🔥ቦምቡም-ፈንድቷል🔥
💥〰️〰️〰️〰️〰️💥
በእርጋታና በጥንቃቄ ይነበብ👇
ወሃቢዮቹ የዛሬ 3 ዓመት ገደማ ለረዥም ሰዓታት ከቀረፁት ከ4ለ4ቱ እጅግ ረዥም ውይይት ላይ እነሱን የሚጠቅማቸው መስሏቸው ሻል ይላል ያሉትን 58 ደቂዳ ብቻ ቆርጠው አውጥተው ነበር፡፡ ዛሬ ከፅሑፌ ጋር ያያዝኩት ቪዲዮ ወሃቢዮቹ ካወጡት ቪዲዮ ላይ የቀነጨብኩት አጭር ቪዲዮ ነው፡፡ ቀንጭቤ ያወጣሁትም 1 ደቂቃ ከ25 ሰከንድ ብቻ የሚፈጅ ቪዲዮ ነው፡፡ ብዙ ሰው ልብ ያላለው ቪዲዮ ይመስለኛል፡፡
👉 ይህን የቀነጨብኩትን አጭር ቪዲዮ ሙሉ ትርጉም በኮመንት ሳጥን ውስጥ አስቀምጬዋለሁ፡፡
በዚህ ቪዲዮ የወሃቢያን አስመሳይነትና ቅጥፈት ድባቅ የሚመቱ በርካታ ነጥቦችን እናገኛለን፡፡ ወሃቢዮቹ ቆርጠው ባወጡት 59 ደቂቃ በማይሞላ ቪዲዮ ይህን ያህል ፋወል ሲሰሩ ስታዩ የተቀረውን ለሰዓታት የተቀረፀውን ረዥም ቪዲዮ ለምን እንዳላወጡትና .. ‹‹እባካችሁ አውጡት›› .. ተብለው ቢለመኑም እስከዛሬ ለምን እንቢ ብለው እንደቀሩ ይገባቹሃል፡፡ ዑለሞቻችን ኪታብ ይዘው በማስረጃና በመረጃ ምን ያህል እርቃናቸውን እንዳስቀሯቸው መገንዘብም ቀላል ነው፡፡ ይህን ደግሞ በወቅቱ ተወያይ የነበሩ የአህለ-ሱና ዑለሞች አስረግጠው ነግረውናል፡፡
ወደ ቪዲዮው እንለፍ፡👇
1️⃣. ከ30 ዓመት ወዲህ ወደ ኢትዮጵያ የገባውን .. ሀገር ያወቀውን እና ፀሐይ የሞቀውን .. የወሃቢያን አይዶሎጂ ሸኽ ጀይላን ትንሽ አሻሽለው 20 አመት መርቀውበት 50 ዓመት ለማድረስ ጥረዋል፡፡ ዕውነታው ግን የወሃቢያ አይዶሎጂ ከ30 ዓመት ወዲህ ወደ ሀገራችን የገባ አይዶሎጂ ነው፡፡ እሳቸው 50 ዓመት ቢሉትም ምንም ያሻሻሉት ነገር የለም፡፡ ያው አልሸሹም ዞር አሉ ነው፡፡ ዞሮ ዞሮ የቡድኑ አይዶሎጂ መጤ ነው፡፡ ምናልባት ወሃቢያ ወደ ሀገራችን ሳይገባ በፊት አስቀድመው እሳቸው ወደ ሳውዲ የሄዱበትን እና የወሃቢያን አይዶሎጂ የተቀበሉበትን ጊዜ ደምረው ይሆናል 50 ዓመት ያደረሱት፡፡ 30 ዓመትም አሉት 50 ዓመት ያው መጤነቱን አይቀየረውም፡፡
ከሁሉም እጅግ የሚገርመውና አደገኛው ደግሞ ዓቂዳና ተውሒድ በጊዜ ሂደት የሚሻሻል እና የሚዘምን አድርገው ማቅረባቸው ነው፡፡ ከእሳቸው ይህን አልጠብቅም ነበር፡፡ እስልምና በተለይ ደግሞ ዐቂዳ እንዴት .. ‹‹ጊዜ አልፎበታል›› .. ሊባል ይችላል?! .. እንዴትስ በዘመናዊ መልኩ ተሻሽሏል ይባላል?!
ሌላው ለ1400 ዓመታት አንድ የነበረውን የኢትዮጵያን ሙስሊም የከፋፈለው ወደ ሀገራችን የገባው የወሃቢያ አስተምህሮ መሆኑንና ከዚያ በፊት በሀገራችን ዑለሞች ዘንድ ይቀሩ የነበሩት የዐቂዳ ኪታቦች የአሽዓሪያ የዐቂዳ ኪታቦች እንደነበሩ የቡድኑ ቁንጮ ከሆኑት ከሸይኽ ጀይላን አፍ ትሰማላችሁ፡፡
ከላይ የተገለፁትን አስመልክቶ ቪዲዮው ላይ እንዲህ ይላሉ፡👇
☄〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️☄
👉 ‹‹(አሽዓሪያን በተመለከተ) አሁን እየተነጋገርን ያለው እኮ (በሀገራችን) ጊዜ ስላለፈበት እና ስላበቃለት ተጨባጭ ነው፡፡ አዎ በእርግጥ ከ50 ዓመት በፊት ‹አስ-ሰኑሲያ› (የተባለው የአሽዓሪያ ዐቂዳ ኪታብና ሌሎችም) በሀገራችን ይቀሩ ነበር ….. እነዚህ ኪታቦች በሙሉ ለዚህ ዘመን አይበጁም፡፡ ምክንያቱም ዘመኑ ተሻሽሏልና››
☄〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️☄
ስማኝ ጎበዝ! .. እሳቸው ሳያስቡት በዚህ መልኩ የአይዶሎጂውን መጤነት መስክረዋል፡፡ አይዶሎጂው ወደ ሀገራችን የገባበትን 30 ዓመት ሊለጥጡት ቢታገሉም ከ50 ዓመት በላይ ግን ሊለጠጥላቸው አልቻለም፡፡ ደግሞ ዓቂዳና ተውሒድም ያረጃል፣ ይሞታል ከዚያም በአዲስና በዘመናዊ ዐቂዳ ይተካል እያሉህ ነው፡፡ ወደፊት የወሓቢያንም ዓቂዳ አርጅቷል ብለውህ ሌላ የዘመነ ዐቂዳ ይዘውልህ እንደሚመጡ እርግጠኛ ሁን፡፡ አትጠራጠር😊
2️⃣. የ‹‹ነሕው›› (የዐረብኛ ሰዋሰው grammer) የስሕትት ብዛት፡፡ እሳቸው በዕድሜ ትልቅ በመሆናቸው እና ለተከታዮቻቸው ሞራል ስል ይህን ማለት አልፈልግም ነበር፡፡ ግን ቪደዮው ላይ ሒስ ካቀረብኩ አይቀር ሁሉንም መዳሰስ ስላለብኝ ነው፡፡ ዐረብኛን በወጉ ሳይረዱ ቁርአንን፣ ሐዲስንም ሆነ የሰለፎችን ትክክለኛ አስተሳሰብ መረዳት አዳጋች ነው፡፡ ከዚህች ቆርጬ ካወጣኋት 1 ደቂዳ ከ25 ሰከንድ ከምትፈጅድ እጅግ አጭር ቨዲዮ ውስጥ ከ5 የማያንሱ ተራ የዐረብኛ ሰዋሰው (grammer) ስሕተቶችን ከእሳቸው ላይ ማግኘት ይደንቃል፡፡ ደግሞ እሳቸው በዚህች አንዲት ደቂቃ ከ25 ሰከንድ ውስጥ የፈፀሟቸው የስሕተት ብዛት እኮ ገና የዐረብኛን ግራመር ሀሁ አንድ ብሎ (ትንሿን ‹አጀሩምያ› የተሰኘችውን የሰዋሰው ኪታብ) የቀራ ጀማሪ ደረሳ እንኳ ለሰዓታት ዐረብኛን ቢያነብ ወይም ቢናገር የማይፈፅማቸው ተራ ስሕተቶች ናቸው፡፡ በዚህ 4ለ4 ውይይት ላይ ከሳቸው ትይዩ የተቀመጡ የዐረብኛን ቋንቋ ዘርፎችን ጥንቅቅ አድርገው ያወቁ እና ቋንቋውን በየዘርፉ አገላብጠውና አኝከው የቀሩና እንደ ውሃ የጠጡ .. ሙፍቲን እና ሸኽ ሙሐመድ ሶብዩን .. የመሳሰሉ ዑለሞች፤ በሸኽ ጀይላን ተራ የግራመር ስሕተት ምን ያህል እንደሚጨናነቁ አሰብኩት፡፡ ለመናገርም አፍረው ዝም ብለው ይሆናል፡፡ እኛ ጃሂሎቹም ዑለሞቻችን ሐሳብ ይስጡበት ብለን ነበር ሐያእ አድርገን እስከዛሬ ዝም ብለን የቆየነው፡፡
((ይህን አስመልክቶ ከዚህ በላይ ብዙ ማለት አልፈልግም፡፡ ‹ሐሰት ነው› .. የምትሉ ወሃቢዮች ካላችሁ በሌላ ፖስት የሰዋሰው ስሕተቱን አንድ በአንድ አውጥቼ ላሳያችሁ ዝግጁ ነኝ፡፡ ያልቀነጨብኩትን የቀረውን ቪዲዮ ከጨመርኩ ደግሞ የስሕተቱ መዓት ስንት ሊደርስ እንደሚችል ገምቱ))
3️⃣. ሸኽ ጀይላን እራሳቸው ከ50 ዓመት በፊት 3 የአሽዓሪያ ዐቂዳን የሚያስተምሩ ኪታቦችን እንደቀሩ ገልፀዋል፡፡ በዚህም የተነሳ ሁሉንም ዓይነት ዒልም አካተው እና ሰብስበው እንደተማሩና እንዳካበቱ በኩራት ይገልፃሉ፡፡ ‹‹ጉራ አይደለም!›› ብለውም ያክላሉ፡፡ እሳቸው ‹‹ቀርቻቸዋለሁ›› ብለው የጠቀሷቸው 3 የዐቂዳ ኪታቦች ግን ገና ጀማሪ የዐቂዳ ተማሪ የሆነ ፍሬሽ ደረሳ የሚቀራቸው፣ በግጥም መልክ የተፃፉ እና እያንዳንዳቸው ጥቂት ስንኞችን የያዙ ፓምፍሌቶች ናቸው፡፡ ይህን ያህል .. ‹‹ሁሉንም አውቄያለሁ›› .. የሚያስብሉ አይደሉም፡፡ ባይገርማችሁ ዑለሞቻችን ቀርቶ ወጣት ደረሶቻችን እንኳ የእነዚህን 3 ኪታቦች እጅግ ረዣዥም ሸርሖች (ትንታኔዎች) በዓይነት ዓይነታቸው በመቅራትና ሌሎችንም ሰፋፊ ኪታቦችን በማከል እሳቸው ከሚሉት የትናየት አልፈው ሄደዋል መሰላችሁ፡፡
ሸኽ ጀይላን ሲናገሩ እንዲህ ይላሉ፡👇
☄〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️☄
👉 ‹‹አዎ በእርግጥ ከ50 አመት በፊት ‹አስ-ሰኑሲያ› (የተባለው የአሽዓሪያ ዐቂዳ ኪታብ) በሀገራችን ይቀራ ነበር፡፡ እኔም ይህን ኪታብ ከቀሩት ውስጥ ነኝ፡፡ ‹በድኡል-አማሊ› እና ‹ጀውሃራ› (የተባሉትን የአሽዓሪያ) ኪታቦችን ከቀሩት ውስጥ ነኝ፡፡ አውቃቸዋለሁ፡፡ እኛ ሁሉንም ዕውቀቶች አካተናል፡፡ አልሓምዱሊላህ፡፡ ጉራ አይደለም፡፡ የጥንቱን (የዐቂዳ) ዕውቀቶች እና ዘመናዊ (የዐቂዳ) ዕውቀቶችንም አካተናል፡፡ (እንዳልኳችሁ) እነዚህን ኪታቦች ቀርተናል፡፡››