በሕገ-ወጥ መንገድ 6 ሺህ 200 ግራም ወርቅ ሲያዘዋውሩ የነበሩ ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ
በሕገ-ወጥ መንገድ 6 ሺህ 200 ግራም (6 ነጥብ 2 ኪሎ ግራም) ወርቅ ሲያዘዋውሩ የነበሩ ተጠርጣሪዎች በአፋር ክልል ሰመራ ከተማ በቁጥጥር ሥር መዋላቸው ተገለፀ፡፡
ከአዲስ አበባ ወደ አክሱም በሚጓዝ የሕዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪ የውስጥ ክፍል 6 ሺህ 200 ግራም ወርቅ በመደበቅ ለማሳለፍ ሲሞክሩ የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ አባላት ከብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ሠራተኞች ጋር ባደረጉት ክትትል ተጠርጣዎቹ በቁጥጥር ስር መዋላቸው ተገልጿል፡፡
ገብረ ስላሴ ዮሐንስ እና ዓለማየሁ ሰማሞ የተባሉ ሾፌር እና ረዳት ከነኤግዚቢቱ በቁጥጥር ሥር ውለው ምርመራ እየተጣራባቸው መሆኑን የፌደራል ፖሊስ መረጃ ያመላክታል፡