الشباب السلفيين dan repost
«ወልዶ መሳም»
-------------------------------------------
በትዳር ተጣምሮ ልጅ ወልዶ ከመምከን፡
ትዕግስት እያደረግን ይሻለናል መስከን፡
በማይጣፍጥ ጥምረት ጊዜ ከማባከን፡
በስቃይ ከመውጣት የህይወትን እርከን፡
ብቸኝነት ጌጥ ነው የለበትም እንከን፡
〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️
እናት እና አባቱን ልጅ ካለ አልታዘዝ፡
አሏህ ይዘንልን ከባድ ነው ይህ መዘዝ፡
ከሰው ፊት ነቅቼ አሏህ ፊት ከመፍዘዝ፡
አያድርስ ነው ፍርጃው እንድህ አይነት መቅረዝ፡
〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️
ውብ ፀባዬ ሰናይ የሆነ እንደሁ ልጁ፡
ካልተልከሰከሰ ንፁህ ከሆነ እጁ፡
ወደ አሏህ ካስጠጋ ሁሌም በችግሩ፡
ለሽርክ ለጥመት ካልተራመደ እግሩ፡
ተውሒዲና ሱናን ካመነ አንደበቱ፡
በሐቅ ከፀና ካማረ ውበቱ፡
በሩቅ ሚስጥር ሁሉ በጌታ ቃል ያምናል፡
እንደዚህ ከሆነ ልጅ መውለድ ያስቀናል፡
--------------------------------------------
በትዳር ተጣምረህ ስትኖር በዚህች አለም፡
ልጅ ወልዶ እንደ-መሳም አርኪ ነገር የለም፡
የተውሒዷን ንግስት በደስታ ካገባት፡
አቋም ያለው ጀግና ልጅ ይወልዳል አባት፡
አባ ሲል ሲጣራ ፍቅሩ ልብ ይቀማል፡
ልጂን ወልዶ መሳም ጥሩ ነው ይጠቅማል፡
ከባድ ነው ትዝታው ፈፅሞ አይረሳም፡
ያጓጓል ያሳሳል ልጅን ወልዶ መሳም፡
〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️
....✍️በኑረዲን አል አረቢ
〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️
https://t.me/nuredinal_arebi
https://t.me/nuredinal_arebi
-------------------------------------------
በትዳር ተጣምሮ ልጅ ወልዶ ከመምከን፡
ትዕግስት እያደረግን ይሻለናል መስከን፡
በማይጣፍጥ ጥምረት ጊዜ ከማባከን፡
በስቃይ ከመውጣት የህይወትን እርከን፡
ብቸኝነት ጌጥ ነው የለበትም እንከን፡
〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️
እናት እና አባቱን ልጅ ካለ አልታዘዝ፡
አሏህ ይዘንልን ከባድ ነው ይህ መዘዝ፡
ከሰው ፊት ነቅቼ አሏህ ፊት ከመፍዘዝ፡
አያድርስ ነው ፍርጃው እንድህ አይነት መቅረዝ፡
〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️
ውብ ፀባዬ ሰናይ የሆነ እንደሁ ልጁ፡
ካልተልከሰከሰ ንፁህ ከሆነ እጁ፡
ወደ አሏህ ካስጠጋ ሁሌም በችግሩ፡
ለሽርክ ለጥመት ካልተራመደ እግሩ፡
ተውሒዲና ሱናን ካመነ አንደበቱ፡
በሐቅ ከፀና ካማረ ውበቱ፡
በሩቅ ሚስጥር ሁሉ በጌታ ቃል ያምናል፡
እንደዚህ ከሆነ ልጅ መውለድ ያስቀናል፡
--------------------------------------------
በትዳር ተጣምረህ ስትኖር በዚህች አለም፡
ልጅ ወልዶ እንደ-መሳም አርኪ ነገር የለም፡
የተውሒዷን ንግስት በደስታ ካገባት፡
አቋም ያለው ጀግና ልጅ ይወልዳል አባት፡
አባ ሲል ሲጣራ ፍቅሩ ልብ ይቀማል፡
ልጂን ወልዶ መሳም ጥሩ ነው ይጠቅማል፡
ከባድ ነው ትዝታው ፈፅሞ አይረሳም፡
ያጓጓል ያሳሳል ልጅን ወልዶ መሳም፡
〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️
....✍️በኑረዲን አል አረቢ
〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️
https://t.me/nuredinal_arebi
https://t.me/nuredinal_arebi