በሶሪያ ኦርቶዶክስ ያዕቆባዊት ቤተክርስቲያን የሕንድ ሜትሮፖሊታን የነበሩት ብፁዕ አቡነ ሞር ባስልዮስ ቶማስ ቀዳማዊ ከዚህ ዓለም ድካም ዐረፉ
ብፁዕ አቡነ ሞር ባስልዮስ ቶማስ ቀዳማዊ እ.ኤ.አ ሐምሌ 22 ቀን 1929 ዓ.ም ቡቸንክሩዝ በተባለ የሕንድ ግዛት የተወለዱ ሲሆን እ.ኤ.አ ከሐምሌ 26 ቀን 2002 ዓ.ም ጀምሮ በሶርያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ሥር የምትተዳደረውን የሕንድ ቤተ ክርስቲያን ለበርካታ ዓመታት በሊቀ ጵጵስና መርተዋል።
ብፁዕነታቸው በዕድሜና በሕመም ምክንያት ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ ዕረፍት በማድረግ ሕክምናቸውን ሲከታተሉ የቆዩ ሲሆን በዛሬው ዕለት አመሻሽ ላይ በሕንድ ኮቺ በተወለዱ በ95 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም ድካም ዐርፈዋል።
በብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ ሞር አግናጢዮስ ኤፍሬም ዳግማዊ፣ ለሶርያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ አባላት፣ ለመላው የቤተ ክርስቲያን አባላት፣ ቀሳውስትና ምእመናን በሙሉ መጽናናትን እንመኛለን።
የብፁዕነታቸው በረከት አይለየን !!!
© ተሚማ
#ድምፀ_ተዋህዶ
https://t.me/dmtse_tewaedo