያወድም ክንፋማ ፍጥረት ነው። የአንበጣ ትንሹ ኩብኩባ ይባላል።
▶️፲፯. "ወይናቸውን በበረዶ በለሳቸውንም በዐመዳይ አጠፋ" ይላል (መዝ.77፥47)። ዐመዳይ የሚባለው ምንድን ነው?
✔️መልስ፦ አመዳይ አመድ የመሰለ ከደመና የሚወርድ በረዷማ ነገር ነው።
▶️፲፰. "ቀንዳችሁን እስከ አርያም አታንሡ" ሲል ምን ማለቱ ነው (መዝ.74፥5)?
✔️መልስ፦ በሥልጣናችሁ በአርያም ያለ እግዚአብሔርን አታሳዝኑ ማለት ነው።
▶️፲፱. መዝ.77፥49 "መዓትህን መከራንም በክፉዎች መላእክት ሰደደ" ይላል። በክፉዎች መላእክት ሲል ምን ለማለት ነው?