© ሊቀ ሊቃውንት ስምዐኮነ መልአክ እንደጻፉት
በጉባኤ ቤት መኖር ደስ የሚያሰኘው በየዕለቱ አዲስ አዲስ ሰው ተፈጥሮ ስለሚያድር ነው። በአትክልት ስፍራ ብትኖሩ በየጊዜው ፍሬ የሚሰጡ፣ በመዓዛቸው ልብን የሚመስጡ ዕፀዋትን ልትመለከቱ ትችላላችሁ በዚህ ከምትደሰቱት በላይ በየዕለቱ እግዚአብሔር ሰው ሲሠራ የምትመለከቱበት ቦታ ስለሆነ በጉባኤ ቤት የመኖርን ጣዕም ብትቀምሱት ደግሞ ከዚህ በላይ በጣም ትወዱታላችሁ።
እኛ የተከልነውን፣ ያጠጣነውን እግዚአብሔር ደግሞ ዕለት ዕለት ያሳድግ ነበርና ይኸው ዛሬ ማደጉን የሚያስረዳ ፍሬውን አንዥርግጎ መታየት ከጀመረ ይህ ለሁለተኛ ጊዜ ነው። በመገብተ ኦሪት የቀመስነውን ፍሬ ደግመን እንድናጣጥመው ይዞልን ብቅ ብሏል።
እንደ አባቶቹ ወምበር ተክሎ ጉባኤ አስፍቶ ያስተማረ በዐውደ ምሕረትም አንደበቱ የሚጣፍጥ የተወደደው ወንድማችን መምህር ምሥጢሩ ታየ ዛሬ በነገረ እግዚአብሔር ላይ ከመምህራን አፍ፣ ከከርሠ መጽሐፍ የሰበሰበዉን ቤተ ክርስቲያን ስለ ነገረ እግዚአብሔር የምትሰብከዉን ቃል በመጽሐፍ ይዞልን በመምጣቱ እያመሰገንሁ ለአንባብያን ደግሞ ቆላ ሳንወርድ ደጋ ሳንወጣ በቆላና በደጋ በሩቅና በቅርብ ያሉ መምህራን ያስተማሩትን በልዩ ልዩ ቋንቋ የተጻፉ መጻሕፍት ለዘመናት በውስጣቸው የተሸከሙትን የሕይወት ቃል ቤታችን ድረስ ስለመጣልን በምስጋና ሁሉም እንዲያነበው እጋብዛለሁ።
ጣዕም የሕይወት ስንቅ ይዞልን ስለመጣ ሁላችንም እጃችንን ዘርግተን እንድንቀበለው እጠይቃለሁ!
© ሊቀ ሊቃውንት ስምዐ ኮነ መልአክ