ሀቅን ፍለጋ ከቁርዐንና ከሀዲስ አርባ ምንጭ ዪኒቨርስቲ AMU chamo Campus


Kanal geosi va tili: Efiopiya, Amharcha
Toifa: ko‘rsatilmagan


ዳዕዋ ሰለፍያ በአርባ ምንጭ AMUጫሞ ካምፓስ
ሃቅን ፍለጋ ከቁርዓንንና ከትክክለኛ ሃድስ በነዚያ ደጋግ ቀደምቶች ( በሰለፉነ–ሷሊሂን) አረዳድ !
"ከሃቅ በሗላ ጥሜት እንጅ ምን አለ! ? "
ስለዚህ ሃቅን ብቻ ተከተል !
ማሳሰቢያ: –ለማንኛውም አስተያየትዎ ከታች ባለው ቦት ያስቀምጡልን ጀዛኩሙላህ ኸይር
@JemalEndroAbuMeryem

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Kanal geosi va tili
Efiopiya, Amharcha
Toifa
ko‘rsatilmagan
Statistika
Postlar filtri


Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር) dan repost
*የዱንያ ነገር!!*
~
ዐሊይ ኢብኑል ሀይሠም እንዲህ ይላሉ:–

"አምሳያ ያላየሁለት የዘመን መገለባበጥ፣ የጊዜ መለዋወጥ አይቻለሁ።
★ የአልፈድል ብኑ ረቢዕ ንብረት በአንድ ሺህ ግመል ተጭኖ አይቻለሁ። ሌላ ጊዜ ግን ጠቅላላ ንብረቱ አንዲት ዘንቢል ውስጥ ሆና ተደብቄ አይቻለሁ። በውስጧ መድሃኒቶቹ ተጨምረው።

★ አልሐሰን ብኑ ሰህልን ደግሞ ጠቅላላ ንብረቱ አንዲት ዘንቢል ውስጥ ሆና ተመልክቻለሁ። ከዚያ ግን ንብረቱ በአንድ ሺ ግመል ላይ ተጭኖ አይቼዋለሁ።"

||

ዱንያ እንዲህ ነች። መርጋት የማታውቅ ወላዋይ!!
♣️ ሃያላን ይዋረዳሉ። ደካሞች ይነግሳሉ።
♣️ ሀብታሞች ጎዳና ላይ ይወድቃሉ። ምንዱባን በሰማይ ጠቀስ ህንፃ ይንፈላሰሳሉ።
♣️ ሳር ቅጠሉን የተፀየፈው ጨፍጫፊ አረመኔ አለም ጠባው ከአይጥ ጎሬ ሲያደፍጥ ታየዋለህ። የትላንቱ ተሳዳጅ ተራውን ሲያሳድድ ትመለከታለህ።

® ይሄው ነች ዱንያ!! ብልጭ ብላ ድርግም፣ ቦግ ብላ እልም የምትል። ሁሌ ሳቅ የለም! ሁሌ ድል የለም።
|
♣️ በድር ላይ ለያዥ ለገናዥ ያስቸገሩ፣ ጥጋብ ያስከራቸው ቁረይሾች፣ 70 መኳንንቶቻቸው ትላንት ሲያሳድዷቸው በነበሩ ሶሐቦች ሰይፍ ተበልተው፣ ሌላ 70 ደግሞ በምርኮ አስረክበው የሐዘን ማቅ ለብሰዋል። መካ በዋይታ ተንጣለች።
|
♣️ ኡሑድ ሌላ ቀን ነው። ሌላ ተራ!! አጋሪዎች የፈነደቁበት፣ እነ ሐምዛን፣ እነ ሙስዐብን ጨምሮ ከ70 በላይ ታላላቅ ጀግኖች ወድቀው ሌላ 70 የቆሰሉበት፣ አሳዝኝ ክስተት እውን የሆነበት ቀን። ሶሐቦች አካላቸው በስለት፣ ልባቸው በሐዘን ቢቆስል ጊዜ አላህ እንዲህ ሲል አሳሰባቸው: –

(إِنْ يَمْسَسْكُمْ قَرْحٌ فَقَدْ مَسَّ الْقَوْمَ قَرْحٌ مِثْلُهُ ۚ وَتِلْكَ الْأَيَّامُ نُدَاوِلُهَا بَيْنَ النَّاسَ)
"ቁስል ቢያገኛችሁ ሰዎቹንም መሰሉ ቁስል አግኝቷቸዋል፡፡ እናም እነዚህን ቀናት በሰዎች መካከል (በመልካምና በሌላ) እናቀያይራቸዋለን፡፡" [ኣሉ ዒምራን: 140]

|||

ዱንያ አመሏ ነው። ዛሬም እንዲሁ ናት።
ግን ማነው የሚማረው? ግን ማነው የሚመረምረው? ግን ማነው የዱንያን ከንቱነት ተገንዝቦ ለዘላለም ቤቱ ከልብ የሚጨነቀው?
እስከ መቼ ነው የምናንቀላፋው?
እስከ መቼ ነው የምንዘናጋው?
እስከ መቼ ነው በከንቱ የምንባዝነው?
ኢና ሊላሂ ወኢና ኢለይሂ ራጂዑን!
ኢላሂ ልብ ስጠን!
=
የቴሌግራም አድራሻ
https://t.me/IbnuMunewor


Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር) dan repost
Video oldindan ko‘rish uchun mavjud emas
Telegram'da ko‘rish
የችግሩ መንስኤ ክፋት ነው። የቅንነት መጥፋት ነው። እንጂ አገሪቱ የጋራ ናት፤ እኩል የመጠቀምም የመወሰንም መብት አላቸው የሚል እምነት ቢኖር ኖሮ ማንም በእብሪት እየተነሳ የራሱን ውሳኔ ባላሳለፈ ነበር። ዋናው ችግር ግን ከላይ ነው። ዋና ወሳኝ ክፍሎች ላይ ቁርጠኝነት ቢኖር ሁሉም ባይሆን እንኳ ብዙ ቦታዎች ችግሩ ይቀረፍ ነበር። ግን ምን ዋጋ አለው? መርፌ ከለገመ ቅቤ አይወጋም።
የጊዜ ጉዳይ እንጂ መብታችን ሳይሸራረፍ የሚከበርበት ጊዜ እንደሚመጣ እናምናለን፣ ኢንሻአላህ። ብቻ ትዝብት ነው ትርፉ። በታሪክ ጥቁር መዝገብ ላይ ስምን ከማኖር በበጎ መታወስ ይሻል ነበር። ዛሬ እያሳለፍነው ያለው ተጨባጭ ትናንት አባቶቻችን ምን አይነት ዘግናኝ ዘመን እንዳሳለፉ የሚጠቁም ነው፡፡ "ለዓለም ምሳሌ የሚሆን መቻቻል ... " የሚለው ፉገራ እንዴት እንደሚያስጠላ!

ሰውየው አብዛኞች ዘንድ የሌለ ሚዛናዊነት ስላሳየን አላህ ሂዳያ ይስጥልን። እናመሰግናለን።
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://t.me/IbnuMunewor


በአካውንቴ ላይ የገባ 5000 ብር (አምስት ሽህ ብር ) አለ የኔ ነው የሚል ማንኛውም አካል የባንክ ሪሲትና ስክሪን ሹት ይዞ መቅረብና መውሰድ ይችላል ::
0933519871
ጀማል እንድሮ

@JemalEndroAbuMeryem

https://t.me/daewaselefiyaArbaminch/15427


ሙርሰል/ አንሷር ሰይድ አቡል ሁማም dan repost
السلام عليكم ورحمةالله وبركاته


         የደዕዋ ኘሮግራም ግብዣ 

ውድና  የተከበራችሁ የአላህ ባሮች የፊታችን እሁድ  ማለትም  27 / 04 /2017 በውጫሌ  በአቡበከር ሲድቅ መስጅድ  ከጧቱ 2 ፡ 00 ሰአት ጀምሮ  ታላቅ የደዕዋ ድግስ  አዘጋጅተን ስንጠራችሁ በታላቅ ደስታ ነው ።

ተጋባዥ መሻይኾቻችን

*   👉  ሸይኽ ሙሀመድ አሚን ከደሴ

*  👉  ሸይኽ  በድሩድን ከደሴ

* 👉  ሸይኽ አህመድ አወቀ ከደሴ
      
* 👉 ሸይኽ  ሁሰይን አያሌው 

* 👉  ሙርሰል ሰኢድ ጨፌ

በውጫሌና አካባቢዋ የምትገኙ የአላህ ባሮች ኘሮግራሙን ላልሰሙ ወንድምና እህቶች በማሰማት የኘሮግራሙና የአጅሩ ተካፋይ እንድቶኑ በአላህ ስም እንጠይቃችኋል  ለሴቶችም በቂ ቦታ አለን  ።

በእለቱ በቦታው መገኘት ለማትችሉ  ኘሮግራሙ የሚተላለፍበት ግሩፕ 👇👇👇
https://t.me/abubeker_siddiq_mesjid


Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር) dan repost
Video oldindan ko‘rish uchun mavjud emas
Telegram'da ko‘rish
ቅናት አያረጅም!
~
የአዛንና የሶላት ሰዓት አጭር ነው። በጥላቻ ስትሞላ ግን 5ቱ ደቂቃ አምስት ሰዓት ይሆንብሃል። ሰፈራችን ላይ የሱብሕ አዛን 11፡25 አካባቢ ተደረገ። ሶላቱ ደግሞ ሩብ ጉዳይ አካባቢ። ሁሉም ቢደመር 20 ደቂቃ አይሞላም። ከማዶ የሚሰማው የቤተ ክርስቲያን ድምፅ ግን እስካሁን አልተቋረጠም። ይሄ የየሰፈሩ እውነታ ነው። ግን የራስ እንትን አይገማም።

የዚች ሃገር ትልቁ ችግር ቅናት ነው። ሙስሊም ተማሪዎችን በአለባበስ ምክንያት ከትምህርት ገበታ የሚገፋው አስተማሪ ከክልከላው ጀርባ ያደፈጠው ምክንያቱ ምቀኝነት ነው። ሌላው እንዲሁ ሽፋን ነው። የራሱን ማስለበስ ሲያቅተው። ሌሎች ላይ ይዘምታል። "ለሙስሊሞች ሒጃብ ከተፈቀደ እኛም ነጠላ እንለብሳለን" የሚለው የምቀኛ ሰፈር ልጆች መፈክርም የታወቀው በሽታ ነው፣ ቅናት። "ለሙስሊሞቹ መስገጃ ከተፈቀደ ለኛም መፀለያ ይፈቀድልን" የሚለው የምቀኝነት ልክፍትም የተለመደና ዝነኛ ህመም ነው።

ምቀኝነት እየተጋተ ያደገ አካል አድጎ አርጅቶ፣ በምርኩዝ እየሄደ፣ የሌሎችን ሃገራት ሁኔታ እያየ እንኳ አይለወጥም። እንዲያውም እየባሰበት ይሄዳል። ወደው አይደለም "ያዳቆነ ሰይጣን ሳያቀስ አይለቅም" የሚሉት። በቅናት የገረጣ ፊት በቅባት አይወዛም።
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://t.me/IbnuMunewor


ሙርሰል/ አንሷር ሰይድ አቡል ሁማም dan repost
Video oldindan ko‘rish uchun mavjud emas
Telegram'da ko‘rish
በመጨረሻም ፈነዳ‼

ሰሞኑን የመሬት መንቀጥቀጥ ሲስተዋልባቸው ከነበሩት አካባቢዎች አንዱ በሆነው ዱለቻ ወረዳ ዶፋን ተራራ ላይ ዛሬ የእሳተ ገሞራ ፍንዳታ ተከስቷል፡፡
✍መረጃዉ የዋሱ ሙሀመድ ነዉ።

♨️ ወላሂ በጣም አስደንጋጭ ክስተት ነዉ ‼️‼️

👉https://t.me/murselseid


Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር) dan repost
ወዳጄቼ ተወልጀ ባደግኩባት ከተማ የተከሰተ አሳዛኝ ክስተት ነው
እናት ቤቴ በሀዘን ተውጧል የቀረኝ አንዱን ልጄን አድኑልኝ ትላለች
የእርዳታ ጥሪ ልጆቼን ተነጠኩ አንዱን ገደሉብኝ አንዱን አድኑልኝ ትላለች እናታችን

ወንድማችን ኡመር ሀሰን ከአዲስ አበባ ወደ ጎጃም ሉማሜ ከተማ የአባቱ የቀብር ስነ ስራአት ላይ ለመገኘት በመሄድ ላይ እያለ መንገድ ላይ ባጋጠማቸው እገታ ታላቅ ወንድሙም ወዲያዉኑ የተገደለ ሲሆን እሱም እንደታገተ ይታወቃል አጋች አካላትም ልጁን ለመውሰድ የምትፈልጉ ከሆነ 2 ሚሊዮን ብር የጠየቁ ሲሆን ቤተሰቦቹም አቅም ስለሌላቸው የአቅማቹሁን እንድትረድን ስንል በፈጣሪ ስም እንማፀናለን

የአካውን ባለቤት ስም
ኢብራሂም ሀሰን (ታላቅ ወንድም)
ንግድ ባንክ
1000270990057

አቢሲንያ
131756399

ለበለጠ መረጃ 0934181613

የአቅማችሁን በማገዝ እና ይህንን መልእክት ሼር በማድረግ አግዙን።

መልእክቱ ከወንድማችን Hussen Oumer የተወሰደ ነው።


Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር) dan repost
ከ1400 ዓመታት በፊት ትግራይ ውስጥ ከዛሬው የተሻለ የሃይማኖት ነፃነት ነበር። መካ ውስጥ በገዛ ወገኖቻቸው የተገፉ የተንገላቱ ሙስሊሞች ባህር አቆራርጠው የተሰደዱት ወደ ሐበሻ ነበር። "እዚያ ከሱ ዘንድ ማንም የማይበደልበት ፍትሃዊ መሪ አለ" ተብሎ በነብዩ ﷺ የተመሰከረለት ድንቅ መሪ ነበር፣ ነጃሺ። ያኔ በግዛቱ ውስጥ ማንም እንዳይነካቸው ዋስትና ሰጥቷቸው ነበር ለስደተኛዎቹ ሙስሊሞች።
ዛሬ ከ1400 ዓመታት በኋላ በ21ኛው ክ/ዘመን ሙስሊም ለጋ ልጆች፣ ከሩቅ የመጡ እንግዶች ሳይሆኑ ተወላጆች፣ ሻሽ ካልጣላችሁ ተብለው በእምነታቸው ተለይተው ከትምህርት ገበታ ተገፍተዋል። ይበልጥ መሰልጠን ሲገባ ጭራሽ እንደ ግመል ሽንት ወደ ኋላ መሄድ የሚያሳዝንም፣ የሚያሳፍርም፣ የሚገርምም ነው።
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://t.me/IbnuMunewor


Abu_Oubeida~channel dan repost
🔻ስራ ፈት'ቶ መቀመጥ እንኳን ለአንድት ሴት ልጅ አይደልም ለወንድም ከባድ ነው ያውም በሰው ሀገር፤ሀገሩም ሰውም አድስ በሆነበት።ቢርብህ እራበኝ አትል ቢቸግርህ ቸገረኝ የማትልበት።ብቻ ከባድ ነው።በየትኛውም ሀገር ሁነው በስራ ማጣት እየተንገላቱ ያሉ እህት ወንድሞችን አላህ የተሻለ ስራ ይስጣቸው።

➡️ታዳ ለብዙ ጊዜያት በስራ ማጣት ከተንገላቱት ውስጥ አንዷን "ኳተር" ላይ ያለች እህታችንን በጀመአችህ ስራ አፈላልጋችሁ ታስገቧት ዘንዳ ትብብራችሁን እንሻለን።

➡️ኳተር ላይ የትኛውም አካባቢ ይሁን ተሸፍኖ"ኒቃብ"ለብሶ፡ መስራት የሚፈቅዱ የሁኑ ስራ ያለበትን ካገኛችሁ ከስር ባለው
Username አሳውቁን ምንዳ ከፋዩ አሏህ ነው።

=>@Umu_Abdillah


Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር) dan repost
የምንችለውን እናስተምር
~
ኢብኑል ሙባረክ - ረሒመሁላህ - "ከእድሜህ አንድ ቀን ብቻ ነው የቀረህ ብትባል ምን ትሰራ ነበር?" ተብለው ተጠየቁ።
"ሰዎችን አስተምር ነበር" አሉ።
[አልመድኸል ኢለሱነን፣ አልበይሀቂይ፡ 309]
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://t.me/IbnuMunewor


Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር) dan repost
#አስቸኳይ የቁርኣን አስተማሪ ይፈለጋል
መርከዝ አት ተውሒድ የቁርኣን ሒፍዝ አስተማሪዎችን አወዳድሮ መቅጠር ይፈልጋል
~ቁርኣንን በጥሩ ሁኔታ የሐፈዘ እና ጠንካራ ሙራጀዓ ያለው
~የቁርኣን ሸሃዳ ያለው ቢሆን ይመረጣል
~መሰረታዊ የዐቂዳ እና የፊቅህ እውቀት ያለው
~ብዛት: 1
~ፆታ: ወንድ
~የቅጥር ሁኔታ: አዳሪ ሙሉ ሰዓት
ከላይ የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ ኡስታዞች ከታች ባሉት አድራሻ ያናግሩን
@durise


Video oldindan ko‘rish uchun mavjud emas
Telegram'da ko‘rish
ታላቅ የምስራች ለእህቶቻችን

በእህታችን ኡሙ ሙንዚር ቁርአን ከቃኢዳ እስከ ሂፍዝ መቅራት ለምትፈልጉ በውስጥ ግቡና አናግሯት !

@Umumunzirazg32

መስፈርት
1 አለማቆራረጥ በቋሚነት መቅራት የምትችል
2 ዳታ ወይንም ዋይፋይ በሚሰራበት ቦታ መገኘት የምትችል


በቁርአንም በመንሃጅም ጠንካራ እህታችን ነች አላህ ይጨምርላት አላህ ኢኽላሱንም ይወፍቃት !


https://t.me/daewaselefiyaArbaminch/15417


Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር) dan repost
Video oldindan ko‘rish uchun mavjud emas
Telegram'da ko‘rish
በነገራችን ላይ እንዲህ አይነት መልእክቶችን ማበረታታት ይገባል። ክፋት የሚናገሩትን ብቻ እያራገብን ሁሉንም ጥግ ማስያዝ አይጠቅመንም። እየታሰበበት።
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://t.me/IbnuMunewor


🌏Abu Hafsua [አቡ ሐፍሷ] dan repost
አረ ተዉ ወንድ ነህ

~ዘዴ ፈጥረህ ሲስተም ዘርግተህ በረቀቀ በዘዴ ከአረብ ሀገር ሴት ብር ከምታስልክና ወሻሽተህ ከምትቀበል ስራ ፈጥረህ አሰራም? ወንድ ነህ በዛም በዚህም ተፍ ተፍ አትልም?

ደሞኮ ለመቀበል የሚጠቀሙት ዜዴያቸው ሲያስጠላ

~ኪታብ ልገዛ ነው
~እኛ ሰፈር መድረሳ፣መስጁድ እየተሰራ ትንሽ ጎድሎን
~እናቴ፣አባቴ፣እህቴ ወንድሜ ታሞ
~እየተማርኩ ነው የሚረዳኝ የለም
~ታምሜ፣ቤት ኪራይ የምከፍለው አጥቼ ሊያውወጡኝ ነው። መሰል ነገር.

© ልብ በሉ እውነት የሆነውን አላልኩም ።ግን ብዙ ውሸቶችና ማጭበርበሮች በእነዚህ መስመርና መሰል ነገሮች ነው እየተፈጠሩ ያሉት። እየጠየቃችሁ እያጣራችሁ። ሌብነቶች አይነታቸውን ቀይረው በብዙ መንገድ እየመጡ ነው። ማጣራትና ማረጋገጥ ግድ ይላል። ልቅ የሆነ ማመን አያዋጣም።
@AbuHafsaYimam


ምክር ለተማሪዎች
🎙ኡስታዝ ኢብኑ ሙነወር

6ኪሎ ሙስሊም ተማሪዎች ጀመዓ
🗓19/04/2017

https://t.me/daewaselefiyaArbaminch/15412


ፆታዊ ፈተናን መከላከል
🎙ኡስታዝ አቡል ዓባስ ናሲር ሙሐመድ

6ኪሎ ሙስሊም ተማሪዎች ጀመዓ
🗓19/04/2017:

https://t.me/daewaselefiyaArbaminch/15413


ፆታዊ ፈተናን መከላከል
🎙ኡስታዝ አቡል ዓባስ ናሲር ሙሐመድ

6ኪሎ ሙስሊም ተማሪዎች ጀመዓ
🗓19/04/2017:

https://t.me/daewaselefiyaArbaminch/15411?single


♨️ተዉሂድን ለየዋሁ የገጠር ማህበረሳባችን ልናደርሰዉ ይገባል‼️

👉ዉሃቢያዎች ነቢዩን አይወዱም
👉ኡለማዎችን አያከብሩም
👉ዱአ አይወዱም

💥እያሉ አህባሾች ለሚያነሷቸዉ ዉሸቶችና ማምታቻዎች መጠነኛ ዳሰሳ ተደርጎበታል

👉ዛሬ በሀይቅ ከተማ በወንድማችን ዘህረዲን ሰኢድ የሰርግ ፕሮግራም ላይ የተደረገ።

🎤በሙርሰል ሰይድ ጨፌ 17/4/2017
👉https://t.me/murselseid




Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር) dan repost
የደዕዋ ፕሮግራም
~
ዛሬ ቅዳሜ ቀጥታ ከዙህር ሶላት በኋላ
ቦታ፦ አፍንጮ በር ፣ አቅሷ መስጂድ

ተጋባዥ እንግዶች
አቡል ዐባስ
እና
ኢብኑ ሙነወር

በ 6ኪሎ ሙስሊም ተማሪዎች ጀማ0 የተሰናዳ

20 ta oxirgi post ko‘rsatilgan.