ጥቂት ወሳኝ ነጥቦች በለይለተል ቀድር ዙሪያ
~
ለይለቱል ቀድር ማለት ትልቅ ደረጃ ያላት ለሊት ማለት ነው። ከፊል ዓሊሞች ዘንድ ደግሞ ፍጡራንን የሚመለከቱ የአመቱ ውሳኔዎች የሚተላለፍባት ለሊት ማለት ነው።
የለይለተል ቀድር ደረጃዎች፦
1. ቁርኣን የወረደባት ለሊት ነች። ጌታችን “እኛ (ቁርኣኑን) በለይለተል ቀድር አወረድነው”ብሏል። [አልቀድር፡ 1]
2. በሷ ውስጥ የተፈፀመ ዒባዳ ከሌሎች ለሊቶች ምንዳው የበለጠ ነው። አላህ “ለይለተል ቀድር ከሺህ ወር በላጭ ናት” ይላል። [አልቀድር፡ 3]
3. በሷ ውስጥ መላእክት ኸይርን ይዘው ወደ ምድር ይወርዳሉ። ጌታችን “በርሷ ውስጥ መላእክትና መንፈሱ (ጂብሪል) በጌታቸው ፈቃድ በነገሩ ሁሉ ይወርዳሉ” ብሏል። [አልቀድር፡ 4]
4. ለሊቷ ዒባዳ የሚበዛባት፣ ሰላም የሚሰፍንባት ለሊት ናት። ጌታችን “እርሷ እስከ ጎህ መውጣት ድረስ ሰላም ብቻ ናት” ብሏል። [አልቀድር፡ 5]
5. የተባረከች ለሊት ናት። ጌታችን “እኛ (ቁርኣኑን) በተባረከች ለሊት ውስጥ አወረድነው” ብሏል። [ዱኻን፡ 3]
6. በዚች ለሊት አላህ በአመቱ ውስጥ ያሉ የፍጡራኑን የእድሜና የሲሳይ ልኬታዎችን ይፅፋል። “በውስጧ የተወሰነው ነገር ሁሉ ይልለያል” ብሏል አላህ። [ዱኻን፡ 4]
7. በዚያች ለሊት ምድር ላይ የሚኖሩት የመላእክት ብዛት ከጠጠሮች ብዛት የበዛ ነው። [አልባኒ ሐሰን ብለውታል]
8. ለተጠቀመባትና አጅሩን ከአላህ ላሰበ ሰው ከወንጀል መማርያ ለሊት ነች። ነብዩ ﷺ እንዲህ ብለዋል፡- “ለይለተል ቀድር አምኖና አስቦ የቆመ ሰው ያለፈ ወንጀሉ ይታበስለታል።” [ቡኻሪና ሙስሊም]
ስለዚህ ይህቺን ወሳኝና እጅግ የላቀ ዋጋ ያላት ለሊት ለማገኘት የምንችለውን ሁሉ ልንጣጣር ሌሎችንም ልናበረታታ ይገባል። ኢብኑል ቀይም ረሒመሁላህ እንዲህ ይላሉ፡- “ለይለተል ቀድር በአመት ውስጥ የምትገኝ አንዲት ቀን ብትሆን እሷን ለማገኘት ስል አመቱን ሁሉ እቆም ነበር። በ(ረመዳን) አስር ለሊቶች ውስጥ ከሆነችማ ምን ነካህ? (እንዴት እዘናጋለሁ?!)” [በዳኢዑል ፈዋኢድ፡ 1/55]
ለይለቱል ቀድር የምትገኘው በየትኛው ጊዜ ነው?
የምትገኘው በረመዳን ብቻ ነው። ከረመዳንም በመጨረሻዎቹ አስሮች ውስጥ። ነብዩ ﷺ “ይቺን ለሊት እየፈለግኩ የመጀመሪያውን አስር ኢዕቲካፍ አደረግኩኝ። ከዚያም መካከለኛውን አስር ኢዕቲካፍ አደረግኩኝ። ከዚያም (የሆነ አካል) መጥቶኝ ‘እሷ በርግጥም የመጨረሻው አስር ላይ ናት’ አለኝ” ማለታቸው ይህን ያስረግጣል።
ይቺ ታላቅ ለሊት እንዳታልፈን የምንችለውን ሁሉ ልንጣጣር ይገባል። ነብዩ ﷺ በሐዲሣቸው እንዲህ ብለዋል፡- “በሱ ውስጥ ከአንድ ሺ ወር የምትበልጥ ለሊት አለች። የሷን ኸይር የተነፈገ በእርግጥም (ትልቅ ነገር) ተነፍጓል።” [ሶሒሑል ጃሚዕ፡ 2247]
መቼ እንፈልጋት?
ይበልጥ የሚገመተው ጊዜ 27ኛዋ ለሊት ናት። ይሁን እንጂ “ለይለተል ቀድርን በ23ኛዋ ለሊት ፈልጓት” ማለታቸው እንዲሁም “ለይለተል ቀድርን በመጨረሻዎቹ አስሩ (ለሊቶች) ፈልጓት። ከተረታችሁ በመጨረሻዎቹ 7 ላይ አትረቱ” ማለታቸው ለይለተል ቀድር ሁሌ በአንድ ለሊት ላይ እንደማትገደብ ያስረዳል። በተለይ ደግሞ በዊትሮቹ (21፣ 23፣ 25፣ 27፣ 29) የመሆን እድሏ ሰፊ ነው። ይህን አስመልክተው ነብዩ ﷺ “ለይለተል ቀድርን ከረመዳን በመጨረሻዎቹ አስሩ (ለሊቶች) በዊትሮቹ ፈልጓት” ብለዋል። [ቡኻሪና ሙስሊም]
ይህ ማለት ግን ከነጭራሹ በሸፍዕ ለሊቶችም (22፣ 24፣ 26፣ 28፣ 30) አትሆንም ማለት አይደለም። ምክንያቱም ነብዩ ﷺ “ከረመዷን የመጨረሻዎቹ አስሮች ውስጥ ፈልጓት። ዘጠኝ ሲቀረው፣ ሰባት ሲቀረው፣ አምስት ሲቀረው” ብለዋልና። ወሩ 29 ቀን ከሆነ 9፣ 7፣ 5 ሲቀር ዊትር የሚሆኑት ከመጨረሻ ወደ ኋላ ሲቆጠር ነው። ከመጀመሪያ ለሚቆጥር ግን ዊትር ሳይሆን ሸፍዕ ቁጥር ነው የሚሆኑት። ይህም ሸፍዕ ለሊቶችም ላይ የመሆን እድል እንዳለ ያስረዳናል። ቢሆንም ግን “ከ(መጨረሻው አስር) በዊትሩ ፈልጓት” ስላሉ ዊትሩ ላይ ይበልጥ ማተኮር ይገባል።
በለይለተል ቀድር ምን ይጠበቅብናል?
ዒባዳ ማብዛት። ነብዩ ﷺ “ለይለተል ቀድር አምኖና አስቦ የቆመ ሰው ያለፈ ወንጀሉ ይታበስለታል” ይላሉ። [ቡኻሪና ሙስሊም] እናም በዚች ለሊት ታላቅነትና መደንገግ አምኖ፣ ከዚያም ለመታየት ለጉራና መሰል አላፊ ኒያ ሳይሆን አጅሩን ከአላህ በማሰብ እንደሶላት፣ ዱዓእ፣ ቁርኣን መቅራት፣.. የፈፀመ ሰው ወንጀሉ ይታበስለታል ማለት ነው።
ምልክቶቿ
1. “በዚያን ቀን ማለዳ ፀሀይዋ ነጭ ሆና ጨረር ሳይኖራት ትወጣለች።” [ሙስሊም]
2. በዚያን ለሊት ዝናብ ሊዘንብ ይችላል። [ቡኻሪና ሙስሊም]
3. ቀጣዩ ቀን አየሩ ሞቃትም ብርዳማም ሳይሆን የተስተካከለ ይሆናል። ፀሀይዋም ደካማና ቀይ ትሆናለች። [ሶሒሑል ጃሚዕ]
እነዚህ ምልክቶች ግን አንፃራዊ ናቸው ይላሉ ሸይኹል አልባኒ ረሒመሁላህ። በአካባቢው ባለው የአየር ሁኔታ ሊወሰን ይችላል። ስለሆነም በትክክል ለይለተል ቀድር በተከሰተበት ጊዜም እነዚህን ምልክቶች ብዙ የማያያቸው ሊኖር ይችላል።
ለይለተል ቀድር ለሰጋጆች ብቻ አይደለችም!
የወር አበባ ላይ፣ የወሊድ ደም ላይ ያሉ፣ መንገደኞች… የዚች ለሊት ትሩፋት አያልፋቸውም። ማስረጃው ጠቅላይ ነውና። ባይሆን ከሶላት ውጭ ባሉ ዒባዳዎች ላይ ሊበራቱ ይገባል። በዚያች ለሊት ዱዓእ ማብዛት ጥሩ ነው። እንዲያውም ሱፍያኑ ሠውሪ ረሒመሁላህ “በለሊቷ ከሶላት ይልቅ ዱዓእ እኔ ዘንድ የተወደደ ነው” ይላሉ።
ለይለተል ቀድር በአይን ትታያለች?
አንዳንዶች እግራቸውን ዘርግተው፣ እያወሩ ሰማይ ሰማይ ያንጋጥጣሉ። የሚጠባበቁት ተወርዋሪ ኮከብ ነው። እሱን ሲያዩ “አኑረን አክብረን” ብለው ይንጫጫሉ። ይሄ ባዶ እምነት ነው። ለይለተል ቀድር አላህ በአንዳንድ ባሮቹ ቀልብ ላይ ከወትሮው ለየት ባለ መልኩ የመረጋጋት ወይም የመለየት ስሜት ከማሳደሩ ውጭ በአይን የሚታይ ነገር አይደለም። የሚታየው ምልክቶቿ እንጂ እራሷ አይደለችም። ሰዎች የሚጠበቅባቸውን ከተወጡ ለሊቱ ለይለተል ቀድር መሆኑን ባያውቁ እንኳን ትሩፋቷን አያጡም።
ለይለተል ቀድር እንደሆነ ውስጡ ያደረ ሰው ምን ያድርግ?
በተለይ ደግሞ ለሊቱ ለይለተል ቀድር እንደሚሆን ውስጣችንን ከተሰማን ይበልጥ ልናተኩርበት የሚገባን ዱዓእ “አሏሁመ ኢነከ ዐፉውዉን ቱሒቡል ዐፍወ ፈዕፉ ዐኒ” (“ጌታዬ ሆይ! አንተ በርግጥም ይቅር ባይ ነህ። ይቅር ማለትን ትወዳለህ። ስለሆነም ከኔ ይቅር በለኝ” የሚለው ነው። [አልባኒ ሶሒሕ ብለውታል] ስለዚህ ዋናው ትኩረታችን የአላህን ይቅርታ ለማግኘት ይሁን።
ግን ለምን አላህ ለይለተል ቀድርን ስውር አደረጋት?
ዑለማዎች እንደሚሉት ታላላቅ ትሩፋቶች በሚገኝባቸው የረመዳን የመጨረሻ ለሊቶች ሙስሊሞች በዒባዳ ይበራቱና ይጠናከሩ ዘንድ ነው አላህ ይቺን ለሊት ስውር ያደረጋት። እናም ለይለተል ቀድርን እንዳታመልጣቸው ሲጣጣሩ ለይተው ቢያውቋት ሊኖራቸው ከሚገባው በበለጠ ለዒባዳ ይተጋሉ። በዚህም ይበልጥ ይጠቀማሉ። ለይተው ቢያውቋት ግን እሷ ብቻ ላይ አነጣጥረው ሌሎቹ ለሊቶች ላይ ይዘናጉ ነበር። እናም መሰወሯ ነብዩ ﷺ እንዳሉት ለኛ ኸይር ነው። [ቡኻሪ]
=
(ኢብኑ ሙነወር፣ ሰኔ 29/2007)
የቴሌግራም ቻናል :-
https://t.me/IbnuMunewor