💙 የጥያቄዎች መልስ ክፍል 152 💙
▶️፩. ምሳ.21፥14 ላይ "የብብትም ውስጥ ጉቦ ጽኑ ቁጣን ታበርዳለች" ይላል። ጉቦ የሚላት ምጽዋትን ነው ወይስ ሙስና? ሙስና ከሆነ እንዴት ቁጣን ታበርዳለች?
✔️መልስ፦ የአማርኛ መተርጉማን ጉቦ ብለው መተርጎም አልነበረባቸውም። ግእዙንም እንግሊዘኛውንም ሳየው እንደዚያ አይልም። ግእዙ የሚለው "ሀብት ዘበጽሚት ይገፍዕ መዓተ። ወዘሰ ይምሀክ ሀብተ ያነሥእ ጽኑዐ መዓተ" ነው። ግእዙ "ሀብት" የሚለው "ወሀበ" ሰጠ ከሚለው የግእዝ ቃል የሚወጣ ምዕላድ ነው። ትርጉሙ ስጦታ ማለት ነው። ስጦታ ደግሞ የፍቅር ምልክት ነው። ሰው ስጦታ ሲሰጥ ፍቅሩን እየገለጸ ስለሆነ የሌላውን ቁጣ ያርቃል ማለት ነው። እንጂ ከጉቦ ጋር አይገናኝም። እንግሊዘኛውም "A gift in secret pacifieth anger: and a reward in the bosom strong wrath" ነው የሚል (King James Version)። በዚህ አገባብ Gift (ስጦታ) ተብሎና Reward (ሽልማት) ተብሎ ተገልጿል። ሁለቱም ከጉቦ ጋር አይገናኙም።
▶️፪. ምሳ.21፥4 ላይ "ትዕቢተኛ ዓይንና ደፋር ልብ የኃጥኣንም እርሻ ኃጢአት ነው" ይላል። ትዕቢተኛ ዐይን ምትባለው ግን ምን ዓይነት ናት?
✔️መልስ፦ ትዕቢተኛ ዓይን የሚባለው ከፍ ዝቅ አድርጎ በንቀት የሚያይና ገላማጭ ዓይን ነው።
▶️፫. ምሳ.፳፬፥፷-፷፪ ላይ "በሦስት ነገር ምድር ትናወጣለች። አራተኛውንም ልትሸከመው አትችልም። ባሪያ በነገሠ ጊዜ፣ ሰነፍም እንጀራን በጠገበ ጊዜ፣ የተጣለች ሴት ቸር ባል ባገኘች ጊዜ፣ ሴት ባሪያም እመቤቷን በወረሰች ጊዜ" ሲል ምን ማለት ነው?
✔️መልስ፦ ክፉ ባሪያ በነገሠ ጊዜ፣ ሰነፍ ሰው እንጀራን በጠገበ ጊዜ፣ የተጣለች ክፉ ሴት ቸር ባል ባገኘች ጊዜ፣ ክፉ ሴት ባሪያ እመቤቷን በወረሰች ጊዜ የሚለው ሁሉም የነበሩበትን ዘንግተው ትዕቢተኛ እንደሚሆኑና ብዙ ጥፋትን እንደሚያጠፉ ለማመልከት ነው።
▶️፬. ምሳ.፳፫፥፳፫ ላይ "እውነትን ግዛ አትሽጣትም። ጥበብንና ተግሣጽን ማስተዋልንም" ሲል እውነት ሊገዛ ይችላል ወይ?
✔️መልስ፦ እውነትን ግዛ ማለት እውነትን ገንዘብ አድርግ ማለት ነው። የገዙት ነገር ገንዘብ እንደሚሆን ሁሉ አንተም እውነትን ገንዘብ አድርግ ማለት ነው። እውነትን አትሽጣት ማለት የተሸጠ ነገር ባለቤትነቱ ለሌላ እንደሚሆን እውነትን አትተዋት ማለት ነው።
▶️፭. ምሳ.፳፩፥፲፮ ላይ "ከጽድቅ መንገድ የሚሰስት ሰው በረዐይት ጉባኤ ያርፋል" ሲል የረዐይት ጉባኤ ምን ማለት ነው?
✔️መልስ፦ ረዐይት የሚባሉት ከደቂቀ ሴትና ከደቂቀ ቃኤል ተዳቅለው የተወለዱና ክፉዎች በመሆናቸው በማየ አይኅ የጠፉ ሰዎች ናቸው። የሚሰስት ሰው በረዐይት ጉባኤ ያርፋል ማለት ረዐይት እንደጠፉ እርሱም ይጠፋል ማለት ነው።
▶️፮. ምሳ.፳፩፥፯-፰ ላይ "የኃጥኣን ጥፋት ከሩቅ ይመጣል። እግዚአብሔር ለጠማሞች ጠማማ ሥራ ይልክባቸዋል" ሲል ምን ለማለት ነው?
✔️መልስ፦ የኃጥኣን ጥፋት ከሩቅ ይመጣል ማለት በበደላቸው ምክንያት ደርሶባቸው የማያውቅ መከራ ይደርስባቸዋል ማለት ነው። እግዚአብሔር ለጠማሞች ጠማማ ሥራ ይልክባቸዋል ማለት መከራን ያመጣባቸዋል ማለት ነው። ጠማማነቱ ለእነርሱ ነው እንጂ ለእግዚአብሔርማ በእነርሱ ላይ ያመጣው ርቱዕ ፍርዱ ነው።
▶️፯. ምሳ.፳፪፥፯ ላይ "ድኾች ባለጠጎችን ይገዛሉ። አገልጋዮችም ለጌቶቻቸው ያበድራሉ" ሲል ምን ለማለት ነው?
✔️መልስ፦ ብልህ ድኾች ሰነፍ ባለጠጎችን ይገዛሉ። ለምሳሌ ዮሴፍ ፈርዖንን በአስተዳደሩ ገዝቶታል። ማለት በዮሴፍ የአስተዳደር ጥበብ ፈርዖን ተመርቷል። አገልጋዮችም ለጌቶቻቸው ያበድራሉ ያለው ይህንኑ ነው። ዮሴፍ ለፈርዖን በአስተዳደሩ ማበደሩን ያመለክታል።
▶️፰. ምሳ. ፳፪፥፳ ላይ "ለዕውቀትና ለምክር ይኾኑኽ ዘንድ ሦስት ነገሮችን እነኾ ጻፍኹልኽ። አንተም በልብኽ ሰሌዳነት ጻፋቸው" ሲል ሦስቱ ነገሮች እነማን ናቸው?
✔️መልስ፦ ሦስቱ ነገሮች የተባሉት ከዚሁ ቀጥለው የተጠቀሱት ድኻን አለመናቅና አለመቀማት፣ ከቁጡ ሰው ጋር ተባባሪ አለመሆን፣ አባቶች ያኖሩትን ድንበር አለማፍረስ ናቸው።
▶️፱. ምሳ.፳፬፥፲፭ ላይ "ኃጥኣንን ወደ ጻድቃን ቦታ አትውሰድ" ሲል ምን ለማለት ነው?
✔️መልስ፦ ኃጥኣንን ወደ ጻድቃን ቦታ አትውሰዳቸው ማለት ጻድቃን ናቸው አትበላቸው ማለት ነው። ኃጥእን ጻድቅ፣ ጻድቅን ኃጥእ ማለት አይገባምና።
▶️፲. "በስውር ያለ ስጦታ ቁጣን ይመልሳል። ስጦታን የሚሸልግ ግን ጽኑ ቁጣን ያመጣል" ይላል (ምሳ.21፥14)። የሚሸልግ ሲል ምን ማለቱ ነው?
✔️መልስ፦ የሚሸልግ ማለት ስጦታን ላለመስጠት የሚሳሳ፣ ወይም ሰጥቶ የሚያዝን ሰው ማለት ነው።
▶️፲፩. ምሳ.24፥16 ላይ "ጻድቅ ሰባት ጊዜ ይወድቃልና ይነሣማል። ኃጥኣን ግን በክፉ ላይ ይወድቃሉ" ሲል ምን ለማለት ነው ቢያብራሩልኝ?
✔️መልስ፦ ጻድቅ ሰባት ጊዜ ቢወድቅ ማለትም ፈጽሞ ቢወድቅ ይነሣል ማለት በንስሓ ከበደሉ ወጥቶ የቅድስና ሥራ ይሠራል ማለት ነው። ኃጥኣን ግን በክፉ ሥራ ጸንተው ይኖራሉ ማለት ነው።
▶️፲፪. ምሳ.22፥8 ላይ "ኃጢአትን የሚዘራ መከራን ያጭዳል። የቍጣውም በትር ይጠፋል" ይላል። የቁጣውም በትር ይጠፋል ሲል ምን ማለቱ ነው?
✔️መልስ፦ አማርኛው ትርጉም አሻሚ ስላደረገው ነው እንጂ ኃጢአትን የሚሠራ ሰው በመቅሠፍት ይጠፋል ማለት ነው። ግእዙ ደህና ገልጾታል። "ወዘይዘርዕሰ ኅብለ የዐርር እከየ። ወመቅሠፍተ ምግባሪሁ ይፌጽም" ይላል።
▶️፲፫. ምሳ.22፥14 ላይ "የጋለሞታ ሴት አፍ የጠለቀ ጕድጓድ ነው። እግዚአብሔር የተቈጣው በእርሷ ይወድቃል" ይላል። እግዚአብሔር የተቆጣው በእርሷ ይወድቃል ሲል እግዚአብሔር በሴቷ ፈቅዶ እንደሚያሰናክለው (እንደሚቀጣው) ለማለት ነው? እግዚአብሔር ከተቆጣን በሌላ ኃጢአት እንድንወድቅ ያደርጋል ማለት ነው? ግን እግዚአብሔር መውደቃችንን አይፈልግም ከተባለ ከዚህ ጋር እንዴት ይታረቃል?
✔️መልስ፦ እግዚአብሔር የተቆጣው ተብሎ የተገለጸው እግዚአብሔር ረድኤቱን የነሣው ለማለት ነው። ሰው ኃጢአትን ሲሠራ እግዚአብሔር ረድኤቱን ይነሣዋል። በዚህ ጊዜ ሰው በጥፋት ላይ ጥፋት ይሠራል። ይህን ለመግለጽ የተነገረ ነው። እግዚአብሔር መውደቃችንን አይፈልግም። ግን ደግሞ የነጻነት አምላክ ስለሆነ አስገድዶ አያጸድቀንም። ሰው ነጻ ፈቃዱን ተጠቅሞ ከበደለ በራሱ ጥፋት ይወድቃል።
▶️፲፬. ምሳ.23፥16 ላይ "ከንፈሮችህም በቅን ቢናገሩ ኵላሊቶቼ ደስ ይላቸዋል" ይላል። ኩላሊቶቼ ያላቸው እነማን ናቸው?
✔️መልስ፦ በኵላሊት መላውን አካል መናገር ነው። ሰው አንደበቱ ቅን ነገርን ሲናገር ሕዋሳቶቹ ደስ ይላቸዋል ማለት ነው።
▶️፲፭. ምሳ.23፥34 ላይ "በባሕር ውስጥ እንደ ተኛ ትሆናለህ። በደቀልም ላይ እንደ ተኛ" ይላል። ደቀል ምንድን ነው?
✔️መልስ፦ ደቀል የሚባለው የመርከብ ጫፍ ማለት ነው። በዚያ የተኛ ሰው ማዕበል ሞገድ በተነሣ ጊዜ ፈጥኖ እንደሚወድቅ እንዲህ ትሆናለህ ማለት ትወድቃለህ ማለት ነው።
▶️፲፮. "ኃጥእም የጻድቅ ቤዛ ነው" ይላል (ምሳ.21፥18)። ትርጓሜ ምንድን ነው?
✔️መልስ፦ ቤዛ ማለት ምትክ ማለት ነው። በዚህ አግባብ ኃጥእ የጻድቅ ቤዛ ነው ማለት በጻድቁ ምትክ መከራን የሚቀበል ነው ማለት ነው። በግ የይስሐቅ ቤዛ ሆነ ማለት በይስሐቅ ፈንታ ተሠዋ ማለት ነው። ስለዚህ ጻድቃን ከመከራ ሲድኑ በኃጥኣን መከራ እንደሚመጣ ለማመልከት የተነገረ ነው።