▶️፴፩. ምሳ.24፥54 ላይ "ለአልቅት" ሲል ምን ማለት ነው?
✔️መልስ፦ አልቅት የሚባለው በወንዝ አካባቢ የሚገኝ ከብቶች ውሃ ሲጠጡ ከውሃው ጋር አብሮ ወደ ሰውነታቸው ገብቶ ደማቸውን የሚመጥ ተሳቢ የሚያሙለጨልጭ ፍጥረት ነው።
▶️፴፪. ምሳ.22፥1 ላይ "መልካም ስም ከብዙ ባለጠግነት ይሻላል" ሲል ምን ለማለት ነው?
✔️መልስ፦ ብዙ ባለጠግነት ካላበሉበት ካላጠጡበት ኃላፊ ነው። ሰው ግን ባለጠጋ ሆኖ ነዳያንን ቢያበላበት፣ ቢያጠጣበት እርሱማ በጎ ሰው ነው፣ በጎ ሰው ነበር እየተባለ በመልካምነት ስሙ ይጠራል ይወሳል ይነገራል ማለት ነው።
▶️፴፫. ምሳ.24፥73 ላይ ሰሎሞን ልጁን እንዴት የማኅፀኔ ልጅ ይላል? ሴት አይደለምና።
✔️መልስ፦ ማኅፀን ያላት ሴት ናት እንጂ ወንድ ማኅፀን እንደሌለው የታወቀ ነው። ከዚህ ላይ ሰሎሞን የማኅፀኔ ልጅ ያለው ግን ከባሕርይዬ የምትወለድ የባሕርዬ ልጅ ለማለት ነው። ማኅፀን ያለው ባሕርይውን ነው።
▶️፴፬. "ጥበብ ወይም ማስተዋል ወይም ምክር በእግዚአብሔር ላይ የለም" ይላል (ምሳ.21፥30) ምሥጢሩ ምንድን እንደሆነ ቢብራራልን።
✔️መልስ፦ ግእዙ የተሻለ አድርጎ ገልጾታል። "አልቦ ጥበብ ወአልቦ እዘዝ በኀበ ዐብድ ወአልቦ ምክር በኀበ ረሲዕ" ይላል። ትርጉሙም በሰነፍ ሰው ጥበብ ማስተዋል (ሥልጣን) የለም። እግዚአብሔርን በዘነጋ ሰውም ምክር የለም ብሎታል። ጥበብ፣ ምክር፣ ማስተዋል በእግዚአብሔር ላይ የለም ማለት እግዚአብሔርን የሚቃወም ጥበብ፣ ምክር፣ ማስተዋል የለም ማለት ነው። በዚህም እንግሊዘኛው ከአማርኛው ጋር ተቀራራቢ አገላለጽ ቢጠቀምም "በ...ላይ" የሚለው ቃል ግን "Against" ብሎ ተቃውሞን አመላክቶ ከአማርኛው ሻል ያለ አገላለጽን ተከትሏል። "There is no wisdom nor understanding nor counsel against the LORD" ይላል።
© በትረ ማርያም አበባው
✝️የዩቲዩብ ቻናሌ:- ንሕነ ዘክርስቶስ https://youtube.com/@edenawizechristos?si=6V4y-73OM3LTzhAf ነው።
🌻የፌስቡክ ገጼ Betremariam Abebaw https://www.facebook.com/profile.php?id=100075547015721 ነው።