ፕሬዝዳንት ዘለንስኪ የባለፈው ሳምንት የኋይት ሀውስ ፍጥጫ “አሳዛኝ” ነው ሲሉ ተናገሩ
የፈረንሳዩ ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮንን ጨምሮ የአውሮፓ መሪዎች ትራምፕ እና ዘለንስኪ ድጋሚ እንዲገናኙ ለማድረግ ጥረት ላይ ናቸው
የባለፈው ሳምንት የኦቫል ኦፊስ ፍጥጫን “የሚያሳዝን” ሲሉ የገለጹት የዩክሬኑ ፕሬዝዳንት ቮለድሚር ዘለንስኪ ከትራምፕ አስተዳደር ጋር ዘላቂ ሰላም ለማስፈን በትብብር መስራት እንደሚፈልጉ ተናግረዋል፡፡
ዘለንስኪ ይህን ያሉት ትራምፕ ለዩክሬን የሚደረገውን ወታደራዊ እርዳታ ማቋረጣቸውን ይፋ ካደረጉ በኋላ በኤክስ ገጻቸው ላይ ባሰፈሩት ጽሁፍ ነው፡፡
"ዩክሬን ዘላቂ ሰላምን ለማምጣት በተቻለ ፍጥነት ወደ ድርድር ጠረጴዛ ለመምጣት ዝግጁ ነች። ከዩክሬናውያን የበለጠ ሰላም የሚፈልግ የለም ፤ እኔና ቡድኔ ዘላቂ ሰላም ለማግኘት በፕሬዝዳንት ትራምፕ ጠንካራ አመራር ስር ለመስራት ዝግጁ ነን” ብለዋል ።
ባሳለፍነው ሳምንት በኋይት ሀውስ ኦቫል ኦፊስ ከፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራፕ እና ከምክትላቸው ጋር የተደረገውን ዱላ ቀረሽ ውይት አስመልክቶ ዘለንስኪ በሰጡት አስተያት “እንደዛ መሆኑ በጣም ያሳዝናል ፤ ነገሮችን ለማስተካከል ጊዜው አሁን ነው። የወደፊቱ ትብብር እና ግንኙነት ገንቢ እንዲሆን እንፈልጋለን ለዚህም ዝግጁ ነን ሲሉ ተናግረዋል"፡፡
Via- አል አይን