Video oldindan ko‘rish uchun mavjud emas
Telegram'da ko‘rish
በግብፅ እና በእስራኤል መካከል ትልቅ ጦርነት በማንኛውም ሰአት ሊፈነዳ ይችላል ስትል እስራኤል አሳውቃለች።
ክስተቱ ከኢትዮጵያ የተጠጋ ውጤት ሊኖረው የሚችል ነው።
ግብፅ በሲና በረሃ የጦር ሰፈሮች የገነባች ሲሆን፣ እነዚህ ጦር ሰፈሮቿ ለወታደራዊ ማጥቃት ብቻ የሚያገለግሉ እንጂ ለመከላከል አላማ የተገነቡ አይደሉም።
በአሜሪካ የእስራኤል አምባሳደር ግብፅ የሰላም ስምምነቱን በእጅጉ እየጣሰች ነው ብለዋል። በቅርቡ በግብፅ ላይ እርምጃ እንወስዳለን ሲሉ በዛሬው እለት ዝተዋል።
አክለውም (በአሜሪካ የእስራኤል አምባሳደር ይሼል ሊተር፣ ግብፅ ኢንተርኔቱን እና ሶሻል ሚዲያውን በጦር ሰራዊቷ ምስሎች አጥለቅልቃው እየተመለከትን ነው ሲሉ ከሰዋል።
በግብፅ በኩል ያልተለመደ የተባለለት ሰሞንኛ ክስተት የተስተዋለው በተለይም የግብፅ ፓራትሮፐር ብርጌዶች በኦክቶበር 7 ሐማስ ጥቅም ላይ ያዋለውን አይነት የአውሮፕላን ዝላዮች እና ኦፕሬሽኖችን ጨምሮ የተቀናጀ ነው የተባለለትን የወታደራዊ ስልጠና ልምምዶችን የሚያካሂዱበት ተንቀሳቃሽ ምስል በስፋት መዳረሱን ተከትሎ ነው።
ይህ ፍጥጫ ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ጥቅም አኳያ የተያያዘ ውጤት የሚከስት ነው። ግብፅ እና እስራኤል መሰል ፍጥጫዎችን ሲያስተናግዱ የካይሮ የመውጫ በር ከኢትዮጵያ ጉዳይ ጋር በተሰናሰለ ገቢር እልባቱን የማግኘቱ ድግግሞሽ ከድሮ እስከ ዘንድሮ ሳይለወጥ የዘለቀ ሐቅ በመሆኑ። አሁን ግብፅ ከተለመዱ ተመሳሳይ ክስተቶች አንፃር ይበልጥ በተወሳሰበ ሁኔታ ውስጥ መግባቷ ግልፅ ሆኗል። ይኸውም የጋዛ ካርድ፣ የዓባይ ውሃ ካርድ፣ የአረብ ሀገራት ካርድ፣ የእስራኤልና አጋሮቿ የዲፕሎማሲ ጫና ካርድ፣ እንዲሁም የእርዳታ ካርዶች ከአረብ ሀገራት እና ከአሜሪካ መራሹ የምዕራባዊ ሀገራት በኩል እያካለቧት ነው የምትገኘው።
ይሁንና የፕሬዝደንት ትራምፕን አዝማሚያ ለታዘበው የሰሞኑ የሲናይ በረሃ ወታደራዊ ፍጥጫ በዓባይ ውሃ ዙሪያ ኢትዮጵያ ላይ ለሚደቅነው የጫና ወጥመድ ሀገራዊ ዝግጁነትን የሚጠይቅ የማንቂያ ደወል አድርጎ መመልከት ተገቢ እሳቤ ይመስለኛል!!
Via EslemanAbay