Postlar filtri


አዳዲስ መረጃዎችን ይፈልጋሉ?

በፕሮፌሺናል ጋዜጠኞች ተከፍቶ መረጃዎችን ተከታትሎ በሚዛናዊነት የሚያቀርብ ቻናል ልጠቁማችሁ ፡፡

ተማመኑበት ታተርፉበታላችሁ ተቀላቀሉት
👇👇👇
https://t.me/+gPveFwjiiXdiMDE0
https://t.me/+gPveFwjiiXdiMDE0


ቲክቶክ አሜሪካ ፌደራል መንግስት እገዳ ምክንያት ጊዜያዊ በሆነ መልኩ ከተዘጋ በኋላ ለአሜሪካ ተጠቃሚዎች አገልግሎቱን እየመለሰ መሆኑን አስታውቋል። እገዳው የተጣለው በመተግበሪያው ላይ ያሉ ሊሆኑ የሚችሉ የደህንነት ስጋቶች እና ከቻይና መንግስት ጋር ያለው ግንኙነት ላይ በተነሱ ስጋቶች ላይ ተመስርቶ ነው። ሆኖም ምርጫ ያሸነፉት ፕሬዚዳንት ትራምፕ መተግበሪያውን ለመመለስ የአስፈጻሚ ትዕዛዝ ለመስጠት ቃል ገብተዋል፣ እናም ቲክቶክ የእሳቸውን አቅጣጫ ለማክበር እየሰራ ነው።
ይህ ዜና በመዝናኛ፣ በማህበራዊ ግንኙነት እና በንግድ ላይ በቲክቶክ የሚመኩ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ተጠቃሚዎች ዘንድ እፎይታ አምጥቷል። በቅርብ ዓመታት ውስጥ የመተግበሪያው ተወዳጅነት በከፍተኛ ሁኔታ ጨምሯል፣ እና ድንገተኛው መዘጋቱ በተጠቃሚዎች መካከል ሰፊ መስተጓጎል እና ብስጭት አስከትሏል።
አገልግሎቱ እንደገና መጀመሩ አዎንታዊ እድገት ቢሆንም፣ ቲክቶክ በዩናይትድ ስቴትስ ለረጅም ጊዜ መስራት እንደሚችል ግልጽ አይደለም። መተግበሪያው ከህግ አውጭዎች እና ከተቆጣጣሪዎች ቀጣይ ምርመራ እያጋጠመው ሲሆን ለደፊቱም አለመረጋጋት አለው።


ቲክቶክ በአሜሪካ አገልግሎቱ ተቋረጠ

ቲክቶክ ከደቂቃዎች በፊት በአሜሪካ መስራት አቁሟል።

ከቻይና መንግስት ጋር ግንኙነት እንዳለው በአሜሪካ መንግስት ክስ የቀረበበት የቲክቶክ ዋና ድርጅት ባይት ዳንስ ማስተካከያ እንዲያደርግ ወይም የድርጅቱን የአሜሪካ ቅርንጫፍ ለአሜሪካ ኩባንያዎች እንዲሸጥ ተጠይቆ ነበር።

ቲክቶክ አገልግሎቱ ለ175 ሚልዮን አሜሪካውያን ዛሬ ቢቋረጥም ሰኞ እለት ወደ ስልጣን የሚመጡት ዶናልድ ትራምፕ እገዳውን እንደሚያስቆሙት ይጠበቃል።


የጥምቀት ከተራ በዓል በኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ምዕመናን ዘንድ እየተከበረ ይገኛል።

🎥 Binye21


አዳዲስ መረጃዎችን ይፈልጋሉ?

በፕሮፌሺናል ጋዜጠኞች ተከፍቶ መረጃዎችን ተከታትሎ በሚዛናዊነት የሚያቀርብ ቻናል ልጠቁማችሁ ፡፡

ተማመኑበት ታተርፉበታላችሁ ተቀላቀሉት
👇👇👇
https://t.me/+gPveFwjiiXdiMDE0
https://t.me/+gPveFwjiiXdiMDE0


💲ሳምንታዊ የፎሬክስ ትሬዲንግ ውድድሮች!💲
——————————————————————
🔥 ጀማሪዎችን ለማበረታታት ብርፎሬክስ በየሳምንቱ ሚደረጉ የፎሬክስ ትሬዲንግ ውድድሮች ይዞላችሁ መቷል።

🗓️📍ውድድሩ ሚደረገው በብር ፎሬክስ የቴሌግራም ቻናል @birrforex ላይ በየሳምንቱ እሁድ እሁድ ሲሆን።

❔ለጀማሪዎች ሚሆኑ ቀለል ያለ የፎሬክስ ጥያቄና መልስ ይዘት ይኖረዋል።

🏆ቀድሞ በትክክል የመለሰ ተሸላሚ ሚሆን ይሆናል።

🧡በዚውድድር ለመሳትፍ ከናንተ ምንም አይነት ወጪ አያስፈልግም፤ ጥያቄ መመለስ ከዛም መሸለም።

📌ውድድሮቹ ላይ ለመሳተፍ አሁኑኑ ከታች የተቀመጠው የብር ፎሬክስ ቴሌግራም ቻናልን ይቀላቀሉ
➡️➡️➡️➡️@birrforex  👈👈👈👈


"የኢትዮጵያ ብሄራዊ የምርጫ ቦርድ የተናጠል ውሳኔን ዛሬ ይሁን ነገ አልቀበልም " - በደብረፅዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር ) የሚመራው ህወሓት ማእከላይ ኮሚቴ

በደብረጽዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) የሚመራው የህወሓት ማእከላይ ኮሚቴ ከጥር 5 እስከ ጥር 7 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ በወቅታዊ የክልሉ ሁኔታ ላይ አተኩሮ ስብሰባ ተቀምጦ ነበር።

ይህንን ተከትሎ ዛሬ ምሽት መግለጫ አውጥቷል።

በዚህም ቡድኑ ፦
- እስከ አሁን ያልተረጋገጠው የትግራይ ግዛታዊ አንድነት፤
- ተፈናቃዮች እና ስደተኞች ወደ ቄያቸው አለመመለስ፤
- የኢትዮጵያ ብሄራዊ የምርጫ ቦርድ ያወጣውን መግለጫ፤
- የፕሪቶሪያ የሰላም ውል አፈፃፀም በሚሉ አጀንዳዎች ላይ መወያየቱን ገልጾ " ቀጣይ የመፍትሄ እና የትግል አቅጣጫ አስቀምጫለሁ " ብሏል።

የህወሓት ማእከላዊ ኮሚቴ ባወጣው መግለጫ ፤ በፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት መሰረት የኢፌዴሪ ህገ-መንግስት እውቅና የሰጠው የትግራይ ግዛታዊ አንድነት አለመረጋገጡ ጠቅሶ " ተፈናቃይ እና ስደተኞች ወደ ቄያቸው ባለመመለሳቸው ሃዘን እና ቁጣ ተስምተኞናል ይህንን አስመልክቶ ' ይበቃል ' በሚል የተካሄደው ሰላማዊ የተቃውሞ ሰልፍ እደግፋለሁ " ብሏል።

ቡድኑ በመግለጫው " የፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት በአግባቡ እንዳይፈፀም የኢትዮጵያ መንግስት እንቅፋት እየሆነ ነው ፡ በትግራይ ውስጥ የበቀለ
#ከሃዲ_ሃይልም በተጨማሪ ስምምነቱ እያደናቀፈ ነው " የሚል ክስ አሰምቷል።

እንዴት እንደሆነ ባያብራራም " ችግሩ ከስር መሰረቱ ለመለወጥ ቆርጬ ተነስቻለሁ " ብሏል።

በመሰረተ ሃሳብ ደረጃ DDR ተቀባይነት ያለው እንደሆነ የገለፀም ሲሆን " ይሁን እንጂ DDR እንደምክንያት በመጠቀም የትግራይ ሰራዊት ለማፍረስ እየተደረገ ያለው ሴራ ተቀባይነተ የለውም " ሲል ገልጿል።


ታላቅ ቅናሽ ስራ ለመጀመር!

የ ሜካፕ መስሪያ መስታወት እና እቃ ማስቀመጫ ሼልፍ አንድላይ 30,000
2 ፍሬ አለን

የ ማስተማሪያ ወንበር 6 ፍሬ አለን አንድ 8,000 ብር

የ አይላሽ መስሪያ 3ፍሬ አለን
አንድ 20,000 ብር

የ ጥፍር ጠረቤዛ 3 ሰዉ የሚይዝ 20,000

አድራሻ ፡ ቦሌ ድልድይ ብራስ ሆስፒታል ተሻግሮ የሺ ህንፃ 3ኛ ፍቅ
ስልክ 0923 98 60 56


⚠️ ጥንቃቄ

#Brooknews የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በካናዳ የሥራና ትምህርት ዕድል ለማመቻቸት ሕጋዊ ውክልና በውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞትዮስ (ዶ/ር) የተሰጣቸው በማስመሰል ሕገ ወጥ ደብዳቤ አዘጋጅተው እያሰራጩ ያሉ አካላት መኖራቸውን አስታውቋል፡፡

የሚኒስትሩ ስም ተጠቅሶ በተለያዩ የማህበራዊ ትስስር ገጾች እየተዘዋወረ የሚገኘው ደብዳቤ ሃሰተኛ መሆኑንም ሚኒስቴሩ አረጋግጧል፡፡

መሰል የወንጀል ተግባር እየፈፀሙ የሚገኙ አካላትን በሕግ ተጠያቂ ለማድረግ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር እየተሰራ መሆኑ ተመላክቷል፡፡

ሕብረተሰቡም ይህንን ተገንዝቦ ራሱን ከአጭበርባሪዎች እንዲጠብቅ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አሳስቧል፡፡


የተኩስ አቁም ስምምነት በተደረሰባት ጋዛ እስራኤል በፈጸመችው የአየር ጥቃት 73 ፍልስጤማውያን መገደላቸው ተገለጸ።

እስራኤል እና ሐማስ የደረሱት የተኩስ አቁም ስምምነት በመጪው እሁድ፣ ጥር 11/2017 ዓ.ም. ተግባራዊ መሆን ይጀምራል የተባለ ሲሆን፣ እስራኤል በጋዛ እየፈጸመችው ያለው ጥቃት እንደቀጠለ ነው።

ሁለቱ ወገኖች የደረሱት የተኩስ አቁም ስምምነት ከእስራኤል በኩል የምክር ቤቱን ይሁንታ ማግኘት አለበት ተብሏል።

የተኩስ አቁም ስምምነቱ ረቡዕ፣ ጥር 7/2017 ዓ.ም. ይፋ መሆኑን ተከትሎ እስራኤል በፈጸመችው ጥቃት 73 ፍልስጤማውያን በአንድ ምሽት መገደላቸውን በሐማስ የሚተዳደረው የሲቪል መከላከያ ኤጀንሲ አስታውቋል።

ከተገደሉት መካከል በጋዛ ከተማ ሼክ ራድዋን ሰፈር በአንድ መኖሪያ ህንጻ ነዋሪ የነበሩ 12 ሰዎች እንደሚገኙበት የጋዛ የጤና ሚኒስቴር ገልጿል።

የእስራኤል መከላከያ በበኩሉ በደቡባዊ እስራኤል "የወደቀ ሚሳኤል" ማግኘቱን መጀመሪያ ላይ አስታውቆ የነበረ ቢሆንም በኋላ ግን ስህተት ነው ብሏል።

እስራኤል የተኩስ አቁም ስምምነቱ ጫፍ ላይ ደርሷል በተባለበት ወቅትም እየፈጸመችው ያለውን የአየር ጥቃት ቀጥላለች።
ዘገባው የ ቢቢሲ (BBC)


የአዲስ አበባ ከተማ አውቶብስ አገልግሎት ድርጅት "በድልድል እና ምደባ" 400 የሚሆኑ ሠራተኞችን ከጥር ጀምሮ ከሥራ ማሰናበቱን ሠራተኞች እና ድርጅቱ ተናገሩ። ድርጅቱም የብቃት ፈተና እና ውድድር ያላለፉ ሠራተኞችን ከሥራ መቀነሱን ገልጾ "የሪፎርም ባሕሪ ነው" ሲል ለቢቢሲ ምላሽ ሰጥቷል።


በትግራይ ክልል የአክሱም ወረዳ ፍርድ ቤት ሙስሊም ሴት ተማሪዎች ሂጃብ እንዳይለብሱ የሚከለክለውን መመሪያ ትናንት ማገዱን የሙስሊም ዜና ምንጮች ዘግበዋል። ከትምህርት የታገዱ ሙስሊም ሴት ተማሪዎች ወደ ትምህርት ገበታቸው እንዲመለሱ ያዘዘው ፍርድ ቤቱ፣ በሂጃብ ምክንያት ተማሪዎችን ከትምህርት ገበታ ያገዱ ትምህርት ቤቶችም ጥር 16 ፍርድ ቤት ቀርበው ቃላቸውን እንዲሠጡ ማዘዙን ዘገባዎቹ ጠቅሰዋል። የክልሉ እስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት እገዳው እንዲነሳ ክስ መመስረቱን ባለፈው ሳምንት ገልጦ ነበር።

Via Brook News
Source Wazema


💲ሳምንታዊ የፎሬክስ ትሬዲንግ ውድድሮች!💲
——————————————————————
🔥 ጀማሪዎችን ለማበረታታት ብርፎሬክስ በየሳምንቱ ሚደረጉ የፎሬክስ ትሬዲንግ ውድድሮች ይዞላችሁ መቷል።

🗓️📍ውድድሩ ሚደረገው በብር ፎሬክስ የቴሌግራም ቻናል @birrforex ላይ በየሳምንቱ እሁድ እሁድ ሲሆን።

❔ለጀማሪዎች ሚሆኑ ቀለል ያለ የፎሬክስ ጥያቄና መልስ ይዘት ይኖረዋል።

🏆ቀድሞ በትክክል የመለሰ ተሸላሚ ሚሆን ይሆናል።

🧡በዚውድድር ለመሳትፍ ከናንተ ምንም አይነት ወጪ አያስፈልግም፤ ጥያቄ መመለስ ከዛም መሸለም።

📌ውድድሮቹ ላይ ለመሳተፍ አሁኑኑ ከታች የተቀመጠው የብር ፎሬክስ ቴሌግራም ቻናልን ይቀላቀሉ
➡️➡️➡️➡️@birrforex  👈👈👈👈


ይሄን ቻሌንጅ ተቀላቀሉ።


"ዳታን" ሊለቀቅ ነው
የያሬድ ነጉ የመጀመርያ የሆነው ዳታ የሙዚቃ አልበም ሊለቀቅ ነው።
#Ethiopia | ድምጻዊ ያሬድ ነጉ "ዳታን" የተሰኘው የመጀመሪያ አልበሙ ለማስመረቅ በዝግጅት ላይ ይገኛል፡፡
ይህ "ዳታን" የተሰኘው አልበም በግጥም ወንደሰን ይሁብ፣ ፍሬዘር አበበወርቅ፣እዩቤል ብርሃኑ፣ ሃ/ማርያም መንግስቴ ፣ ጃሉድ አወል፣ሄኖክ ክብሩ(ጎፈር)መልእቲ ኪሮስ እና ፈለቀ ማሩ በዜማ ፋኑ ጊዳቦ ፣ ፀጋው ተክሉ (ቹቹ) ፣ኤሊያስ ግዛቸው ፣ጃሉድ አወል፣ሙሉአለም ታከለ እና ዩሃና ሲሆን በመዚቃ ቅንብር ሚካኤል ኃይሉ (ሚኪ ጃኖ) ፣ስማገኘው ሳሙኤል፣ፋኑ ጊዳቦ፣ ጊልዶ ካሣ፣ሱራፌል የሺጥላ እና ሃይፐር በሚክሲንግ ይትባረክ ክፍሌ ማስተሪንግ ክሩቤል ተስፋዬ ተሳትፈውበታል፡፡
ከነዚህም መካከል:- ከዳይመንድ፣ ያሚ አላዲ፣ሪቫኒ እና ሃርመናይዝ ጋር ሙዚቃን በብቃት መጨወት ችሏል፡፡
ድምጻዊ ያሬድ ነጉ ከሀገራች በርካታ ወጣት ድምጻዊያን ጋር ሙዚቃን አብሮ በመስራት በህዝብ ዘንድ እውቅናን ተወዳጅነትነ አግኝቷል፡፡
ዳታን አልበም 11 track ያሉት ሲሆን አርቲስቱ የአለቀ አልበም አፍርሶ እንደ አዲስ የሰራው አልበም ነው ፡፡
ዳታን አልበምን ሰርቶ ለማጠናቀቅ 3 ዓመት እና ከፍተኛ በጅት ፈጅቷል።
አልበሙ ላይ ሦስት የሙዚቃ ቪዲዮዎችን ተሰርቶ የተጠናቀቁ ሲሆን ይህ አልበም ሙሉ በሙሉ ወጪ በድምጻዊ ያሬድ ነጉ ፕሮዲዩስ ተደርጓል፡፡
በቴሌግራም ካሴት የቴሌግራም ቻናል የሚገኝ ሲሆን አልበሙን በሲዲ አሳትሞ የሚያከፋፍለው ኪነት ኢንተርቴይመንት አማካኝነት ይሆናል፡፡
ስለዚህ እናንተ የሚዲያ ሰዎች ሰምታችሁ ለሁሉም እንድታዳርሱ ስል በአክብሮት እጠይቃለሁ ፡፡


"የኢትዮ ቴሌኮም ሠራተኞች፣ በኩባንያው ውስጥ ካለፉት ሦስት ዓመታት ወዲህ የሠራተኛ የደረጃ ዕድገትና ዝውውር የሚፈጸመው ሕግን ባልተከተለ መንገድ ነው"ሲሉ ቅሬታቸውን አሰምተዋል።

"የሠራተኛ ዕድገትና ዝውውር ይፋዊ ማስታወቂያ ወጥቶ በውድድር መሆኑ ቀርቶ፣ በሃላፊዎች ውሳኔ ብቻ እየተፈጸመ እንደሆነ ሠራተኞቹ ነግረውኛል" ብሏል ራዲዮው። "በአሁኑ ወቅት አዲስ አበባ ውስጥ በሚገኝ አንድ የተቋሙ ቅርንጫፍ የሚሠራ ሠራተኛ ለደረጃ ዕድገት ከተማዋ ውስጥ ባለ ሌላ ቅርንጫፍ መወዳደር የማይችልበት ሁኔታ እንደተፈጠረም" ሠራተኞች ለራዲዮው ገልጸዋል።

በጉዳዩ ዙሪያ የኩባንያው የሠራተኛ ማኅበር ፕሬዝዳንት ካሳሁን ሰቦቃ ማብራሪያ እንዲሰጡ በራዲዮው ተጠይቀው "ማብራሪያ ለመስጠት በቅድሚያ የሥራ አስፈጻሚው ውሳኔ ያስፈልጋል" ሲሉ መልሰዋል።
ዋዜማ ራዲዮ እንደዘገበው


🔥 በጉጉት ሲጠበቅ የነበረው እና በአጭር ግዜ ውስጥ የ TIKTOK ተፅኖ ፈጣሪ እና ኮንተንት ክሬተር የሚያደርጋቹ ስልጠና ተጀምሯል::

ብሩክ ኒውስ ከሌሎች ተፅኖ ፈጣሪዎች ጋር በመሆን ይሄን ስልጠና በብዙዎች ጥያቄ መሰረት በ WEBSITE ( https://brooknewstraining.com/) ይዞላቹ መቷል::

በኮርስ ታላቅ ቅናሽ ተደርጎ በ 450 ብር ብቻ ለናንተ ቀርቧል::
በዚህ ስልጠና
1. TikTok Content Creation Strategy
2. TikTok Video Filming and Editing Technique
3. TikTok Promotion Marketing Strategy

ስልጠናውን ለመከታተል ከታች ባለው ዌብሳይት በኩል በመግባት እና REGISTER በማድረግ በቴሌብር ክፍያዎን በመፈፀመ መከታተል ትችላላቹ::
https://brooknewstraining.com/


✅Broz mobile and computer ✅

🍏Original iPHONE, MacBook, Samsung & Tab Apple watch’s አዳዲስ እንዲሁም ያገለገሉ ስልኮችን በተመጣጣኝ ዋጋ እና ያሎት ስልክ ላይ በመጨመር ከበቂ ዋስትና እና ጥገና ጋር እኛው ጋር ያገኛሉ ።

📢Telegram Channel
https://t.me/+rKw6vNZJp49kOWM0
ቀድመው ይደውሉ 👇
Contact us ☎️
+251911120707
+251904818881
📍ቦሌ መድሃኒአለም


Video oldindan ko‘rish uchun mavjud emas
Telegram'da ko‘rish
የቪዛ ሂደትን የሚያቃልል አፕሊኬሽን ተጀመረ!

ላይን አዲስ ኮንሰልቲንግ በሃገራችን በአይነቱ የመጀመርያው የሆነው የተላያዩ የቪዛ አይነቶችን ለማመልከት የሚያስፈልግዎትን ሙሉ መረጃ ለማግኘትና ማንኛውም ተያያዥ የማመልከቻ አገልግሎቶችን ካሉበት ሆነው የሚያገኙበትን GoLine የተባለ የሞባይል መተግበርያ አቅርቧል!

ይህን አፕሊኬሽን ከፕሌይና አፕስቶር መጫን ሳይጠበቅብዎ በቀላሉ በቴሌግራም ላይ መክፈት የሚችሉትና ከ40 በላይ በሚሆኑ አዲስ አበባ ካሉ ኤምባሲዎች የጉብኝትና ሌሎች የቪዛ አይነቶችን ለማመልከት የሚያስፈልግዎትን መረጃ ለማግኘት ፡ በተለያዩ ሃገራት ስላሉ የስኮላርሽፕ እድሎችን ለማመልከት እንዲሁም የተለያዩ አለም አቀፍ የጉብኝት ጥቅሎችን መግዛት የሚችሉበት መተግበርያ ሲሆን በተጨማሪም በቪዛ ማመልከቻ ሂደትዎ ላይ የሚያስፈልግዎትን አገልግሎቶች፡ ከማማከር ጀምሮ፡ ቀጠሮ ማስያዝ፡ የቪዛ ኢንተርቪው ትሬኒንግ መስጠትና የቪዛ ፎርምና ዶክመንቶችን ማዘጋጀት ጨምሮ የኦንላይን ቪዛ ማመልከቻዎችን በመተግበርያው ማስገባት ይችላሉ !

@Golineapp_bot በማለት ቴሌግራም ላይ ሰርች በማድረግ አፕሊኬሽኑን ማገኘትና መጠቀም የሚችሉ ሲሆን በአካል መማከርና መገልገል የምትፈልጉ ድግሞ ቦሌ ራክሲም ፕላዛ አምስተኛ ፎቅ በሚገኘው የላይን አዲስ ኮንሰልቲንግ መስሪያ ቤት አገልግሎቱን ማግኘት ይችላሉ፡


#እንድታውቁት

ከተሻሻለው የመንገድ ትራንስፖርት ትራፊክን ለመቆጣጠር የወጣው የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ

➡ ከፖሊስ በተሽከርካሪ ላይ የደረሰውን የጉዳት አይነት የሚገልጽ የፅሁፍ ማስረጃ ሳይቀበሉ ጥገና የሚያከናውኑ ጋራዦች / የጋራዥ ባለቤቶች / በወንጀል ህግ የሚጠየቁት እንዳለ ሆኑ የ20 ሺህ ብር ቅጣት ይጣልባቸዋል።

➡ አመታዊ የተሽከርካሪ ምርመራ ያላደረገ የተሽከርካሪ ባለንብረት 3,000 ብር ይቀጣል።

➡ የአሽከርካሪ ብቃት ማረጋገጫ ፈቃድ ሳይኖረው ተሽከርካሪ ያሽከረከረ ማንኛውም ሰው 5,000 ብር ይቀጣል።

➡  የአሽከርካሪ ብቃት ማረጋገጫ ፈቃድ ሳይኖረው ተሽከርካሪ በማሽከርከር በንብረት ላይ ጉዳት ያደረሰ ማንኛውም ሰው 7000 ብር ይቀጣል።

➡ ከባለቤትነት ወይም በይዞታው የተያዘውን ተሽከርካሪ የአሽከርካሪ ብቃት ማረጋገጫ ፈቃድ ለሌላው ሰው አሳልፎ የሰጠ ማንኛውም የተሸከርካሪ ባለንብረት 3,000 ብር ይቀጣል።

🚨የትራፊክ ግጭት ወይም ጉዳት አድርሶ በቦታው ላይ ያልቆመ ወይም ባደረሰው የትራፊክ ጉዳት የተጎዳውን እና ሕክምና የሚያስፈልገውን ሰው ወደ ህክምና በመውሰድ እንዲታከም ያላደረገ 👉 በወንጀል ህጉ መሰረት ይጠየቃል።

➡ ወጣት አሽከርካሪዎች፣ ጀማሪ አሽከርካሪዎች ፣ ሞተር ሳይክል አሽከርካሪዎች ፣ የንግድ ተሽከርካሪ አሽከርካሪዎች እና አደገኛ ጭነት የጫኑ አሽከርካሪዎች የአልኮል መጠን በትንፋሽ በየትኛውም መጠን ከተገኘ 2,000 ብር ቅጣት ይጠብቃቸዋል።

➡ የአሽከርካሪ ብቃት ማረጋገጫ ፈቃድ ታግዶበት ሳለ ያሽከረከረ 3,000 ብር ቅጣት ይጣልበታል።

➡ አልኮል መጠን በትንፋሽ ውስጥ ፦
🍻 0.24 እስከ 0.6 ሚሊግራም/ሊትር 1,500 ብር ያስቀጣል።
🍻 0.61 እስከ 0.8 ሚሊግራም /ሊትር 2,000 ብር ያስቀጣል።
🍻 0.81 እስከ 1.0 ሚሊግራም/ሊትር 2,000 ብር ያስቀጣል።
🍻 1.0 ሚሊግራም/ሊትር በላይ የተገኘበት 3,000 ብር ይቀጣል።

➡ በተሽከርካሪ ላይ ተገቢ ያልሆነ አካል የጨመረ ወይም ከተፈቀደለት ወንበር ውጭ ተጨማሪ ወንበር ወይም መቀመጫ የጨመረ የተሽከርካሪ ባለንብረት 400 ብር ይቀጣል።

➡ የህዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪ ሞተር እየሰራና በተሽከርካሪው ውስጥ መንገደኞች እያሉ ነዳጅ መሙላት 1,500 ብር ያስቅጣል።

➡ ቴሌቪዥን ወይም ሌሎች ምስሎችን ተሽከርካሪ ውስጥ እየተመለከተ ያሽከረከረ 1,500 ብር ይቀጣል።

➡ የደህንነት ቀበቶ ሳያስር ወይም ተሳፋሪዎች የደህንነት ቀበቶ ማሰራቸውን ሳያረጋግጥ ያሽከረከረ 1,500 ብር ይቀጣል።

➡ የተንቀሳቃሽ ስልክ በእጁ ይዞ እያነጋገረ፣ ወይም መልዕክት እየጻፈ እየላከ ወይም እያነበበ ያሽከረከረ 1,500 ብር ይቀጣል።

➡ ጫት ቅሞ ወይም እየቃመ ወይም አደንዛዥ ዕፅ ወስዶ ያሽከረከረ 1,500 ብር ይቀጣል።

➡ የተሽከርካሪ የፊት ወይም የኃላ ሰሌዳ ሳይኖረው ያሽከረከረ 1,500 ብር ይቀጣል።

➡ ለአውቶብስ ብቻ ተብሎ በተለየ መንገድ ላይ ያሽከረከረ 1,500 ብር ይቀጣል።

➡ ቀይ መብራት የጣሰ 1,500 ብር ይቀጣል።

➡ የትራፊክ ተቆጣጣሪ ትዕዛዝ ያልፈጸመ፣ ወይም የተሳሳተ መረጃ የሰጠ ወይም እንዲቆም ሲታዘዝ በእንቢተኝነት ሳይቆም የሄደ 1,000 ብር ይቀጣል።

➡ የአሽከርካሪ ብቃት ማረጋገጫ ፈቃድ ኖሮት ሳይዝ ያሽከረከረ ወይም የአሽከርካሪ ብቃት ማረጋገጫ ፈቃዱን ሳያሳድስ ያሽከረከረ 1,000 ብር ይቀጣል።

➡ ከተፈቀደው ፍጥናት በታች ያሽከረከረ ወይም የቀኙን ጠርዝ ሳይዝ በዝግታ ያሽከረከረ 1,000 ብር ይቀጣል።

➡ ከመጠን በላይ ድምጽ እያሰማ ወይም የጆሮ ማዳመጫ እያዳመጠ ያሽከረከረ 1,000 ብር ይቀጣል።

➡ መንገድ ላይ ያለን ውሃ በተሽከርካሪው አማካኝነት እግረኛ ላይ እንዲረጭ ያደረገ 1,000 ብር ይቀጣል።

(ተጨማሪ የጥፋት ዝርዝር እና ቅጣቶቹን ከላይ ያንብቡ)
Source
tikvahethiopia

20 ta oxirgi post ko‘rsatilgan.