♥♥ሀያቱና ሁቡ ሙሀመድ++


Kanal geosi va tili: Efiopiya, Amharcha
Toifa: ko‘rsatilmagan


👇👇👇👇👇👇👇
አትገፍሉ መገፈል የለም
ቀብር ከገቡ መመለስ የለም
…ያሸምሰል አለም አሰላማለይክ
♥♥♥👏👏👏👏👏👏👏👏
ነቢ ስል ውዬ ነቢ ስል ባድር
ለኔ ደስታ ነው ለነፍሴ
Lemangnawm asteyayet
@abubeker

Связанные каналы

Kanal geosi va tili
Efiopiya, Amharcha
Toifa
ko‘rsatilmagan
Statistika
Postlar filtri


ያሲራጀል አለም dan repost
#የሸሂዶች ሃገር ኢትዮጲያ

ሸሂድነት ከ ሚነላህ መታደልን ይጠይቃል
ወንድማችን አላህ በሰፊው ጀነቱ ያብስርህ
አል ፋቲሃ




▫️▫️💥ትክክለኛው መረጃ💥
💥የትላንቱ የቤተ-መንግስት ስብሰባ💥

ወሃቢዮቹ ትላንት በሶሻል ሚዲያ መንጋቸውን ለማጃጃልና በመንጋቸው አዕምሮ ላይ እንደለመዱት ለመሳለቅ ሲያራግቡት የነበረው ነገር በሙሉ ሐሰት ነው፡፡ ሰው ተሳስቶ እንኳ 1 ዕውነት አያወራም እንዴ?! ለናሙና አንድ ዕውነት እንኳ አላገኘሁበትም፡፡

ለምሳሌ፡👇

1️⃣. ተቀዳሚ ሙፍቲ እና ‹ኢብኑ ቱፋ› ፌደራል መጅሊስን በጋራ ይምሩ ተብሏል ብለው ወሃቢዮቹ ትላንት ሲያራግቡት የነበረው ፍፁም ሐሰት ነው፡፡

2️⃣. በቀጣዩ የዒድ አል-አድሓ ሶላት ላይ በአ.አ. እስታዲየም ሙፍቲ በንግግር ከፍተው ‹ኢብኑ ቱፋ› በዱዓ ይዘጉታል ብለው ወሃቢዮቹ ሚያናፍሱትም ውሸት ነው፡፡

3️⃣. አቶ ሱልጣን አማን የታሸገው የአዲስ አበባ መጅሊስ ቢሮ እንዲከፈትላቸው ጠይቀው በቅርቡ እንደሚከፈትላቸው ቃል ተገብቶላቸዋል ብለው ወሃቢዮቹ ሚያናፍሱትም ፍፁም ቅጥፈት ነው፡፡

4️⃣. ሙፍቲን በየቀኑ አውርጃለሁ ብሎ ሲሰበሰብ የነበረው 25 “ዑለሞችን” የያዘው “ጠቅላላ ጉባኤ” እንዲመለስ ተወስኗል ብለው ወሃቢዮቹ ሚያራግቡትም ከዕውነት የራቀ ሐሰት ነው፡፡

5️⃣. ከዛሬ 3 ዓመት በፊት የ479 ሑጃጅ 40 ሚሊየን ብር የሚጠጋን ገንዘብ ቁርጥም-አድርጎ የበላው የወሃቢያ አካል የሆነው ቦርድ ወደ ስራው እንዲመለስ ተወስኗል ብለው ወሃቢዮቹ የሚፈበርኩት ፊልምም ምናልባት በሕንዱ Bollywood ካልሆነ በስተቀር በአሜሪካው Hollywood ሊሰራ የማይችል ቅዠት ነው፡፡

6️⃣. ጠ/ሚ. ዐብይ የአንዋር መስጂዱን ኢማም ሰዪድ ሸኽ ጧሃን እንዲህ አሉ፤ እከሌን እንዲህ አሉ .. ወዘተ … እያሉ ወሃቢዮቹ መንጋቸውን የሚያስጨፍሩበትም ምኞት ቢሆን ያስጨበጨበ ተረት-ተረት ነው፡፡

💥ትክክለኛውስ መረጃ የቱ ነው?💥

ከላይ እንደገለፅኩላችሁ ወሃቢዮች የትላንቱን የቤተ-መንግስት ስብሰባን በተመለከተ የሚያራግቡት በሙሉ ሐሰት ነው፡፡ እንዲያውም እራሳቸው ከፍተኛ ውርደትን እና ቅሌትን የተከናነቡበት ስብሰባ ነበር፡፡ ለዚህም ነው መንጋቸው እንዳያፈነግጥባቸው እንደለመዱት ሐሰት ከመፈብረክ ውጪ ሌላ አማራጭ ያላገኙት፡፡

ጠ/ሚ ዶ/ር ዐብይ ወሃቢዮች ከመጅሊስ ተገንጥለው መውጣታቸውን እና ሌሎችንም እስከዛሬ ሲፈፅሙት የነበረውን ወንጀል በሙሉ ህገ-ወጥ እንደሆነ በግልፅ ቋንቋ ነው የነገሯቸው፡፡

ጠ/ሚ ዐብይ እንዲህ ነበር ያሏቸው፡👇

👉 ‹‹ይህን ሁሉ ሕገ-ወጥ ተግባር ስትፈፅሙ እኛ አውቀን ነው አይተን እንዳላየ ዝም ያልናችሁ፡፡ ሴራው ሳይገባን ቀርቶ አይደለም፡፡ ደሞ በየጓዳው ተደብቃችሁ መንግስት ህግ አያስከብርም ብላችሁ ታሙናላችሁ፡፡ እኛ እርምጃ መውሰድ እና ህግ ማስከበር ጠፍቶን ወይም አቅቶን አይደለም ዝም ያልነው፡፡ እናንተ የሃይማኖት አባቶች ናችሁ ብለን ነው እስኪ ትንሽ እንያቸው በሚል ዝም ያልናችሁ፡፡ ከአሁን በኋላ እኛ በምንላችሁ መስመር ካልሄዳችሁ ግን ህግ እንዴት እንደምናስከብር እናሳያችኋለን››

በዚህ መልኩ በአብዛኛው የወሃቢዮቹን ትዕቢት የሚያጋልጥ፣ ወሃቢዮቹን አፍ የሚያስይዝ እና አንገት የሚያስደፋ ንግግር በውይይቱ ላይ ከተናገሩ በኋላ እና ተሳታፊዎችን ጨምሮ ሐሳቦችን ካንሸራሸሩ በኋላ የሚከተሉት ውሳኔዎች ተላልፈዋል፡ 👇

1️⃣. በሙፍቲ የሚመራው ህጋዊው መጅሊስ (በሙፍቲ መሪነት ብቻ) አሁን ባለበት ይቀጥል፡፡

2️⃣. አቶ ሱልጣን በበኩላቸው .. ‹‹እንደምታዩት አሁን በዓል ደርሷል ነገር ግን የአ.አ. መጅሊስ በመታሸጉ የተነሳ ለመጅሊሱ ሰራተኞች ደሞዝ መክፈል አልቻልንም›› .. የሚል ቅሬታ ሲያቀርቡ፤ ቢሮው ለሚቀጥሉት 10 ቀናት ብቻ ለሰራተኞች ደሞዝ ለመክፈል እንዲከፈት እና ከ10 ቀን በኋላ ዳግም እንዲታሸግ ተወስኗል፡፡ ደግሞ 10 ቀኑንም ቢሆን ልክ በፊት እንደነበረው አቶ ሱልጣን ዋና ፕሬዝደንት እና ሸኽ ዓሊ ሙሐመድም ም/ፕሬዝደንት ሆነው የወሃቢያውም የሱፊያውም አባላት ሁሉም የቀድሞ ቦታቸውን ይዘው እኩል ቢሮ ገብተው በጋራ ደሞዝ ከፍለው ከ10 ቀን በኋላ እንዲታሸግ ነው የተወሰነው፡፡

3️⃣. ከ4 ዓመት በፊት የአሁኑን መጅሊስ ያዋቀሩት ከ300 እስከ 400 የሚጠጉ ዑለሞች ከዐረፋ በኋላ ባሉት 10 ቀናት ውስጥ በሙፍቲ የበላይነት ከየገጠሩ ተጠርተው መጥተው (የወሃቢያው ቡድን አልወያይበትም ብሎ ወርውሮት የወጣውን) የመጅሊሱን ረቂቅ ህገ-ደንብ ዑለሞቹ እና መሻኢኾቹ በጥልቀት እንዲወያዩበትና እንዲመረምሩት ተወስኗል፡፡

4️⃣. ከዚያም እነዚህ ዑለሞች በተወያዩት መሰረትና መርምረውት የተስማሙበትን ውጤት መሰረት አድርገው የፌደራል መጅሊስን ፕሬዝደንት እና ዋና ፀሐፊውን እንዲሰይሙ ተወስኗል፡፡

5️⃣. በዚህ በትላንቱ በቤተ-መንግስት ስብሰባ ላይ የተገኙትን የመንግስት ባለሥልጣናትን እና የፖሊስ እና የፀጥታ ኃላፊዎችን.. ‹‹እከሌ ከእንገዲህ ይህን ታስፈፅማለህ›› .. እያሉ ዶ/ር ዐብይ አፅንኦት ለመስጠት የያንዳንዳቸውን ባለሥልጣናት ስም በየተራ እየጠሩ ይህን ውሳኔ እንዲያስፈፅሙ ጥብቅ ትዕዛዝ ሰጥተዋል፡፡

6️⃣. የፊታችንን የዒደል-አድሓ የዒድ ሶላትን በተመለከተ ክቡር ተቀዳሚ ሙፍቲ የመክፈቻ ንግግር እንዲያደርጉ ከጠ/ሚ ዶ/ር ዐብይ ጥያቄ ቢቀርብላቸውም ሙፍቲ ግን .. ‹‹በጭራሽ አላደርግም›› .. ብለው እንቢ አሉ፡፡ ጠ/ሚ ዐብይ ለሙፍቲ .. ‹‹እሺ ዱዓ እንኳ አድርጉ›› .. ሲሏቸው ሙፍቲ ደግሞ .. ‹‹በጭራሽ ዱዓም ሆነ ንግግር አላደርግም›› .. አሉ፡፡ በዚህ የተነሳ በዒድ ዕለት የብልፅግና ፓርቲ ም/ፕሬዝደንት አቶ አደም ፋራሕን ጨምሮ ሁለት ከመንግስት የተወከሉ ሰዎች ብቻ በወቅታዊ የሀገሪቷ ጉዳይ ዙሪያ ንግግር እንዲያደርጉ እና ሌላ ማንም ሰው ንግግር እንዳያደርግ ተወስኗል፡፡

7️⃣. በመጨረሻም ጠ/ሚ ዐብይ እንዲህ አሉ፡👇

👉 ‹‹በእነዚህ በተወሰኑት ውሳኔዎች መሰረት የማትስማሙ ከሆነና መፍትሔ ላይ የማትደርሱ ከሆነ ግን የመጅሊሱን ቁልፍ ከ4 ዓመት በፊት የነበረው የቀድሞው መጅሊስ ፕሬዝደንት ለነበሩት ለሸኽ ሙሐመድ አሚን ጀማል ቁልፉን አስረክባቸው እና የቀድሞው መጅሊስ ይመለሳል›› .. በማለት ኮስተር ብለው ይህን ተናግረው ብድግ ብለው ተነስተው ሄዱ፡፡

ስብሰባውም በዚህ ተቋጨ፡፡ ዕውነታው እንግዲህ ይህ ነው።


ከነጃሺ ኢስላማዊ ማህበር ( ከአ/አ ሙስሊም ወጣቶች ማህበር ) የተላለፈ መልዕክት
ህልውናችን በትግላችን ይፀናል !!

ሚያዝያ 23/2011 በተቀመረ ሴራ የሰለፊ/ወሃቢ ቡድን መጅሊስ ውስጥ መግባቱ የታወቃል። ከዚህ ጊዜ ጀምሮ ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች ብዙ ሁከት በየመሳጂዱ አስተናግደዋል። አዲስ አበባ መጅሊስን እንዲመራ በተቀዳሚ ሙፍቲ ደብዳቤ የተሾመው ሱልጣን አማን አዲስ አበባ መጅሊስን ከረገጠበት ቀን አንስቶ ነባሩ ሙስሊም ማህበረሰብ ለዘመናት ደምና አጥንት ከፍሎ የገነባቸው ከ60 በላይ መሳጂዶችን በመንጠቅ ለተደራጁ የወሃቢያ ቦዘኔዎች ለማስከብ በሚፅፋቸው ደብዳቤዎች በየመስጂዱ ብዙ ሁከቶች ተከስተዋል። ይህን ያስተዋለው ፌደራል መጅሊስ ባለፈው ሳምንት አቶ ሱልጣን አማን እና ሌሎች ሁከት ፈጣሪ የወሃቢያ አመራሮች ከሹመት መነሳታቸውን የሚገልፅ ደብዳቤ ፃፈላቸው።

ሰኔ 18/2014 ከጠዋቱ 12 ሰአት ከሥራ ሰአት ውጭ አቶ ሱልጣን አማን እና ግብረ አበሮቹ ፌደራል መጅሊስ ከሹመታቸው እንዲነሱ የፃፈው ደብዳቤ ተግበራዊ ሊሆንብን ነው ሳንቀደም እንቅደም ብለው የመጅሊሱን ቋሚ ዘበኞች በመደብደብ እና ወደ ፎቁ የሚያስወጣውን በር በመስበር የውንብድና ተግባር ፈፅመው ጥበቃዎቹን አባርረው ከ20 በላይ ቦዘኔዎችን ለጥበቃ በሚል ሽፋን መጅሊሱ ጊቢ ውስጥ ውለው እንዲያድሩ መቀለብ ጀመረ። የአዲስ አበባ መጅሊስ ምክትል ፕሬዝደንት ሸህ ዓሊ እና የቦርድ ፀሀፊው ቶፊቅ ወደ ቢሮ ሊገቡ ሲል አቶ ሱልጣን ያደራጃቸው ወንበዴዎች እንዳይገቡ ከለከሉ። ይህ ሁሉ ሲሆን በአካባቢው ያለው የጸጥታ አካል ሙሉ መረጃው እያለው እርምጃ እንዲወስድም እየተጠየቀ ዝምታን መረጠ።

ትላንት ሰኔ 23/2014 ሸህ ዓሊ ወደ ቢሮ ለመግባት ለምን ተከለከሉ ብለው የተቆጡ ኢማሞችና ወጣቶች ሸህ ዓሊን አጅበው ወደ ቢሮ ለማስገባት አዲስ አበባ መጅሊስ ጊቢ ውስጥ ቢገኙም አቶ ሱልጣን ያደራጃቸው ወንበዴዎች ድንጋይ መወርወር እና ሚስማር ባለው ዱላ ጥቃት ማድረስ ጀመሩ ሁከት ተፈጠረ በመሀል ቦዘኔዎቹ ወደ ፎቅ በመውጣት ወደታች ድንጋይ ሲወረውሩ የቢሮ መስታወት ተሰበረ። ሁከት ቀስቃስሽ ድንጋይ ወርዋሪ ጥቃት አድራሽ መስታወት ሰባሪዎቹ የአቶ ሱልጣን ቦዘኔዎች ናቸው።

ከትላንት እስከዚህ ሰአት ድረስ ያለ ወንጀላቸው ታስረው ጣቢያ የሚገኙ ከ150 በላይ የሚሆኑ ሙስሊሞች እስካሁን ይፈታሉ በማለት ከፖሊስ መምሪያው የተለያዩ መሬት ያልረገጡ ሃሳቦችን እየሰማን በትእግስት እየጠበቅን የቆየን ቢሆንም ዛሬ ከረፋዱ ጀምሮ እስከ 8 ሰአት ድረስ ከ5 በላይ የሚሆኑ ዑለማኦች የጣቢያው ኃላፊን ቢያናግሩትም ኢማሞቹን እንጂ ወጣቶቹን አልለቅም፣ ወጣቶቹን ከለቀቅኩ ወሃብዮቹ ይጮሁብኛል ስማችንን ያጠፉታል ፍርድ ቤት ቀርበው ፍርድ ቤት በዋስ ይልቀቃቸው የሚል ደረቅ ምላሽ እንደሰጠ ለማወቅ ተችሏል። ከፍትህ ይልቅ የወሃቢያ ጩኸትና ስም ማጥፋት የሚፈራበት ፍትህ አልባ ወቅት ላይ ደርሰናል። እንደ ሀገር እጅግ ያሳዝናል።

በመሆኑም ለ1400 አመታት ደምና አጥንት ተከፍሎበት የቆየውን ነባሩን እስልምና ለማስቀጠል ሲሉ የታሰሩ ከ150 በላይ የሚሆኑ ወንድሞቻችን ታስረው እኛ በነፃነት ቤታችን ቁጭ ብለን ዝም እንደማንል የኢትዮጵያ ህዝብና መንግስት ሊያውቁት ይገባል። ከገጠር እስከ ከተማ ጫፍ ድረስ ያለው ህዝባችን የታሰሩ ወንድሞቻችንን ጉዳይ በትኩረት እየተከታተለው እና ምን እናግዝ እዘዙን ከእናንተ ጋር ነን እያለ ፍፁም የነቃ ዝግጁነት ላይ ይገኛል።

መንግስት ያለ ወንጀላቸው የታሰሩ ልጆቻችንን በአስቸኳይ እንዲፈታቸው እንጠይቃለን። የወሃቢያ ጩኸት ተፈርቶ ልጆቻችን በእስር እንዲማቅቁ ፈፅሞ አንፈቅድ


የዲን ወታደር ye din wetader dan repost
https://www.facebook.com/940301656169619/posts/pfbid0TfPQUehrRwADrYxTmTjBbP5YkJEjecvS6mrLPTrMqYa3QWQA3cg9gXYFT5FrrFSvl/
ተቀዳሚ ሙፍቲ ሚያዚያ 23 ሳይሆን ከ13 አመት በፊትም ለአንድነት ዋጋ የከፈሉ ዘምን አይሽሬ አሊም ናቸው!!!
**********^---->
ተቀዳሚ ሙፍቲ የሚሆን መስሏቸው፣ውሀብይ ወንድም ሆኖ የሚቀርብ መስሏቸው ሁሉም ተው እያላቸው ብቻቸውን ለአንድነት መድከም ከጀመሩ 16 አመት አልፏቸዋል።እነሱ ቢክዱ የራሳቸው ሰለፍያ ጋዜጣ እንዲህ ያስታውሰናል።

ሙፍቲ ያልተሸከሙት ግሳንግስ የለም፣ያልቻሉት ትችት የለም፣ያልፈነቀሉት ድንጋይ የለም፣የዚህ ሁሉ ልፋታቸው በሚያዚያ 23 ተቋጨ።ትንሽ ሳይቆዩ ግን በአንቱ ላይ ተረማምደን ተቋሙን ሽጡልን አሏቸው፣ያኔ ግን ሙፍቲ ቆም ብለው በቁጣ መለሱ፣ለዚህም ነው ኡለሞችን በተደጋጋሚ አውፉ በሉኝ እኔ መቸ እንዲህ መሰለኝ ሲሉ የሚሰሙት።

አሁንም አባታችን ሙፍቲ ሀጅ ኡመር የታላላቅ ኡለሞቸን፣ታሪኬን፣ተቋሜን አስልፌ አልሰጥም እንጅ ስለ ማንም እምነት ምንም ያሉት የለም።ግን ተቋም ሊቀሙበት የሄዱበት ርቀትና የማጭበርበሪያ ቴክኒኩ እጅግ የሚያበሳጭና ሱፍዩን በአንድነት አስተኝቶ፣እንደ ሀጅ ኑሩ አደም አይነት አስመሳዮችን ቀላቅሎ ተቋምንም ሱፍይነትንም አስረክቡን ወይንም ሽጡልን ያሉ ጊዜ ጨዋታው ፈረሰ።በቃ ይህ ነው እውነታው፣ለዚህ ነው የሙፍቲ መከዳት በአደባባይ የታወቀው

SHARE SHARE SHARE ያድርጉ
LIKE LIKE LIKE LIKE በማድረግ የእርስወን ድርሻ ለሌሎች በማዳረስ ይወጡ
#የፌስቡክ #ገጻችንን #የዲን #ወታደር #የሚለዉን #ይህንን👇🏿
https://m.facebook.com/yedinwetader
በመንካት ገብተዉ #LIKE #ያድርጉ

በቴሌግራም ይከታተሉን
https://t.me/joinchat/AAAAAFlZ0HCkBTtYs5KqDA
#እኔ_ኡለሞቸን_ተቋሜን_መስጅዴን_የምጠብቀው_ጀግናው_የሙፍቲ_ትውልድ_ነኝ


ታቢዒዩ ሐጃጅ ቢን ሐሳን :

" ሰሐብዩ አነስ ቢን ማሊክ ረ.ዐ. ጋር ነበር.. የሰይዳችንን ﷺ ውሀ የሚጠጡባት እቃን እንዲመጣ አዘዙ .. ውሀም ተደረገልንና በዛች እቃ ጠጣን ፊታችንም ጭንቃላታችንም ላይ አፈሰስን .. ነብያችንም ﷺ ላይ ሰለዋት አወረድን .."

📗ሙስነድ ኢማም አህመድ : 20/277

።።።።።።።።።።።።።።

ሰይዳችን ﷺ ወደ አኼራ ከሄዱ ቡሀላ ነው ይሄን የሚያደርጉት .. እሳቸው የሚጠጡበትን እቃ በክብር ከተቀመጠበት አውጥተው በፍቅር በናፍቆት በመሀባ ውሀ ይጠጡበታል ፣ ሰለዋት ያወርዳሉ ፣ ሰይዳችንን ﷺ ይናፍቃሉ ..

ይሄን የሚያደርጉት በረካቸውን ከጅለው አይደለምን ?!

https://t.me/mededulhabib


ጭራሽ ከሒጅራ አቆጣጠር ከ700 ዓመታት በኋላ የመጡ አፈንጋጭ ሐሳቦችን ያራምዱ የነበሩ 2 ሰዎችን እና ከሂጅራ አቆጣጠር ከ1150 ዓመታት በኋላ መጥቶ በእነዚህ 2ቱ ሰዎች አፈንጋጭ አስተሳሰብ ላይ በመመርኮዝ የወሃቢያን አንጃ ከመሰረተ በኋላ በመቶ ሺ የሚቆጠሩ ሙስሊሞችን «ከፍራቹሃል» ብሎ ያረደን 1 ግለሰብ ነበር፡፡ እሱ አርዓያ አድርጎ የተከተላቸው 2ቱ ሰዎች በዘመናቸው አፈንጋጭና ፅንፈኛ አስተሳሰብ በማራመዳቸው የተነሳ ከዘመናቸው ዑለሞች እና ከማህበረሰቡ ተገልለው የኖሩ ናቸው፡፡ በተለይ ኢብኑ ተይሚያህን በዚህ ከሸሪዓ ያፈነገጠ ፅንፈኛ አስተሳሰቡ የተነሳ የዘመኑ ዑለሞች እና የዘመኑ የሙስሊሞች መሪ በተደጋጋሚ አስረውት ነበር፡፡ እንግዲህ ወሃቢዮቹ በመጅሊስ ሰነድ ውስጥ እንዲካተቱላቸው የጠየቁት እነዚህ 2 ሰዎች ከሞቱ ከ5 መቶ ዓመታት በኋላ መጥቶ የእነሱን የተዳፈነ አፈንጋጭ አስተሳሰብን ከተቀበረበት ቆፍሮ በማውጣትና አቧራውን በማራገፍ ከእነሱ የከፉ ሐሳቦችን ጨምሮበት በሙስሊሞች ላይ ሽብርተኝነትን ያወጀውን ሙሐመድ ኢብኑ ዐብዱል-ወሃብንና እሱ ሚከተላቸውን እነዚህን 2ቱን ሰዎች ነው ወሃቢዮቹ በመጅሊስ ሰነድ ውስጥ እንዲካተቱላቸው የጠየቁት፡፡

እስኪ አስተንትኑ🤔 .. ‹‹እኛ የምንከተለው ሰለፎችን ነውና በሰለፎች ዘመን የነበሩ 2 ሰለፎች በመጅሊስ ሰነድ ውስጥ ይካተቱልን›› .. የሚለው ወገን ነው ትክክለኛው ሰለፎችን የሚከተል? .. ወይስ .. ‹‹ከሰለፎች ዘመን ከ700 ዓመታት በኋላ እና ከ1150 ዓመታት በኋላ የመጡ 3 ሰዎችን ነው ምንከተለውና እነሱ በሰነዱ ይካተቱልን›› .. የሚለው ወገን ነው ሰለፍን የሚከተል? .. 👉 መቸም ንፁህ ልቦና ላለው መልሱ ግልፅ ነው፡፡

እንግዲህ ከዚህ በላይ የወሃቢያው ቡድን ሴራና ምንነት ሊጋለጥ አይችልም፡፡ ይህን የተፍረጠረጠ ሐቅ በዓይኑ ተመልክቶና በጆሮው ሰምቶ የማይረዳና የማያገናዝብ የመንጋው አባል ካለ የእሱ ጉዳይ ‹‹ሸቃዋ›› ነውና ወደ «ሰዓዳ» ይለወጥለት ዘንድ ለኃያሉ አላህ ይዋደቅ፤ ያልቅስ፡፡

በመረሻም👇

وَقُلْ جَآءَ ٱلْحَقُّ وَزَهَقَ ٱلْبَٰطِلُ ۚ إِنَّ ٱلْبَٰ


ብለህ መጅሊስ ብቻ ግባ›› ነው😅

እሳቸው ቃል-በቃል ሲናገሩ እንዲህ ነበር ያሉት፡👇

☄〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️☄
👉 ‹‹እነዚህ (የአሽዓሪያ) ኪታቦች በሙሉ ለዚህ ዘመን አይበጁም፡፡ ምክንያቱም ዘመኑ ተሻሽሏልና፡፡ (እነዚህን የአሽዓሪያ ዐቂዳዎችን እንከተል የሚል ሰው) ልክ በአህያ እና በበቅሎ እንሄዳለን እንጂ በመኪና እና በአውሮፕላን አንሳፈርም እንደሚል ዓይነት ሰው ነው፡፡ (ከ50 ዓመት በፊት ወደነበረው) ጊዜ-ወዳለፈበት (የአሽዓሪያ ዐቂዳ) ታሪክ መመለስ የሚፈልግ ሰው ‹መደመር›ን አይፈልግም ማለት፡፡ ዶ/ር ዐብይ ‹ሐፊዘሁላሁ ወሃዳሁ› ያወጀውን ‹መደመር›ን አልፈልግም የሚል ሰው ነው ወደ ኋላ እና ከ50 ዓመት በፊት ወደነበረው እንመለስ የሚለው››
☄〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️☄

በዓለም ላይ 95 ከመቶ የሚሆኑት ዑለሞችና ተከታዮቻቸቸው የሚከተሉትን የአህለሱናን ዐቂዳ ለማጣጣል የቀረቡ እነዚህን የአህያ😀 እና የበቅሎ😀 ምሳሌዎችን እና የ‹መደመር› ማስፈራሪያዎችን ከሳቸው አንደበት ሰምቶ ከት ብሎ መሳቅ ያልቻለ ወሃቢይ ካለ እውነትም ከልቡ ወሃቢይ ነው!😅

5️⃣. ሸኽ ጀይላን በዚህ ቪዲዮ ላይ እንደሚገልፁት፤ የኢትዮጵያ ሙስሊም አብዛኛው ከዛሬ 50 ዓመት ጀምሮ ቀስ በቀስ ወደ ወሃቢይነት እንደተቀየረ እና ዛሬ ላይ አሽዓሪያዎች ጥቂቶች እንደሆኑ ይናገራሉ😊 ይህ እንግዲህ ዕውነታ ሳይሆን የእሳቸው ምኞት ነው😉 ዋናው ጉዳይ ግን 👉 እሳቸው እና ተከታዮቻቸው የሆኑ ወሃቢዮች የሚከተሉት ቁርአንን እና ሐዲስን ሳይሆን የወሃቢያ ቡድን መስራች የሆነውን 👉 ሙሐመድ ኢብኑ ዐብዱልወሃብን መሆኑን ማመናቸው ነው👍

በጣም ደስ የሚለው .. ‹‹እኛ ወሃቢዮች አይደለንም፤ ሙስሊሞች ነን፤ ሁላችም አንድ ነን፤ የምንከተለውም ቁርአንን እና ሐዲስን ብቻ ነው›› .. የሚለው የወሃቢዮች የዘወትር ማስተኛና ማደናገሪያ መዝሙር የወጣለት ቅጥፈት መሆኑን የቡድኑ አውራ ሸኽ ጀይላን በሚገርም አገላለፅ ምስክርነት ሰጥተዋል፡፡ እጃቸውን እና ሌባ ጣታቸውን እያወራጩ እና እያስጠነቀቁም በሚመስል መልኩ ነው ቃላትን ጫን እያሉ በመናገር ኮስተር ብለው ይህን አጥብቀው ሚገልፁት😀

ይህን በተመለከተ ቪዲዮው ላይ ቃል በቃል እንዲህ ይላሉ፡👇

☄〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️☄
👉 ‹‹በአሁኑ ወቅት የዚህች ሀገር አብዛኛው ሕዝብ ‹አቡል-ሐሰን አል-አሽዓሪ›ን አይደለም ሚከተለው፡፡ አብዛኛው ሕዝብ የሚከተለው (የወሃቢያውን መስራች) ‹ሸኽ ሙሐመድ ኢብኑ ዐብዱል-ወሃብ›ን ነው፡፡ ዕውነታውን የግድ ልናውቅ ይገባል››
☄〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️☄

ባሻዬ! .. ሸኽ ጀይላን እና የሀገራችን ወሃቢዮች የሚከተሉት የወሃቢያ መስራች የሆነውን ሙሐመድ ኢብኑ ዐብዱል-ወሃብን እና የዛሬ 30 ዓመት ወደ ሀገራችን የገባውን መጤውን የወሃቢያ አይዶሎጂን እንደሆነ ከእሳቸው በላይ ማን መጥቶ ኮስተር ብሎ እያስጠነቀቀ ጭምር ሊንግርህ ትፈልጋለህ?!😀

በዚህ 4ለ4 ውይይት ላይ እነ ኡስታዝ ሐሰን ታጁ ከዑለሞቻችን ተርታ ተሰልፈው ኪታብ ይዘው ወሃቢዮቹን በማስረጃ እርቃናቸውን ሲያስቀሩ .. ለተወያዮቹ ሻይ ያፈሉ የነበሩትና ከኋላ ኩርምት ብለው እንደ ጩጬ ልጅ ያዳምጡ የነበሩት .. አሕመዲን ጀበል እና አቡበከር አሕመድ .. ለምን ሸኽ ጀይላን ይህን ሲሉ ሰምተው ተስማሙ?! .. ለምንስ ሁሌም እንደሚፎግሩን .. ‹‹እኛ ምንከተለው ቁርአንን፣ ሐዲስን እና ሰለፎችን ነው፡፡ ወሃቢዮች አይደለንም›› .. ለምን አላሉም?! .. መልሱ ቀላል ነው፡፡ ሐሳቡን ስለሚደግፉት እና ስለተመቻቸው ነው፡፡ ረዥሙን ቪዲዮ ደብቀውት የቀሩትም ከዚህ በላይ ብዙ ሚስጥር እንዳይወጣባቸው ሰግተው ነው፡፡

መንጋው ሆይ! .. ሸኽ ጀይላን እና ወሃቢዮቹ የሚከተሉት ከዛሬ 250 ዓመት ወዲህ በሳውዲ የተፈለሰፈውን እና የዛሬ 30 ዓመት ገደማ ወደ ሀገራችን የገባውን መጤውን የወሃቢያ አይዶሎጂን እና የአይዶሎጂውን መስራች ኢብኑ ዐብዱል-ወሃብን መሆኑን ሸኽ ጀይላን በአንደበታቸው ሲናገሩ በድምፅና በቪዲዮ አሰምቼሃለሁ፡፡ ከእንግዲህ ስለወሃቢያ ስንፅፍ አንተ ከወሃቢያው ቁንጮ ከሸኽ ጀይላን በልጠህ መጥተህ .. ‹‹አትከፋፍሉን! ወሃቢዮች አይደለንም! ሙስሊሞች ነን! ምንትሴ›› .. እላለሁ ብትል ከመቀፅፈት በብሎክ ቀስት ነው ማስወግድህ!

6️⃣. ወሃቢዮቹ ሁሌም .. ‹‹በዐቂዳ ቁርአንን፣ ሐዲስንና ሰለፎችን ነው ምንከተለው›› .. ብለው እኛን ሊፎግሩን እንደሚሞክሩት ሳይሆን በትክክል የሚከተሉት ከዛሬ 250 አመት ወዲህ ተፈልስፎ የዛሬ 30 ዓመት ገደማ ወደ ሀገራችን የገባውን የወሃቢያን ፅንፈኛ አይዶሎጂ እና ፈልሳፊውን ሙሐመድ ኢብኑ ዐብዱልወሃብን መሆኑን ከላይ በተራ ቁጥር 5️⃣ ላይ እንዳስተዋላችሁት የቡድኑ አውራ ሸኽ ጀይላን አረጋግጠዋል፡፡ ወሃቢዮቹ .. ‹‹ሁላችንም አንድ ነን! ወሃቢያ የሚባል ነገር የለም! ሁላችንም ሙስሊሞች ነን!›› .. እያሉ ሲፎግሩን ይኖሩና ልክ እንደ 👉 4ለ4ቱ ውይይት ዓይነት አጣብቂኝ ውስጥ ሲገቡ እንዲሁም ጉዳዩ የሚናፍቁት የመጅሊስ ሥልጣን ጉዳይ ሲሆንባቸው በልባቸው ደብቀው የኖሩትን አውጥተው ሐቅ ሐቁን ይናገራሉ፡፡ ምክንያቱም አማራጭ የላቸውማ፡፡

እጅግ የሚገርመው ደግሞ የኛ መሻኢኾች በመጅሊስ ሰነድ ውስጥ .. የአሽዓሪያ/ማቱሪዲያ .. ዓቂዳ ይካተት ብለው ሲጠይቁ ወሃቢዮች ግን .. ‹‹ቁርአን፣ ሐዲስ እና ሰለፎች›› .. ይካተቱ አላሉም፡፡ ምክንያቱም ወሃቢዮቹ እነዚህን ስሞች ለመነገጃነት ብቻ ነው ሚጠቀሙባቸዋ፡፡ በትክክል የሚከተሉት የወሃቢያውን መስራች ኢብኑ ዐብዱልወሃብን ነውና፡፡

እስኪ የወሃቢያው ቡድን ቁንጮ የሆኑት ሸኽ ጀይላን በመጅሊሱ ሰነድ ውስጥ ማን ይካተትልን እንዳሉ እንደሚከተለው ንግግራቸውን ቃል በቃል ተመልከቱና ተገረሙ፡👇

☄〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️☄
👉 ‹‹በመጅሊስ ሰነድ ውስጥ አሽዓሪያን እና “አቡ-መንሱር አል-ማቱሪዲ”ን መጨመር ከፈለግን እኛም ደግሞ በበኩላችን ‹ሸይኹል-ኢስላም ኢብኑ-ተይሚያህ›፣ ‹ሸይኹል-ኢስላም ኢብኑል-ቀዪም› እና (የወሃቢያው መስራች) ‹ሸኽ ሙሐመድ ኢብኑ ዐብዱል-ወሃብ› በሰነዱ ውስጥ ይጨመሩልን እንላለን፡፡ ምክንያቱም በአሁኑ ወቅት የዚህች ሀገር አብዛኛው ሕዝብ ‹አቡል-ሐሰን አል-አሽዓሪ›ን አይደለም ሚከተለው፡፡ አብዛኛው ሕዝብ የሚከተለው (የወሃቢያውን መስራች) ‹ሸኽ ሙሐመድ ኢብኑ ዐብዱል-ወሃብ›ን ነው፡፡ ዕውነታውን የግድ ልናውቅ ይገባል››
☄〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️☄

እንግዲህ አህለ-ሱና የሆኑት መሻኢኾቻችን በመጅሊስ ሰነድ ውስጥ እንዲካተቱላቸው የጠየቁት ሰለፍ የሆኑትን .. ‹‹አቡል-ሐሰን አል-አሽዓሪ››ን .. እና .. ሰለፍ የሆኑትን .. ‹‹አቡ-መንሱር አልማቱሪዲ››ን .. ሲሆኑ፤ ወሃቢዮቹ ግን በቪዲዮው እንደሰማችሁት በምትኩ እንዲካተትላቸው የጠየቁት አንድም ሶሓባም ሆነ አንድም ሰለፍ አልነበረም፡፡ ወሃቢዮቹ በመጅሊስ ሰነድ ውስጥ እንዲካተቱላቸው የጠየቁት .. ሰለፎች ሊሆኑ ይቅርና ..


ወደ ንግግራቸው ስንዘልቅ ለምሳሌ፡- እሳቸው ‹‹ጀውሀራ›› ብለው የጠቀሱት ‹‹ጀውሀረቱ ተውሒድ›› የተሰኘው የአሽዓሪያ ዐቂዳ ኪታብ 144 ስንኞችን ብቻ የያዘ ትንሽዬ የግጥም ፓምፍሌት ነው፡፡ የተካበደ አይደለም፡፡ ‹‹በድኡል-አማሊ›› የተሰኘው የዐቂዳ ኪታብም 66 ስንኞችን ብቻ የያዘ ጢንጥዬ የግጥም በራሪ ወረቀት ነው፡፡ እሳቸው ‹‹አስ-ሰኑሲያ›› ብለው የጠሩት ‹‹መትኑ አስ-ሰኑሲያ አስ-ሱግራ››ም ቢሆን ሱፃፍ ከ150 መስመር ያልበጠና ቢበዛ ከ3 እና ከ4 ገፅ የማይበልጥ ነው፡፡ እነዚህን በድምሩ 10 ገፅ የማይሞሉ ወረቀቶችን ቀርቻለሁ ብሎ .. ‹‹ሁሉንም ዓይነት ዕውቀት አካብቻለሁ››፣ ‹‹ጉራ አይደለም›› .. ማለት … እንግዲህ እናንተው ጨርሱት …

4️⃣. እጅግ የሚደንቀው ደግሞ ሸይኽ ጀይላን መሻኢኾቻችንን በዶ/ር ዐብይ እና በ‹‹መደመር›› ፍልስፍናው ሊያስፈሯሯቸው መሞከራቸው ነው፡፡ በሸኽ ጀይላን አባባል መሠረት የ‹‹መደመር›› ፍልስፍና አዲስና ዘመናዊ ፍልስፍና ነው፡፡ የወሃቢያም ዐቂዳ አዲስና ዘመናዊ ዐቂዳ ነው፡፡ የአሽዓሪያ ዐቂዳ ግን “ጊዜ ያለፈበት” “ያረጀ” ዐቂዳ በመሆኑ አዲሱን እና ዘመን አመጣሹን የወሃቢያን ዓቂዳ ትቼ “ጊዜ ያለፈበትን” የአሽዓሪያን ዐቂዳ እከተላለሁ የሚል ሰው የዶ/ር ዐብይን አዲሱን እና ዘመናዊውን የ‹‹መደመር›› ፍልስፍና አልፈልግም እንዳለ ይቆጠራል ብለው ሸኽ ጀይላን ሲናገሩ ለሳቸው እኔ ተሳቀቅኩ😔 አሳምነውም ሆነ አስቦካክተውም ቢሆን መጅሊስን ለመቆጣጠር ያደረባቸው ከመጠን ያለፈ ጉጉት ይበልጥ ፍንትው ብሎ ታየኝ፡፡

እሳቸው ይህን መጅሊስን የመቆጣጠር ከፍተኛ ጉጉት ለማሳካት ብለው ሲናገሩ 👉 ዘመናዊውን የ‹መደመር› ፍልስፍናን የሚመጥነው ዘመን አመጣሹ የወሃቢያ ዐቂዳ ነው ይላሉ፡፡ በዚህ መልኩ ወሃቢያን ትቶ አሽዓሪያን መከተል ጠ/ሚ ዐብይ ላይ እንደ ማመፅ በማስመሰል አስቂኝ የማስፈራሪያ ንግግር ይናገራሉ፡፡ ዑለሞቻችንን ማስቦካኪያ መሆኑ ነው😀 በአጭሩ ‹‹በባሌም በቦሌም


🔥ቦምቡም-ፈንድቷል🔥
💥〰️〰️〰️〰️〰️💥

በእርጋታና በጥንቃቄ ይነበብ👇

ወሃቢዮቹ የዛሬ 3 ዓመት ገደማ ለረዥም ሰዓታት ከቀረፁት ከ4ለ4ቱ እጅግ ረዥም ውይይት ላይ እነሱን የሚጠቅማቸው መስሏቸው ሻል ይላል ያሉትን 58 ደቂዳ ብቻ ቆርጠው አውጥተው ነበር፡፡ ዛሬ ከፅሑፌ ጋር ያያዝኩት ቪዲዮ ወሃቢዮቹ ካወጡት ቪዲዮ ላይ የቀነጨብኩት አጭር ቪዲዮ ነው፡፡ ቀንጭቤ ያወጣሁትም 1 ደቂቃ ከ25 ሰከንድ ብቻ የሚፈጅ ቪዲዮ ነው፡፡ ብዙ ሰው ልብ ያላለው ቪዲዮ ይመስለኛል፡፡

👉 ይህን የቀነጨብኩትን አጭር ቪዲዮ ሙሉ ትርጉም በኮመንት ሳጥን ውስጥ አስቀምጬዋለሁ፡፡

በዚህ ቪዲዮ የወሃቢያን አስመሳይነትና ቅጥፈት ድባቅ የሚመቱ በርካታ ነጥቦችን እናገኛለን፡፡ ወሃቢዮቹ ቆርጠው ባወጡት 59 ደቂቃ በማይሞላ ቪዲዮ ይህን ያህል ፋወል ሲሰሩ ስታዩ የተቀረውን ለሰዓታት የተቀረፀውን ረዥም ቪዲዮ ለምን እንዳላወጡትና .. ‹‹እባካችሁ አውጡት›› .. ተብለው ቢለመኑም እስከዛሬ ለምን እንቢ ብለው እንደቀሩ ይገባቹሃል፡፡ ዑለሞቻችን ኪታብ ይዘው በማስረጃና በመረጃ ምን ያህል እርቃናቸውን እንዳስቀሯቸው መገንዘብም ቀላል ነው፡፡ ይህን ደግሞ በወቅቱ ተወያይ የነበሩ የአህለ-ሱና ዑለሞች አስረግጠው ነግረውናል፡፡

ወደ ቪዲዮው እንለፍ፡👇

1️⃣. ከ30 ዓመት ወዲህ ወደ ኢትዮጵያ የገባውን .. ሀገር ያወቀውን እና ፀሐይ የሞቀውን .. የወሃቢያን አይዶሎጂ ሸኽ ጀይላን ትንሽ አሻሽለው 20 አመት መርቀውበት 50 ዓመት ለማድረስ ጥረዋል፡፡ ዕውነታው ግን የወሃቢያ አይዶሎጂ ከ30 ዓመት ወዲህ ወደ ሀገራችን የገባ አይዶሎጂ ነው፡፡ እሳቸው 50 ዓመት ቢሉትም ምንም ያሻሻሉት ነገር የለም፡፡ ያው አልሸሹም ዞር አሉ ነው፡፡ ዞሮ ዞሮ የቡድኑ አይዶሎጂ መጤ ነው፡፡ ምናልባት ወሃቢያ ወደ ሀገራችን ሳይገባ በፊት አስቀድመው እሳቸው ወደ ሳውዲ የሄዱበትን እና የወሃቢያን አይዶሎጂ የተቀበሉበትን ጊዜ ደምረው ይሆናል 50 ዓመት ያደረሱት፡፡ 30 ዓመትም አሉት 50 ዓመት ያው መጤነቱን አይቀየረውም፡፡

ከሁሉም እጅግ የሚገርመውና አደገኛው ደግሞ ዓቂዳና ተውሒድ በጊዜ ሂደት የሚሻሻል እና የሚዘምን አድርገው ማቅረባቸው ነው፡፡ ከእሳቸው ይህን አልጠብቅም ነበር፡፡ እስልምና በተለይ ደግሞ ዐቂዳ እንዴት .. ‹‹ጊዜ አልፎበታል›› .. ሊባል ይችላል?! .. እንዴትስ በዘመናዊ መልኩ ተሻሽሏል ይባላል?!

ሌላው ለ1400 ዓመታት አንድ የነበረውን የኢትዮጵያን ሙስሊም የከፋፈለው ወደ ሀገራችን የገባው የወሃቢያ አስተምህሮ መሆኑንና ከዚያ በፊት በሀገራችን ዑለሞች ዘንድ ይቀሩ የነበሩት የዐቂዳ ኪታቦች የአሽዓሪያ የዐቂዳ ኪታቦች እንደነበሩ የቡድኑ ቁንጮ ከሆኑት ከሸይኽ ጀይላን አፍ ትሰማላችሁ፡፡

ከላይ የተገለፁትን አስመልክቶ ቪዲዮው ላይ እንዲህ ይላሉ፡👇

☄〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️☄
👉 ‹‹(አሽዓሪያን በተመለከተ) አሁን እየተነጋገርን ያለው እኮ (በሀገራችን) ጊዜ ስላለፈበት እና ስላበቃለት ተጨባጭ ነው፡፡ አዎ በእርግጥ ከ50 ዓመት በፊት ‹አስ-ሰኑሲያ› (የተባለው የአሽዓሪያ ዐቂዳ ኪታብና ሌሎችም) በሀገራችን ይቀሩ ነበር ….. እነዚህ ኪታቦች በሙሉ ለዚህ ዘመን አይበጁም፡፡ ምክንያቱም ዘመኑ ተሻሽሏልና››
☄〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️☄

ስማኝ ጎበዝ! .. እሳቸው ሳያስቡት በዚህ መልኩ የአይዶሎጂውን መጤነት መስክረዋል፡፡ አይዶሎጂው ወደ ሀገራችን የገባበትን 30 ዓመት ሊለጥጡት ቢታገሉም ከ50 ዓመት በላይ ግን ሊለጠጥላቸው አልቻለም፡፡ ደግሞ ዓቂዳና ተውሒድም ያረጃል፣ ይሞታል ከዚያም በአዲስና በዘመናዊ ዐቂዳ ይተካል እያሉህ ነው፡፡ ወደፊት የወሓቢያንም ዓቂዳ አርጅቷል ብለውህ ሌላ የዘመነ ዐቂዳ ይዘውልህ እንደሚመጡ እርግጠኛ ሁን፡፡ አትጠራጠር😊

2️⃣. የ‹‹ነሕው›› (የዐረብኛ ሰዋሰው grammer) የስሕትት ብዛት፡፡ እሳቸው በዕድሜ ትልቅ በመሆናቸው እና ለተከታዮቻቸው ሞራል ስል ይህን ማለት አልፈልግም ነበር፡፡ ግን ቪደዮው ላይ ሒስ ካቀረብኩ አይቀር ሁሉንም መዳሰስ ስላለብኝ ነው፡፡ ዐረብኛን በወጉ ሳይረዱ ቁርአንን፣ ሐዲስንም ሆነ የሰለፎችን ትክክለኛ አስተሳሰብ መረዳት አዳጋች ነው፡፡ ከዚህች ቆርጬ ካወጣኋት 1 ደቂዳ ከ25 ሰከንድ ከምትፈጅድ እጅግ አጭር ቨዲዮ ውስጥ ከ5 የማያንሱ ተራ የዐረብኛ ሰዋሰው (grammer) ስሕተቶችን ከእሳቸው ላይ ማግኘት ይደንቃል፡፡ ደግሞ እሳቸው በዚህች አንዲት ደቂቃ ከ25 ሰከንድ ውስጥ የፈፀሟቸው የስሕተት ብዛት እኮ ገና የዐረብኛን ግራመር ሀሁ አንድ ብሎ (ትንሿን ‹አጀሩምያ› የተሰኘችውን የሰዋሰው ኪታብ) የቀራ ጀማሪ ደረሳ እንኳ ለሰዓታት ዐረብኛን ቢያነብ ወይም ቢናገር የማይፈፅማቸው ተራ ስሕተቶች ናቸው፡፡ በዚህ 4ለ4 ውይይት ላይ ከሳቸው ትይዩ የተቀመጡ የዐረብኛን ቋንቋ ዘርፎችን ጥንቅቅ አድርገው ያወቁ እና ቋንቋውን በየዘርፉ አገላብጠውና አኝከው የቀሩና እንደ ውሃ የጠጡ .. ሙፍቲን እና ሸኽ ሙሐመድ ሶብዩን .. የመሳሰሉ ዑለሞች፤ በሸኽ ጀይላን ተራ የግራመር ስሕተት ምን ያህል እንደሚጨናነቁ አሰብኩት፡፡ ለመናገርም አፍረው ዝም ብለው ይሆናል፡፡ እኛ ጃሂሎቹም ዑለሞቻችን ሐሳብ ይስጡበት ብለን ነበር ሐያእ አድርገን እስከዛሬ ዝም ብለን የቆየነው፡፡

((ይህን አስመልክቶ ከዚህ በላይ ብዙ ማለት አልፈልግም፡፡ ‹ሐሰት ነው› .. የምትሉ ወሃቢዮች ካላችሁ በሌላ ፖስት የሰዋሰው ስሕተቱን አንድ በአንድ አውጥቼ ላሳያችሁ ዝግጁ ነኝ፡፡ ያልቀነጨብኩትን የቀረውን ቪዲዮ ከጨመርኩ ደግሞ የስሕተቱ መዓት ስንት ሊደርስ እንደሚችል ገምቱ))

3️⃣. ሸኽ ጀይላን እራሳቸው ከ50 ዓመት በፊት 3 የአሽዓሪያ ዐቂዳን የሚያስተምሩ ኪታቦችን እንደቀሩ ገልፀዋል፡፡ በዚህም የተነሳ ሁሉንም ዓይነት ዒልም አካተው እና ሰብስበው እንደተማሩና እንዳካበቱ በኩራት ይገልፃሉ፡፡ ‹‹ጉራ አይደለም!›› ብለውም ያክላሉ፡፡ እሳቸው ‹‹ቀርቻቸዋለሁ›› ብለው የጠቀሷቸው 3 የዐቂዳ ኪታቦች ግን ገና ጀማሪ የዐቂዳ ተማሪ የሆነ ፍሬሽ ደረሳ የሚቀራቸው፣ በግጥም መልክ የተፃፉ እና እያንዳንዳቸው ጥቂት ስንኞችን የያዙ ፓምፍሌቶች ናቸው፡፡ ይህን ያህል .. ‹‹ሁሉንም አውቄያለሁ›› .. የሚያስብሉ አይደሉም፡፡ ባይገርማችሁ ዑለሞቻችን ቀርቶ ወጣት ደረሶቻችን እንኳ የእነዚህን 3 ኪታቦች እጅግ ረዣዥም ሸርሖች (ትንታኔዎች) በዓይነት ዓይነታቸው በመቅራትና ሌሎችንም ሰፋፊ ኪታቦችን በማከል እሳቸው ከሚሉት የትናየት አልፈው ሄደዋል መሰላችሁ፡፡

ሸኽ ጀይላን ሲናገሩ እንዲህ ይላሉ፡👇

☄〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️☄
👉 ‹‹አዎ በእርግጥ ከ50 አመት በፊት ‹አስ-ሰኑሲያ› (የተባለው የአሽዓሪያ ዐቂዳ ኪታብ) በሀገራችን ይቀራ ነበር፡፡ እኔም ይህን ኪታብ ከቀሩት ውስጥ ነኝ፡፡ ‹በድኡል-አማሊ› እና ‹ጀውሃራ› (የተባሉትን የአሽዓሪያ) ኪታቦችን ከቀሩት ውስጥ ነኝ፡፡ አውቃቸዋለሁ፡፡ እኛ ሁሉንም ዕውቀቶች አካተናል፡፡ አልሓምዱሊላህ፡፡ ጉራ አይደለም፡፡ የጥንቱን (የዐቂዳ) ዕውቀቶች እና ዘመናዊ (የዐቂዳ) ዕውቀቶችንም አካተናል፡፡ (እንዳልኳችሁ) እነዚህን ኪታቦች ቀርተናል፡፡››
☄〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️☄




ቢስሚላህ

ጠዋት 2:12 ነበር ቦታው የተገኘነው
ከሱፍዩ ጀመዓ ሸይሆቹም ጭምር በጊዜ ቦታ ቦታቸውን እየያዙ ነው
እስከ 3:45 ማንም የወሀብይ ተወካይ አልተገኘም
ከ3:45 በኋላ አንዲት ሴትና አንድ ወንድ ገቡ
የሱፍይ ሸይሆች መጥተዋል ቦታቸውን ይዘዋል
4:10 ገደማ ሌላ 2 ወሀብይ ገቡ
ከ4:15 በኋላ በነመሐመድ አባተ የተመራ ቡድን ተንጋግቶ ወደአዳራሽ ገባ
ከሱፍዩም ከወሀብዩም ጥሪ የተደረገላቸው 40:40 ሰዎች ነበሩ ግና ስም ቼክ ሲደረግም ቆጠራ ሲካሄድም የወሀብይ 53 አለፈ
3 ጊዜ የ'ኛ ሰዎች እኒህ ናቸው እያሉ ወረቀት ቀያይረዋል
ውይይቱ ሳይካሄድ 6:00 ሰዓት አለፈ
በዚህ መሀከል ሸይህ ቃሲም ታጁዲን ይቅርታ አድርጉልንና ሁላችሁም ውጪ ውጡና ስም እየተጠራ ይግባ ተባለ
ሁሉም ወደውጪ ወጣና እየተጠራ ገባ
ሌላው ውጪ እንዲቆይ በርም ተቆለፈ
ተቀዳሚ ሙፍቲህ ሀጅ ዑመር እድሪስ ወደ አዳራሹ ገቡ
ሸይህ ቃሲም ታጁዲን የመግቢያ ንግግር አደረጉ
የዛሬው ዓላማችን በልዩነት ነጥቦች ላይ መወያየት ነው ፣ ሌላ አጀንዳ የለንም አሉ
ተቀዳሚ ሙፍቲህ ሀጅ ዑመር እድሪስ በልዩነቶች እንጂ በሌላ አንወያይም የሚል ሐሳብ አቀረቡ
ዶ/ር ጄይላንም ዛሬ የተገናኘነው በልዩነቱ ለመወያየት ነው አሉ
ከወሀብያ በኩል መነጫጭ ተፈጠረ
እጅ እያወጡ ሓሳቦችን መሰንዘር ጀመሩ
ግማሹ በልዩነት ሓሳቡ እንወያይ ፣ አይ አይሆንም በመተዳደሪያ ደንቡ ነው ምንወያየው የሚሉ ሃሳቦች መነሳት ተጀመረ
ዶ/ር ጀይላን መጀመሪያ ላይ በልዩነቱ ላይ እንወያይ አሉ ቀጠሉና ምንም የልዩነት ሓሳብ የለንም/አላዘጋጀንም/ አንድ ወገን ብቻ ነው ያዘጋጀው ብለው ዋሹ
ሸይህ ቃሲም ታጁዲን ይኸው ያቀረባችሁት የልዩነት ሓሳብ በአረብኛ የተፃፈ ሀርድ ኮፒም ሲዘዋወር የነበረ ሶፍት ኮፒውም ደርሶናል ብለው አሳይዋቸው
ወደ ውይይቱ ይገባ የሚል ዕንድምታ በቤቱ ተወሰነ
ዶ/ር ጀይላን ውይይቱን እኔም ሀጂም አይመሩትም ገለልተኛ ወገን ነው መምራት ያለበት አሉ
ይህንን ንግግር አድርገው እንኳ አልጨረሱም አዳራሹ አላሁ አክበር በሚል ድምፅ ተረበሸ
በትልቅ ጩኸት በሚረብሽ ድምፅ አላሁ አክበር እያለ ተቀዳሚ ሙፍቲህ ሀጅ ዑመር እድሪስን ለመምታት ወደፊት ተንደረደረ (ኩራባቸው)
የወሀብያ ሰዎች ሁሉም ብድግ ብድግ አሉ
ኩራባቸው የተባለው ጎረምሳ ከሁሉም ጀርባ ነበር የተቀመጠው ከገባበት ሰዓት ጀምሮ እየረበሸ እያዋከበ በአደብ አልቀመጥ እያለ እያስቸገረ ነበር (ተወያይ ነኝ ብሎ ገብቶ የእንግዳ ወንበር ላይ አልቀመጥም በማለት ነበር ከኋላ የተቀመጠው)
ማን ማንን እንደያዘ መለየት በማያስችል ሁኔታ ግርግር ተፈጠረ
ተቀዳሚ ሙፍቲህ ሀጅ ዑመር እድሪስ ብድግ ብለው ሊወጡ ሲሉ እንዳይወጡና ውይይቱ እንዲካሄድ ተብሎ ቁጭ እንዲሉ ሸይህ ቃሲም ታጁዲን አረጓጓቸው
ኩራባቸውን ይዘው አስቀመጡት
ግርግሩ ግን ሊቆም አልቻለም
በዚህ መሀከል የተቀዳሚ ሙፍቲህ ሀጅ ዑመር እድሪስ ጥበቃዎች (ደህንነቶች) ይዘዋቸው ሊወጡ ተነሱ
ይሄኔ ኩራባቸው የተባለው ግለሰብ ተቀዳሚ ሙፍቲህ ሀጅ ዑመር እድሪስን ሊደበድብ ያዙት ያዙት እንዳይወጣ ለምን ይወጣል እያለ ወንበር አነሳ አገላጋይ ያዘው በፍፁም እምቢ አለ ጩኸቱ ተበራከተ ተቀዳሚ ሙፍቲህ ሀጅ ዑመር እድሪስ ይዘዋቸው ከአዳራሽ ወጡ
በብዙ ልመናና ኡኡታ አዳራሹ ፀጥ እንዲል ተደረገ
ሸይህ ቃሲም ታጁዲን ዝሁር ሰግደን ምሳ በልተን እንምጣ ብለው ተወጣ
ምሳ አቀርባለሁ ብሎ የነበረው አቡበከር አህመድ ነበር አላቀረበም
ምሳ ለማቅረብ የተስማማው ውይይቱ ሆቴል ቢሆን እንደነበርና እሱ ሲጠበቅ ተቋሙ ምሳ ለማቅረብ የዘገየ መሆኑ ተገለፀ
ምሳ ሳይበላ ተገባ
የተለያዩ ሃሳቦች ከሁለቱም ወገን ተነስተዋል ነገር ግን በዚህ ስሜታዊነት ውይይት እንደማይካሄድ ታመነበት
ውይይቱ መቋረጡንና ሌላ ጊዜ እናሳውቃለን ብለው ሸይህ ቃሲም ታጁዲን አቀረቡ
በዚህ ተጠናቀቀ






Hasen Injamo dan repost
መውሊድ ማን አከበረው?
1️⃣ አላህ - አዎ
ነቢዩ ﷺ የተወለዱ ቀን በመቶዎች የሚቆጠሩ ተአምራት ተመዝግቧል:: ሲነድ የነበረ የጣዖታውያን እሳት ጠፍቷል, የሮማና የፋርስ ቤተመንግሥት ተነቃንቋል, ከመወለዳቸው 50 ቀን ቀድሞ የአክሱም ሰራዊት በአእዋፍ ተደምስሷል, ብዙ ጅራታም ከዋክብት ተወንጭፈዋል, የጀነት በር ተከፍቷል, የጀሀነም በር ተዘግቷል::

2️⃣ ቁርአን - አዎ
በማያሻማና በግልጽ ቃላት በእዝነቱ ነብይ እንድንደሰት መክሯል:: ከሰበሰብነው ሁሉ በነቢዩ ﷺ መምጣትና በቁርአን መውረድ መደሰት እንደሆነ በሱረቱል ዩኑስ 10:57-58 ተቀምጧል::

3️⃣ መላኢካዎች - አዎ
ከአላህ ጋር በነቢዩ ﷺ ላይ ሶለዋት ያወርዳሉ:: አማኞችም ታዘዋል:: ተጋብዘዋል::

4️⃣ ነቢዩ ሙሐመድ ﷺ - አዎ
የተወለዱባትን ሰኞ ዕለት ጾመዋል

5️⃣ ኸሊፋዎች - አዎ
የሰኞን መውሊድ የኻለፈ (የተቃረነ) ኸሊፋ አልተመዘገበም::

6️⃣ ሶሀቦች - አዎ
ነቢዩ ﷺ በመወለዳቸው ሰኞን ሲጾሙ ኖረዋል::

7️⃣ ቀጣይ ትውልዶች - አዎ
በመጾም እና ምስኪን ምግብ በማብላት አክብረዋል:: ምግብ ለአእዋፍ ተርፏል::

8️⃣ አራቱ ሊቃውንት - አዎ
የተቃረነ የለም:: በተመሳሳይ በፆም, ባሪያ ነጻ በማድረግና በሶደቃ አክብረዋል::

9️⃣ ዑለሞቻችን - አዎ
በጾም, ምስኪን በማብላት, በማዜም, ሌሊቱን ቆሞ በማደር አክብረዋል::

🔟 ወላጆቻችን - አዎ
ሸይኾቻቸው የሠሩትን በየቤታቸው ሠርተዋል::

1️⃣1️⃣ የነቢያችን ﷺ ዘመዶች - አዎ
የተወለዱ ቀን በሗላ በጠላትነት የተቃረናቸው አጎታቸው ሳይቀር ሱወይባ የምትሰኝን ባሪያ ነጻ አድርጓል:: በዚህም ሰኞ ዕለት የጀሀነም ቅጣት እንደሚበርድለት በሀዲስ ተነግሯል::

1️⃣2️⃣ አባታቸው ዐብዱላህ የተወለዱ ቀን ሳይቀር የነቢዩ ﷺ አያት ዓብዱልሙጦሊብ 12 ግመል አርደው ደግሰው አብልተዋል::

1️⃣3️⃣ ክርስቲያኖች - አዎ
ሥራ ዘግተው አብረው አክብረው ይውላሉ::
_____

↘️ ኢብሊስ - አይ
ነቢዩ ﷺ የተወለዱ ቀን እላዩ ላይ አፈር እየበተነ ጮሆአል:: አሁንም ይጮኻል, ያስጮኻል::

↘️ ወሃቢያ - አይ
የመውሊድ ቀን ሲረብሽ ሲጮህ ሲያንጉዋጥጥ ይውላል:: እስልምና ማለት መውሊድን መከልከል እስኪመስል ሌላ ሥራ ይተዋል::

ከሁለቱ ውጭ ወዳጅም ጠላትም አክብሮታል:: ያከብረዋል::






🟢ኢስላማዊ ፎቶግራፍ መደድ /islamic photograpy dan repost
መውለድን ከሚያሳምሩት እና አይረሴ ከሚያረጉት አንዱ ወንድም ከወንድሞቹ እህትም ከእህቶቿ ጋር የሰይዳችን❤️ሰ ዐ ወ ስም ያለበት ተመሳሳይ ልብስ መልበስ ነው ። እኛም እያዘጋጀን ነው ከጀሊሉ ጋር በጀመዐ በግል ለምትፈልጉ አናግሩን ሳያልቅ ።

@Abubeker
@rimixachn


🟢ኢስላማዊ ፎቶግራፍ መደድ /islamic photograpy dan repost
መውለድን ከሚያሳምሩት እና አይረሴ ከሚያረጉት አንዱ ወንድም ከወንድሞቹ እህትም ከእህቶቿ ጋር የሰይዳችን❤️ሰ ዐ ወ ስም ያለበት ተመሳሳይ ልብስ መልበስ ነው ። እኛም እያዘጋጀን ነው ከጀሊሉ ጋር በጀመዐ በግል ለምትፈልጉ አናግሩን ሳያልቅ ።

@Abubeker
@rimixachn


🟢ኢስላማዊ ፎቶግራፍ መደድ /islamic photograpy dan repost
መውሊድ ❤❤ ደረሰ 40 ቀናት አከባቢ ቀሩት ሁላችንንም አላህ በሰላም ያድርሰን ።አሚን

እንደተለመደው መውሊዳችንን አይረሴ ከሚያረጉልን አንዱ የሰይዳችን ❤(ሰ ዐ ወ) ስም ያለበትን ልብስ መልበስና መውሊዳችንን ማሳመር ሲሆን እንደተለመደው ዘንድሮም እያዘጋጀን ነው የዚህ ድምቀት ተሳታፊ መሆን የምትፈልጉ ማንኛውም ሰው ወንድም ሴት ያለ ሸርጥ
አንድ ነው ሸርጡ እሡም የሰይዳችን ሀቂቃ ወዳጅ መሆን ብቻ የምላስ ሳይሆን የልብ


@abubeker
@Rimixachn

20 ta oxirgi post ko‘rsatilgan.

231

obunachilar
Kanal statistikasi