Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር) dan repost
ወደ ሱንና ቢመጣም ጥላቻው ከልቡ አይፋቅም፡፡ ሰበብ እየፈለገ ከማጠልሸትም አይመለስም፡፡ እጅግ የሚያስጠላው ግን በልቡ ያረገዘውን የጥላቻ መንፈስ ኢስላማዊ ቅብ ሲቀባው ነው፡፡ ሌላው ደግሞ ቀድሞ የሚወደው ሰው - ምናልባት አስተማሪውም ሊሆን ይችላል- የፈተና ሰበብ ሲሆንም አብሮ የሚከንፍ አለ፣ በፈሰሰበት የሚፈስ፡፡ ወንድም እህቶች እኛስ ከየትኞቹ ነን?
ኡስታዝህ ቢድዐውም ሺርኩም የማይጎረብጠው የላሸ የላሸቀ ሊሆን ይችላል፡፡ የራሱ መላሸት አልበቃ ብሎት አንተንም ልሽት፣ ልሽቅ ሊያደርግህ ይችላልና ተጠንቀቅ፡፡ ኡስታዝህ “ጭር ሲል አልወድም” ባህሪ የተፀናወተው በየሄደበት አቧራ የሚያስነሳ “ሙበጥቢጥ” ሊሆንም ይችላል፡፡ በቃ አመላችን እንደ መልካችን ብዙ አይነት ነው፡፡ በሙብተዲዑም በሱኒውም መደነቅ የሚሻ አግበስባሽ እንዳያስተኛህ እንደምትጠነቀቀው ሁሉ የሱንና ሰዎችን በመደዳ እያጨደ ታዋቂዎችን በመተቸት ታዋቂ መሆን የሚሻ አጉል ግብዝ በሱንና ስም፣ በሰለፊያ ስም ከማትወጣበት መቀመቅ እንዳይነክርህ ተጠንቀቅ፡፡ ምናልባት በዚያ ማዶ መንሸራተቱን እንደ ጥበብ የሚቆጥር ሰው ሊያጋጥምህ ይችላል፡፡ በሌላ ማዶ ደግሞ “እከሌ ሙብተዲዕ ነው! እሱን ሙብተዲዕ ያላለም ሙብተዲዕ ነው፣…” እያለ ሰንሰለታማ የተብዲዕ ዘመቻ የሚከፍት ሰነፍ “የሂሳብ አዋቂ” አለ፡፡
በምድር ላይ ብዙ አይነት ዋልጌዎች አሉ፡፡ ከዋልጌነትም የከፋው በዲን ስም፣ በሱንና ስም የሚፈፀም ዋልጌነት ነው፡፡ ግና ተጠንቀቅ!! የዋልጌዎች ዋልጌነት ዋልጌ አያድርግህ፡፡ ከቻልክ ምከር፡፡ ካልቻልክ ባንተና በዋልጌዎች መካከል የብረት አጥር ይኑር፡፡ ከዋልጌ ጋር እየተወራወርክ ወደ ሰፈራቸው አትውረድ፡፡
ፊትና ሲነሳ አቋም ከመያዝህ በፊት ቆም ብለህ ተመልከት፡፡ አንድን አካል “እቃወማለሁ” ብለህ ሌላ ፅንፍ እንዳትረግጥ፡፡ ካጥፊ “እሸሻለሁ” ብለህ የእውር ድንብር ስትሮጥ ሌላ መልክ ያለው የአጥፊዎች ወጥመድ ጠልፎ እንዳያስቀርህ ተጠንቀቅ፡፡ ከሺዐዎች ለመሸሽ ከናሲባዎች መጠጋት መፍተሄ አይሆንም፡፡ ከኸዋሪጅ የጥፋት ዶፍ ሸሽቶ ከሙርጂኣ ጣሪያ ስራ መጠለል ከድጡ ወደማጡ ነው፡፡ ከኢኽዋን “እሸሻለሁ” ብለህ ከሐዳዲያ የመንደር ውሪ ጋር የጥፋት ኩሬ ውስጥ እንዳትንቦጫረቅ፡፡ “ሐዳዲያ ኢትዮጵያ ውስጥ የለም” የሚል ካለ ወይ በማያውቀው የሚቀባጥር ሳይጠራ አቤት የሚል ጭልጥ ያለ መሀይም ነው፡፡ ወይ ደግሞ ሽወዳን እንደ እድሜ ማራዘሚያ የሚጠቀም ከራሱ በስልት የሚከላከል የነጋበት “ብልጣብልጥ” ነው፡፡ የነዚህኞቹ አፀፋ ገፋፍቶትህ ሌላ ፅንፍ በመያዝ በአንዳንድ ርእሰ-ጉዳዮች ላይ ያለምንም ተብዲዕ የተለየ ሀሳብ ስለያዘ ብቻ ማንንም በሐዳዲይነት ከመፈረጅም ተጠንቀቅ፡፡ ሐቁ ያለው ከመሀል ነው፡፡
ብቻ ካንዱ የቢድዐ አንጃ ወደሌላው ሲከረባበት የኖረ ፅንፍ የረገጠ ጥሬ ሁሉ እየተነሳ “ከኛ ጋር ያልሆነ ከጠላት ነው” የሚል ሰይፍ መዝዞ ሲያስፈራራህ አትንቦቅቦቅ፡፡ ማንም ምንም አያመጣም፡፡ የማንም ውዳሴ ወደ ሱንና እንደማይስገባህ ሁሉ የማንም ቀረርቶም ከሱንና አያስወጣህም፡፡ ኢስላም ክርስትና አይደለም፡፡ ማንም “ውግዝ ከማሪዎስ” ብሎ አያስወጣህም፡፡ ስለሆነም የማንም ፍረጃ አያስፈራህ፡፡ የማንም ሙገሳም አይሸውድህ፡፡ ደግሞ ተጠንቀቅ፡፡ ለፈታኞች አጋዥ አትሁን፡፡ ከቻልክ በግልፅ መልስ፡፡ ካልሆነ በግልፅ ራቅ፡፡ በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ በየትኛውም መልኩ አጥፊዎችን በሚያስተዋውቅ ስራ ላይ አትሰማራ፡፡ ሌላው ቀርቶ በፌስቡክ ጓደኝነት እንኳን ለአጥፊዎች አጋር እንዳትሆን ተጠንቀቅ፡፡ የጭቅጭቅ በር እየከፈትክ ፔጃቸውን አታስተዋውቅ፡፡ እያንዳንዷ ኮሜንትህ ለተቃውሞ እንኳን ቢሆን የአጥፊዎችን የጥፋት ገፅ የማስተዋወቅ ሚና እንዳላት አስተውል፡፡ ለእያንዳንዱ ጩኸታቸው መልስ አትስጥ፡፡ ዝንብ “ጢንንንን” ባለ ቁጥር እጅህን እያነሳህ ክብር አትስጥ፡፡ ከነጭራሹ ዝም በል ማለቴ አይደለም፡፡ ሲያስፈልግ ካልተንቀሳቀስክ የዝንብ ቀፎ ትሆናለህ፡፡
ሸይኽ ፈውዛን በክፉ አንጠረጥራቸውም፡፡ ግና ለማንም እንደማይሰወረው የሳቸውም መጨረሻ አይታወቅም፡፡ ቀጥተኛ በሆነ መልኩ ለመናገር ያክል፣ አይደለም በሱንና ስም የሚነግድ የመንደር ኡስታዝ ይቅርና ፈውዛን ቢንሸራተቱ ልንንሸራተት አይገባም፡፡ ነገሩን ይበልጥ ለማጉላት የተጠቀምኩት ምሳሌ ነው፡፡ መንሸራተት ማለት መርገብ ፣ መላላት፣ መዋለል ብቻ አይደለም፡፡ ጠርዘኝነትም ከሱንና መንሸራተት ነው፡፡ ጠባብነትም መንሸራተት ነው፡፡ በሱንና ስም ሰዎችን ከሱንና ማስወጣትም መንሸራተት ነው፡፡ የነገር ሁሉ ቀንጮው ኢስላም ነው፣ ሱንና ነው፡፡ ከዚያ በመለስ ያለ ሁሉ በየትኛውም አቅጣጫ ይውረድ፣ ወጠረም ረገበ ተንሸራቷል፡፡ የሙርጂአዎች ለጥፋት ቁንጮዎች ሁሉ በሙሉ ኢማን መመስከር መንሸራተት እንደሆነው ሁሉ የኸዋሪጆች በኢስላም ስም ሰዎችን ከኢስላም ማስወጣትም መንሸራተት ነው፡፡ የኢኽዋኖች በኢስላም ስም እየነገዱ ሁሉን ማግበስበስ መንሸራተት እንደሆነው ሁሉ የተኻለፋቸውን ሁሉ “ኢኽዋን” እያሉ የሚያስፈራሩ በጥባጮች አካሄድም ያለጥርጥር መንሸራተት ነው፡፡ ስለሆነም ኢኽዋኑ የተለያዩ ቅፅሎች ሲለጥፍልህ ያልደነገጥከውን ሌላው ትላንት እራሱ በነበረበት ማንነቱ “ኢኽዋኒ” እያለ ከኋላ በኩል በነገር ጩቤ ቢወጋህ አትደናገጥ፡፡ ይህ የአላህ ሱንና ነው፡፡ መቼም ቢሆን ከተቺዎች አትተርፍም፡፡ በርግጠኝነት መሀል ላይ ስትቆም ማዶና ማዶ ባሉት አንጃዎች በሌላኛው ማዶ ትፈረጃለህ፡፡ ሰለፊያ ቁርኣንና ሱንናን በቀደምቶች ግንዛቤ መረዳት እንጂ የነ እንቶኔ ጎጠኛ ስብስብ አይደለም፡፡
ትላንት ሰለፎቻችን፣ ዛሬም ታላላቅ ዑለማዎቻችን አንዳቸው በቢድዐ የፈረጁትን አካል ሌላቸው ሲከላከሉለት ያጋጥማል፡፡ ግና “እንዴት እኔን ተከትለህ አልፈረጅክም” ብለው አንዳቸው በሌላው ላይ አልዘመቱም፡፡ ለዚህ አንድ ሁለት አይደለም፣ አስር ሃያ አይደለም እጅግ በርካታ ምሳሌዎችን መዘርዘር ይቻላል፡፡ ለናሙና ያክል ታላላቅ የሱንና ተራራ የሆኑት እነ አቡ ዙርዐ፣ እነ ዙህሊ ታላቁን የሐዲሥ ሊቅ ኢማሙ ቡኻሪን በቢድዐ ወንጅለዋቸዋል፡፡ በአንፃሩ እነ ኢማሙ ሙስሊም ግን ለቡኻሪ ተከላክለውላቸዋል፡፡ ሆኖም ግን አንዳቸው በሌላው ላይ በመዝመት በዚህ ሳቢያ ጎራ ለይተው አልተናቆሩም፡፡ የቅርብ ታሪክ ብንመለከት ሸይኽ ሙቅቢል በሸይኽ ሙሐመድ ረሺድ ሪዳ ላይ በታዩ ከባባድ ጥፋቶች ሳቢያ በጥመት ገልጸዋቸዋል፡፡ በሌላ በኩል አልኢማም አልባኒ ረሒመሁላህ ይህንን የሙቅቢልን አቋም ተችተዋል፡፡ ይህም ከመሆኑ ጋር ግን ዛሬ በአንዳንድ ቂላቂሎች እንደሚታየው “ከሙብተዲዕ የተከላከለ ሙብተዲዕ ነው” በሚል ስሌት ሙቅቢል አልባኒን ከሱንና አላስወጡም፡፡ ሊዳፈሩም አይቻላቸውም፡፡ እርግጥ ነው ከሙብተዲዕ የሚከላከለው ሙብተዲዕ ነው፡፡ ግና “ሙብተዲዕ” የሚባለው ሰው ላይ የሚሰጠው ብይን አነታራኪ ሊሆን ይችላል፡፡ ወይም ለሱ የሚከላከለው አካል መዕዙር ሊሆን ይችላል፡፡ ይህን ስሌት የሚሰራው ደግሞ የመንደር ጎረምሳ ሳይሆን አርቆ አስተዋይ የሆነ ዐሊም ነው፡፡
ወላሂ ድሮ ለዐሊሞች ጭፍን ተከታይ እንዳይኮን ነበር የሚመከረው፡፡ ዛሬ ግን በዲን ስም ትንሽ ላንጎራጎረ ሁሉ ጭፍን ተሟጋች የሚሆነው በሽ ነው፡፡ ይሄ ሲበዛ ግብስብስነታችንን የሚያጋልጥ ነውር ነው፡፡ ብቻ ሳጠቃልል ደግሜ ደጋግሜ የምለው ማንም ይሁን ምን ሰው ላይ ጥገኛ አንሁን ነው፡፡ ያለበለዚያ የሚከተለን አስፈሪ አደጋ ነው፡፡
ነብዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዳሉት “የአደም ልጅ ልቦች ልክ እንደ አንድ ልብ ሁሉም በአርረሕማን ጣቶች መካከል ነው ያሉት፡፡ እንዳሻው ይገለባብ