🎤✨ድምፀ ተዋህዶ✨🎤


Kanal geosi va tili: Efiopiya, Amharcha
Toifa: Musiqa


ድምጻችን ለተዋህዶ ሐይማኖታችን ለኢትትዮጲያ አገራችን

የእግዚአብሔር ሰላም የእናታች የቅድስት ድንግል ማርያም ምልጃና ፀሎት የመላእክት ጥበቃና የቅዱሳን በረከት ከናንተ
ጋር ይሁን አሜን!

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Kanal geosi va tili
Efiopiya, Amharcha
Toifa
Musiqa
Statistika
Postlar filtri


🙏ኦርቶዶክሳዊ ዝማሬ🙏 dan repost
🗓 ነገ ማለትም
ዕለት:- ረቡዕ
#ቀን:- ጥር ፲፬ ፳፻፲፯ ዓ.ም
በቅድስት ቤተክርስቲያናችን


አቡነ አረጋዊ (አመታዊ)
አባ ጳኩሚስ ፣ ቅዱስ ገብረ ክርስቶስ ፣ አቡነ ተስፋ ጽዮን ፣ ሰማዕቱ አብሮኮሮስ ፣ አባ ዘሚካኤል ፣ ሙሴ ጸሊም


አክብረን እና አስበን እንውላለን

እስትንፋስ ያለው ሁሉ እግዚአብሔርን ያመስግን( መዝ 150 - 6 )


✝️ለባለ ማህተቦች✝️ሼር ያድርጉ↗️

✨✨✨✨✨✨✨
✝️#ኦርቶዶክሳዊ_ዝማሬ✝️
✨✨✨✨✨✨✨


​​​​✝️ጾመ ገሀድ✝️


ከዘጠኙ ዓበይት የጌታ በዓላት ሁለቱ የልደትና የጥምቀት በዓላት ተጠቃሾች ናቸው  በሁለቱ በዓላት ቀን ክርስቲያን የሆነ ሁሉ በኀዘን ማሳለፍ እንደሌለበት ቅዱሳት መጻሕፍት ይናገራሉ ምክንያቱም የክርስቶስ ልደትና ጥምቀት የዕዳ ደብዳቤያችን የተቀደደባቸው የድኅነታችን መሠረት የተጣለባቸው ዐበይት በዓላት  ስለሆኑ ነው እነዚህ በዓላት በረቡዕና በዓርብ ቀን ከዋሉ አስቀድመን በዋዜማው ለውጥ አድርገን እንጾማቸዋለን ልደት ረቡዕ ከሆነ ማግሰኞ በዋዜማው፣ ዓርብ ከሆነ ሐሙስ በዋዜማው እስከምሽቱ አንድ ሰዓት (13 ሰዓት) እንጾማቸዋለን በሌሎችም ቀናት በዋዜማቸው በየዓመቱ ይጾማሉ ቀናቱ ሁለት ቢሆኑም  ቁጥራቸው ግን ከሰባቱ አጽዋማት አንዱ ተብለው ነው የሚቆጠሩት፡፡

ገሃድ ሁለት መጠሪያ ስሞች አሉት ገሃድና ጋድ፡፡ ገሃድ ማለት መገለጥ መታየት መታወቅ ማለት ነው ተገለጠ ታየ ታወቀ የተባለውም ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው ምንም ከዚያ በፊት አምላክነቱ የተገለጠባቸው ብዙ መንገዶችና ተአምራት ቢኖሩም አብ በደመና ሁኖ የምወደው ልጄ ይህ ነው በማለት፣ መንፈስ ቅዱስም በርግብ አምሳል ወርዶ በራሱ ላይ በመቀመጥ የክርስቶስ አምላክነት የተገለጠበት ዕለት ስለሆነ ገሀድ መገለጥ ተብሎ ተሰይሟል

➦በሌላም በኩል ጋድ ማለት ለውጥ ማለት ነው ልደትና ጥምቀት ረቡዕና ዓርብ ሲሆኑ ለውጥ ሁኖ የሚጾምበት ማለት ነው ስለዚህ ገሀድ ስንል የክርስቶስን አምላክነት በዕለተ ጥምቀት መገለጥ፣ ጋድ ስንል ደግሞ ለዓርብና ለረቡዕ ጾም ለውጥ ሁኖ የተጾመውን ጾም ማለታችን ነው፡፡ ይህንን ጾም ጥር 10 ቀን የሚነበበው ስንክሳር እንዲህ ሲል ይገልጸዋል፡፡

   

  
🕯 ✝️መልካም በዓል✝️✨🕯

✨✨✨✨✨✨
✝️#ድምፀ_ተዋህዶ✝️
✨✨✨✨✨✨


🗓🤲ሰላም ለሕላዌክሙ ዘአይትአወቅ እምጥንቱ ወዘኢይትረአይ ተፍጻሜቱ ሥሉስ ቅዱስ ዘኢትመውቱ እንዘ ሠለስቱ አሐዱ ወእንዘ አሐዱ ሠለስቱ ለዕበይክሙ ፍፃሜ አልቦቱ 👉

       
መልክአ ሥላሴ


✝️ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ✝️

📣 እንኳን ለአጋዕዝተ ዓለም ሥላሴ በዓል በሰላም አደረሳችሁ አደረስን 🙏

👉 ጥር ፯(7) በዓለ ሥሉስ ቅዱስ ሶል ጴጥሮስ ዘሮሜ ወኢፍራ ወአትንያኖ ወሉያ ወመይልን ወመሰላዮስ ወማርትያ 👉

✝️ ዘነግህ ምስባክ ✝️

ሣህሉ ለእግዚአብሔር መልአ ምድረ
ወበቃለ እግዚአብሔር ጸንዓ ሰማያት
ወእምእስትንፋስ አፉሁ ኵሉ ኀይሎሙ

✤ ትርጉም ✤

የእግዚአብሔር ቸርነትን ምድርን መላች
በእግዚአብሔር ቃል ሰማዮች ጸኑ
ኀይላቸውም ሁሉ በአፉ እስትንፋስ

             መዝ ፴፪-፭
                    32  5

✤ ወንጌል ✤

ማቴ ም ፳፰ ቁ ፲፮-ፍ.ም
            28    16  ፍፃሜው

✝️ የቅዳሴ ምንባባት ✝️

ቈላስ ም ፪ ቁ ፲-፲፯
፩ ዮሐ ም ፪ ቁ ፳፭-ፍ.ም
ግብ.ሐዋ ም ፳፪ ቁ ፯-፳፪

✝️ ምስባክ✝️

የሐዩ ወይሁብዎ እምወረቀ ዓረብ
ወዘልፈ ይጼልዩ በእንቲአሁ
ወኵሉ ዓሚረ ይድኀረዎ

✝️ ትርጉም ✝️

እርሱ ይኖራል፤ከዐረብ ወርቅ ይስጡታል
ሁልጊዜ ወደርሱ ይጸልያሉ
ዘወትርም ይባረኩታል

             መዝ ፸፩-፲፭
                     71  15

❖ ወንጌል ❖

ማቴ ም ፪ ቁ ፳፩-ፍ.ም
           2     21   ፍፃሜው


✝️ቅዳሴ✝️

ዘእግዚእነ

" በሱራፌል በኪሩቤል የምትቀመጥ አምላካችን እግዚአብሔር የምትመለከት ወንዶቹንና ሴቶቹን ባሮችህን ልጆቻቸውንም ባርክ "

        ቅዳሴ እግዚእነ
          ም ፩ ቁ ፸፰
              1     78


📣📣📣📣📣📣📣📣📣📣

በዓሉን በዓለ ምህረት በዓለ ፀጋ በዓለ በረከት ያድርግልን አምላካችን መድኃኒታችን ዘላለም ሥላሴ በቸርነቱ ይማረን እናታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በምልጃዋ አትለየን ፍቅሯን በልባችን ጣዕሟን በአንደበታችን ታሳድርብን በዕፀ መስቀሉ ይባረከን ይጠብቀን ቤተክርስቲያን ቅድስትን በረድኤት ይጠብቅልን በየሰዓቱ በየደቂቃው ጠባቂ መላዕክት አያሳጣን በቅዱሳኑ ፀሎት ይማረን ዕጣነ አሮን ፀሎተ ምናሴ የተቀበለ ዘላለም ሥላሴ የኛንም ፆም ፀሎት ምስጋና በብሩህ ገጽ ይቀበልልን በዓል ተከትሎ ከሚመጣ መቅሠፍት አምላክ ቅዱሳን ይሰውረን ይጠብቀን ለሃገራችን ስላም ለህዝባችን አንድነትን ይስጥልን ለብርሃነ ጥምቀቱ በሰላም ያድርሰን ህንጻ ስናዖርን ያፈረሰ ዘላለም ሥላሴ የኃጢአተኛን ድልድይ ዘመናችንን ይባርክል


 ✨✨✨✨✨✨
✝️#ድምፀ_ተዋህዶ✝️
✨✨✨✨✨✨


" ልጆቻችን በሰላም መኖር እንዲችሉ፣ በጦርነት እየተሰቃዩ የሕመማቸውን ልክ መናገር የማይቻለን የኦሮሚያና የአማራ ክልል ነዋሪዎች ሰላምን እንዲያገኙ ጥሪ እናስተላልፋለን " - ቅዱስነታቸው

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ  ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት  ወቅታዊ  ጉዳዮችን አስመልክተው አባታዊ የሰላም ጥሪ አስተላለፉ።

ቅዱስነታቸው ፤ በሀገራችን በልዩ ልዩ አካባቢዎች ያሉ ጦርነቶች እንዲቆሙ ጥሪ አቅርበዋል።

" ልጆቻችን በሰላም መኖር እንዲችሉ፣ በጦርነት እየተሰቃዩ የሕመማቸውን ልክ መናገር የማይቻለን የኦሮሚያና የአማራ ክልል ነዋሪዎች ሰላምን እንዲያገኙ አባታዊ ጥሪ በድጋሚ እናስተላልፋለን " ብለዋል።

ቅዱስነታቸው ፤ በትግራይ ክልል ያለው የአስተዳዳሪዎች አለመግባባት በሕዝቡ ላይ ተጨማሪ ችግርና ጭንቀት እያመጣ መሆኑን ጠቁመዋል።

" በትሕትና መንፈስ እርስ በርስ መገናዘብ ተፈጥሮ ዕረፍት ያጣው ሕዝብ መረጋጋት እንዲችል ታደርጉ ዘንድ አደራችን የጠበቀ ነው " ብለዋል።

በተጨማሪም ቅዱስነታቸው በትግራይ ክልል ስለሚገኙ የሃይማኖት አባቶች ጉዳይ በአባታዊ የሰላም ጥሪ መልዕክታቸው አንስተዋል።

" መበደላችሁን እናውቃለን ፣ በኀዘናችሁ ሰዓት አብረን መቆም ባለመቻላችን ማዘናችሁም እርግጥና ተገቢ ነው " ያሉት ቅዱስነታቸው " ነገር ግን ሁሉም ነገር የሚካሰው በእርቅ ሲሆን እኛ የገፋነውን እርቅ ዓለም ሊቀበለው ስለማይችል፤ በእጃችንም የያዝነው መስቀለ ክርስቶስ የሰላም ዓርማ ነውና ልባችሁን ለሰላም፣ ለአንድነት እንድታዘጋጁ እንጠይቃለን " ብለዋል።

በሌላ በኩል ቅዱስነታቸው በመሬት መንቀጥቀጥ እየተጨነቁ ላሉ እና ስለተጎዱ ልጆቻቸው መልዕክት አስተላልፈዋል።

" የመሬት መንቀጥቀጥ ባለበት አካባቢ እየተጨነቃችሁ ያላችሁ ልጆቻችን ረድኤተ እግዚአብሔር ከእናንተ ጋር እንዲሆን ቤተ ክርስቲያን በጸሎት የምታስባችሁ መሆኑን እየገለጽን መላው ኢትዮጵያውያን ለጉዳቱ ተጋላጭ በሆኑ አካባቢዎች ለሚኖሩት ወገኖቻቸው አቅማቸው በፈቀደው መጠን ድጋፍ ያደርጉ ዘንድ አባታዊ መልእክታችንን በእግዚአብሔር ስም እናስተላልፋለን " ብለዋል።

(የቅዱስነታቸው ሙሉ መልዕክት ከላይ ተያይዟል)



✨✨✨✨✨✨
✝️#ድምፀ_ተዋህዶ✝️
✨✨✨✨✨✨


✨የጌታ ልደት✨
    🪔🪔🪔🪔

🗓የጌታ ልደት ክርስቲያናዊ ክብረ በዓል
ከጾም መጨረሻ በኋላ የሚመጣ መልካም ቃላትና በጎ ፈቃድን የምንለዋወጥበት ቀን ብቻ አይደለም፡፡ነገር ግን እውነተኛ በዓል ከደስታውና ከአከባበሩ ጋር በዓሉን ተከትሎ የሚመጣ መልካም ነገርና ጥበብን ሁሉ የምንማርበት ነው፡፡ለመሆኑ ከበዓላት የምንማረው በጎ ነገር ምንድን ነው?                        ፩.ትህትና   
  ከገና በዓል የምንማረው ታላቅ ነገር ትህትና ነው፡፡ጌታችን በቤተልሔም ይሁዳ በከብቶች በረት በመወለዱ ምሳሌውን ትቶልናል፡፡ጌታችን ሲወለድ ብዙ አጀብና ክብር አልነበረም፡፡ወደ ዓለም ሲመጣ ለሁሉም እየታየ በኪሩቤልና በሱራፌል ሠረገላ ላይ ተቀምጦ ለዓለሙ ሁሉ እያወጀ መሆን ይገባው ነበር፡፡ነገር ግን ለውጫዊ ዕይታ ትኩረት አልሰጠም፡፡በቀዝቃዛ ወራት በብርድ ቀን በሌሊት ማንም ትኩረት ሊሰጥ በማይችለው በከብቶች ግርግም ተወለደ፡፡የሚለብሰው በቂ ልብስ አልነበረውም፡፡ የጌታ በከብቶች በረት መወለድ ትህትናን የምንማርበት ትልቁ ትምህርት ቤት ነው፡፡ትሕትናው ባይኖር ኖሮ ይህ በዓል ሰማያዊ መንፈሳዊ የሆነ ምስጢሩ ባልተገለጠ ነበር፡፡የጌታን ትሕትና ገንዘብ ለማድረግ ሞክር፡፡ በሥጋዌው ራሱን ዝቅ አደረገ የባሪያ መልክ ይዞ በሰው አምሳል ተገለጸ፡፡/ፊል 2፡8/፡፡ትሕትናን ከጥልቁ እንፈልገው እንዴት እንደምንጠቀም እንወቅበት መድኃኒታችን በሥጋዌው ያደረገው ይኼንን ነው፡፡                           ፪.የዋኅነት       
  ከልደት በዓል የምንመለከተው ጌታ ፈቃዱን የገለጸው ለተወሰኑ ወገኖች ነው፡፡ሌሎች ምንም እንኳን በሥልጣን ከፍ ከፍ ያሉ ቢሆኑም አልተመረጡም፡፡ለምሳሌ ጌታ ልደቱን የገለጸው ለእረኞች ነው፡፡ሌሎች ጸሐፍት፣ ፈሪሳውያን ካህናትና ሽማግሌዎች ይህንን መልካም ዜና አላዩም፡፡ምክንያቱም የእግዚአብሔር ምሥጢር የሚገለጸው ልበ ንጹሐን ለሆኑ ወገኖች ስለሆነ ነው፡፡ሰብዓ ሰገልና እረኞች የሰሙትን ነገር አመኑ፡፡የዋኻንም ነበሩ፡፡ ታላላቅ ሰዎች እንዲህ ያለ የተዘጋጀና የዋኅ የሆነ ልብ አልነበራቸውም፡፡ ሄሮድስ ይሄንን ሁኔታ በሰማ ጊዜ ውሸትንና ምክንያትን በመፈለግ ለሥልጣኔ ባላንጣ ነው ብሎ ስላሰበ የማሳደድ ዕቅድን አወጣ፡፡ታዲያ እኛ ከየትኛው ወገን ነን ክርስቶስን በየውኀት ከሚቀበሉት ወይስ ከሚያሳድዱት?          
ቅድስት ድንግል ማርያም የዋኅ ልብ የነበራት ነበረች፡፡ስለ እርሷ ከጌታ የተነገረላትን አመነች፡፡ድንግል ሳለች ልጅ እንደምትወልድ አመነች፡፡ዮሴፍ በሕልም የጌታ መልአክ የነገረውን ነገር አመነ፡፡እራሳችንን እንዲህ ብለን እንጠይቅ ‹‹የምንመላለሰው በየዋኅ ልብ ነውን? ወይንስ የተወሳሰበና የሚጠራጠር ልብ ነው ያለን? መልሱን ለእናንተ ትተናል፡፡ እኛ ግን እንደ እርግብ የዋሓን ሁኑ የሚለውን የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል እናስታውስዎት፡፡

                                                                     ✍️ብፁእ ወቅዱስ  አቡነ ሺኖዳካከ


✨✨✨✨✨✨
✝️#ድምፀ_ተዋህዶ✝️
✨✨✨✨✨✨


ብፁዕ አቡነ ዳንኤል ዐረፉ

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን በ5ኛው ኢትዮጵያዊው ፓትርያርክ በብፁዕ አቡነ ጳውሎስ  ነሐሴ 22 ቀን 1997 ዓ.ም ከተሾሙ 17 ጳጳሳት አንዱ የሆኑት ብፁዕ አቡነ ዳንኤል ዐረፉ።

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የድሬዳዋ እና የጅቡቲ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳሳት የነበሩት ብፁዕ አቡነ ዳንኤል ትናንት ከምሽቱ አምስት ሰዓት አካባቢ በመንበረ ፓትርያርክ በሚገኘው ማረፊያ ክፍላቸው እንዳረፉ ለማወቅ ተችሏል። 
ብፁዕነታቸው በሰሜን አሜሪካ ለረጅም ዓመታት አገልግሎት በመስጠት እንደሚታወቁ የገለጠው ዐደባባይ ሚዲያ የልብ ሕመም እንዳለባቸው ሐኪም ሲነግራቸው በዚህ ዕድሜዬ ቀዶ ጥገና አይደረግልኝም ወደ አገሬ ሔጄ ለአገሬ አፈር ልብቃ ማለታቸውን ዘግቧል።
የብፁዕነታቸው በረከት ይደርብን።
ነፍሳቸውን በቅዱሳን እቅፍ ያሳርፍልን።


✨✨✨✨✨✨
✝️#ድምፀ_ተዋህዶ✝️
✨✨✨✨✨✨


🗓" እኔ በእግዚአብሔር ፊት የምቆመው ገብርኤል ነኝ " (ሉቃ 1:19)


        
✝️ ቅዱስ ገብርኤል ማን ነው ???

❤️ ገብርኤል:- ማለት የእግዚአብሔር አገልጋይ ማለት ነው ከሰባቱ ሊቃነ መላእክት አንዱና ከሊቀ መላእክት ከቅዱስ ሚካኤል ቀጥሎ ስልጣን የተሰጠው ታላቅ መልአክ ነው።

​​እንኳን አደረሰን አደረሳችሁ❣️

👑" እኔ በእግዚአብሔር ፊት የምቆመው ገብርኤል ነኝ " (ሉቃ 1:19)


         ✝️ ቅዱስ ገብርኤል ማን ነው ???

❤️ ገብርኤል:- ማለት የእግዚአብሔር አገልጋይ ማለት ነው ከሰባቱ ሊቃነ መላእክት አንዱና ከሊቀ መላእክት ከቅዱስ ሚካኤል ቀጥሎ ስልጣን የተሰጠው ታላቅ መልአክ ነው።

❤️ለእመቤታችን ለቅስተ ቅዱሳን ለድንግል ማርያም የዓለም ድኅነትን የሚሆን ልጅ እንደ ምትወልድ በታላቅ ምስጋና ያበሠረ! የነቢያትንም ትንቢት የፈጸመ ድንቅ መልአክ ነው።

✨🌿 ለካህኑ ዘጋርያስ የመጥምቀ መለኮት የቅዱስ ዮሐንስን መወለድን ያበሰረ  አብሳሪ መልአክ ነው።

🌹✨ሐምሌ  19  ቀን  ህጻኑን ቅዱስ ቂርቆስን እና እናቱ ቅድስት ኢየሉጣን ከእቶን እሳት ያዳነበት ታላቅ ቀን ነው።

🌹🍃ታህሳስ  19  ቀን  ሃያሉ መልአክ ቅዱስ ገብርኤል ሠልስቱ ደቂቅን ከእቶን እሳት ያዳነበት ታላቅ ቀን ነው።

✝️ ዳንኤልን ከአናብስት አፍ ያዳነም ሃያል መልአክ ነው ሰብአ ሠገልን በኮከብ ምልክት የመራ መልአክም ነው በጨለማ በሞት ጥላ ውስጥ ለሚኖሩ ብርሃንን የገለጸ ሃያል መልአክ ነውና ክብር እና ምስጋና ይገባዋል።

✝️ የመልአኩ የቅዱስ ገብርኤል በረከት፣ ፍቅር፣ ምልጃ አይለየን ሀገራችንን ሠላም ያድርግልን።


🌺እንኳን አደረሳችሁ✝️
🙏

✨✨✨✨✨✨
✝️#ድምፀ_ተዋህዶ✝️
✨✨✨✨✨✨


🗓እንኳን ሃያሉ መልአክ ቅዱስ ገብርኤል
ሠልስቱ ደቂቅን ከእቶን እሳት ላዳነበት ታላቅ ቀን በሰላምና በጤና አደረሳችሁ።


✨✨✨✨✨✨
✝️#ድምፀ_ተዋህዶ✝️
✨✨✨✨✨✨


#ድምፅ_መስጠት_ተጀመረ!

#አንቴክስ_ፉድ_ኤይድ_ፕላስ ባዘጋጀው BIWs prize ብፁዕ አቡነ ኤርምያስን የሰላም ዘርፍ እጩ ተሸላሚ አድርጓቸዋል።

ብፁዕ አቡነ ኤርምያስ በሰላም ዘርፍ ከአምስት እጩዎች ውስጥ ተክትተዋል የዘርፉ አሸናፊ ከሆኑ #10ሚሊየን ብር ይሸለማሉ!!!

ብፁዕነታቸውን BIWን በማስቀደም ኮድ08 (BIW08) በማስገባት በSMS 9355 ላይ አሁኑኑ ይምረጡ!!! 

ድምጽ መስጠቱ እስከ ሐሙስ ታህሳስ 17/2017 ዓም ከቀኑ 6፡00 ሰዓት ድረስ ብቻ ይካሄዳል!

በSMS 9355 ላይ BIW08 በማለት ብፁዕነታቸውን አሁኑኑ  ይምረጡ!!!

#10ሚልዮን #አንቴክስ #ፉድኤይድፕላስ #biwsprize #BTM #ብፁዕአቡነኤርምያስ  #ይምረጡ

Vote Abune Ermias now for the BIWs prize!

#AbuneErmias
#10million #BIWS2024 #Prize  #ANTEXETHIOPIA  #ANTEXTEXTILE  #FOODAIDPLUS #BESHATUTOLEMARIAMMULTIMEDIA


🗓  😊ታፍራለች ⭐️
ልጅቷ ባል ትፈልጋለች ሃይማኖቷ በሚፈቅደው ሕግና ስርዓት መሠረት ዘወትር ወደ እግዚአብሔር ትጸልያለች።

ዳሩ ግን አንድም ቀን እግዚአብሔርን በቀጥታ ጥሩ ባል ጥሩ ትዳር እንዲሰጣት ለምናው አታውቅም። ለምን ቢባል ታፍራለች። "እግዚአብሔር እንዴት ስለ ባል ይጠየቃል?"
የሚል ደካማ አመለካከት አላት። እግዚአብሔርንም ጥሩ ባል ስጠኝ ብላ መለመን ያሳፍራታል። እንዳትተወው ደግሞ ባል ያስፈልጋታል። ታድያ አንድ ቀን ሲጨንቃት እንዲህ ብላ ጸለየች፤ "ፈጣሪዬ እባክህን ለእናቴ ጥሩ አማች ስጣት"

በእርግጥ እግዚአብሔርን ስንለምን "የምትለምኑትን አታውቁምን" ተብለው እንደተወቀሱት ሰዎች እንዳንሆን መጠንቀቅ አለብን። ለብዙዋች ግን የሚያሳፍረው ሳያሳፍራቸው፤ የማያሳፍረው ያሳፍራቸዋል

    📣📣📣📣📣
#ድምፀ_ተዋህዶ
     📣📣📣📣📣


🗓 ነገ ማለትም
#ዕለት:- ረቡዕ
#ቀን:- ታኅሣሥ ፪  ፳፻፲፯ ዓ.ም

በቅድስት ቤተክርስቲያናችን
ሐዋርያዉ ታዴዎስ ፣ ሠለስቱ መዕት ፣ ቅድስት አትናስያ ፣ አቡነ እንድርያኖስ ፣ ቅድስተ ዜና ማርቆስ ፣ አባ ጉባ

አክብረን እና አስበን እንውላለን።

📣📣📣
✔️ የጻድቅ መታሰቢያ ለበረከት ነው። ምሳ ፲፤፯

✔️  መታሰቢያ ለዘለዓለም ይኖራል መዝ.፻፳፮፥፮


✔️ "ቅዱሳን በዓለም ላይ እንዲፈርዱ አታውቁምን? ፩ኛ ቆሮ ፮:፪

የመላዕክት ፣ የቅዱሳን ፣ የሰማዕታት ተራዳይነት እና በረከት ከሁላችንም ጋር ይሁን።

✨#ድምፀ_ተዋህዶ✨


✨አንድ ትእቢተኛና ልብ አውልቅ ተማሪ
መምህሩን ሊሳለቅባቸው አሰበና "የኔታ ገሀነም በየት በኩል ነው ?"

አላቸው።የኔታም የውስጡን አውቀው "ልጄ እመንገዱህ ላይ ነህ ......"አሉት ይባላል

✨#ድምፀ_ተዋህዶ✨


🗓ድጓ ከምን ያድናል❓🧠
አንድ መናፍቅ  ታላቁን የድጓውን መምህር የናቀ መስሎት "የኔታ ድጓ ከምን ያድናል "ሲል ጠየቃቸው እሳቸውም ቀበል አድርገው "እንዲህ ከማለት ያድናል" አሉት ይባላል።
↗️#ድምፀ_ተዋህዶ ↗️


~ኅዳር 21~

እንኳን-ለቅድስት_ጽዮን_ድንግል_ማርያም አመታዊ በአል በሰላም አደረሳችሁ🙏🙏

  ~ኅዳር ሃያ አንድ ቀን ጽዮን ማርያምን የምናከብርባቸውን ምክንያቶች ~።

በዚህች_ቀን:-
✞ ታቦተ ጽዮን (ጽላተ ኪዳን) ለሊቀ ነቢያት ቅዱስ ሙሴ መሰጠቷን እናስባለን።

✞ ታቦተ ጽዮን በምርኮ በሄደችበት በሀገረ ፍልስጤም ዳጎን የተባለ የአህዛብን ጣኦት አድቅቃ በድል የተመለሰችበትን ዕለት በማሰብ።

✞ በዘመነ ልበ አምላክ ቅዱስ ዳዊት በአሚናዳብ ሠረገላ ሁና ከአቢዳራ ቤት ስትመጣ ቅዱሱ ንጉሥ በታላቅ ሐሴት በፊቷ ዘመረ። አገለገለ። ምድራዊ ክብሩን እስኪረሳ ድረስ ለታቦተ አምላክ የተቀኘላት በማሰብ።

✞ ታቦተ ጽዮን ንጉሥ ሰሎሞን ወደ ሠራላት ቤተመቅደስ በክብር የገባችበትን ዕለት በማሰብ፤

✞ የቀደሙ ነብያት ስለእመቤታችን በተለያየ አምሳል ያዩበት ለምሳሌ፦ ነብዩ ዕዝራ በሃገር መንፈሳዊት፣ ሕዝቅኤል በተዘጋች ቤተመቅደስ፣ ዘካርያስ በተቅዋመ ወርቅ ወዘተ ያዩበትን ዕለት በማሰብ፤

✞ ቀዳማዊ ምኒሊክ ከዐሥራ ሁለቱ ነገድ እስራኤል የበኩር ልጅ ጋር ሊቀ ካህናቱን  አዛሪያስንና ታቦተ ጽዮንን ይዞ አክሱም የደረሰበትን ዕለት በማሰብ፤

✞ በዘመነ አፄ ባዜን (በ4 ዓ/ም አካባቢ) አማናዊት ጽዮን ድንግል ማርያም ወደ አክሱም ጽዮን በስደት መጥታ ገብታለች። በዚህ ጊዜም 2ቱ ጽዮኖች ሲገናኙ ታላቅ ብርሃን አክሱምን ውጧታልና ይህንንም በማሰብ፤

✞ በአብርሃ ወአፅብሃ ዘመነ መንግስት ክርስትና የኢትዮጵያ ብሔራዊ ሃይማኖት ሆኖ አዋጅ የታወጀበትን በማሠብ፤

✞ አብርሃ ወአጽብሃ በወርቅና በዕንቁ ያሠሩት ባለ አሥራ ሁለት ክፍል ቤተ መቅደስ ለመጀመሪያ ጊዜ ቅዳሴ ቤቱ የተከበረበት ዕለት በመሆኑ፤

✞ በዘጠነኛው መቶ ክፍለ ዘመን ዮዲት ጉዲት አብያተ ክርስቲያንን ስታቃጥል ታቦተ ጽዮንን ይዘው ወደ ዝዋይ ሀይቅ ከተሰደዱ በኋላ ዘመነ ሰላም ሲጀመር አክሱም በነበሩ ካህናት አስታዋሽነት ከዝዋይ ወደ አክሱም የገባችበት ዕለት በመሆኑ፤

በእነዚህ ምክንያቶች በመላው ኢትዮጵያ በተለይም በርእሰ አድባራት ወገዳማት አክሱም ጽዮን ከፍ ባለ መንፈሳዊ በዓል እናከብራለን።

#ድምፀ_ተዋህዶ


ቅዱሳኑን ያዳነ ቅዱስ መልአክ እኛንም ያድነን ዘንድ እንደ አባቶቻችን "አድኅነኒ ዘአድኃንኮሙ በአክናፊከ ምንትው:: አመ ውስተ እሳት ተወድዩ ሠለስቱ እደው::" እያልን እንለምነው::

     (መልክዐ ገብርኤል)

"በአምላኬም በእግዚአብሔር ፊት ስለ ተቀደሰው ስለ አምላኬ ተራራ ስለምን: ገናም በጸሎት ስናገር አስቀድሜ በራእይ አይቼው የነበረው ሰው ገብርኤል እነሆ እየበረረ መጣ:: በማታም መሥዋዕት ጊዜ ዳሰሰኝ:: አስተማረኝም ." †

       (ዳን. ፱፥፳)

† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †

#አቤቱ የሆነብንን አስብ

#ድምፀ_ተዋህዶ


የቀድሞው ዘማሪ ሐዋዝ ተገኝ ወደ ቀደመው የአባቱ ቤት ወደሆነችው ቅድስት ኦርቶዶክሳዊት መቅደስ ተመልሷል
***

በተ*ዶሶ እንቅስቃሴ ላይ የነበረው የቀድሞ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ዘማሪ የነበረው ሐዋዝ ተገኝ

ቀድሞ ያገለግልባት ወደነበረችው ቅድስት እና ንጽሕት ወደሆነችው ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ መቅደስ በንሰኃ ጥምቀት ተመልሷል።

እግዚአብሔር ይመስገን !!!

#ድምፀ_ተዋህዶ


+++ድንቅ ልዩነት ተመልከቱ+++

በዓለም ለመጀመሪያ ጊዜ ፈርዲናንድ ማጄላን ዓለምን በመርከብ ዞረ።

👉ሐዋርያቱ ደግሞ መርከባቸውን ጥለው ዓለምን ዞሩ!

ዛሬ ይዘንባል እያሉ ትንቢት የሚተነብዩ ሜትሮሎጂስቶች ሞልተዋል።

👉እንደ ኤልያስ ዝናብ እንዳይዘንብ ሰማይን የዘጋ ዳግመኛም ዝናብን ያዘነበ ከቶ የለም።

በላብራቶሪው ተመራምሮ ህሙማንን የፈወሰ ሞልቷል።

👉እንደ ጴጥሮስ ጥላው ድውይ የፈወሰ ከቶ አላየሁም።

በዘፈኑ አጋንንትን የጠራ እንደ ማይክል ጃክሰን ሞልቷል።

👉እንደ ዳዊት በበገና መዝሙሩ አጋንንትን ያስወጣ እስከ ዛሬ አልተገኘም።

ከረቫትና ሱፉን ለብሰን የምንጎራደድ ሞልተናል።

👉የልብሱ ቁጨት አጋንንት ያስወጣ እንደ ጳውሎስ ከቶ አልተገኘም።

የግብጽ ነገሥታት አጽማቸው በክብር ይቀመጣል።

👉ዐጥንቱ ሙት ያስነሳ እንደ ኤልሳዕ ከቶ አላየንም።

በአሜሪካ የነገሥታትን ምሥጢር የሚሰልሉ ድርጅቶች ሞልተዋል።

👉እንደ ኤልሳዕ በእስራኤል ሆኖ በሶሪያ ቤተመንግሥት የሚደረገውን ምሥጢር ያወቀ አልተገኘም።

ለመጀመሪያ ጊዜ ጨረቃን በእግሩ የረገጠ ዩሪ ጋጋሪ ዛሬ ብዙዎቹ አድርገውታል።

👉እንደ ኢያሱ ፀሐይን ያቆመ ከቶ አልተገኘም።

በነገራችን ላይ በተፈጥሮ ሕግ መሰረት ፀሐይ በመሃል ቆማ መሬት ዙሪያውን ትዞራለች። በፀሐይ ፊት ያለው የመሬት ክፍል ቀን ሲሆን ሌላኛው ጎን ደግሞ ማታ ይሆናል።

እነ ኢያሱ በሚዋጉበት ጊዜ መሬት ከፀሐይ ፊቷን አዙራ ቀኑ ሊጨልም ነበር።

👉ኢያሱ ግን መሬት እንዳትዞር አደረጋት! ፀሐይን በገባኦን አቆመ ተባለ! መጽሐፈ ኢያሱ ወልደ ነዌ

ሕዝቡም ጠላቶቻቸውን እስኪበቀሉ ድረስ ፀሐይ ቆመ፥ ጨረቃም ዘገየ። ይህስ በያሻር መጽሐፍ የተጻፈ አይደለምን? ፀሐይም በሰማይ መካከል ዘገየ፥ አንድ ቀንም ሙሉ ያህል ለመግባት አልቸኰለም።

👉 እግዚአብሔር ለእስራኤል ይዋጋ ነበርና ((እግዚአብሔር የሰውን ቃል የሰማበት እንደዚያ ያለ ቀን ከዚያም በፊት ከዚያም በኋላ አልነበረም።))
የዓለም መሪዎች ከአስር በላይ ቋንቋ መናገራቸውን እንጃ፤

👉ሐዋርያቱ ግን 72 ቋንቋ ተገለጠላቸው።

ኃያላን ነገሥታት ድውይ እንኳን መፈወስ አይችሉም።

👉ቅዱሳኑ ግን የ70 የ80 ዘመን ሬሳ አስነሱ።

👉ጠቢባን ነን የሚሉ ጸሐፍት ፈሪሳዊያንን ምላሽ ያሳጣቸው ዘንድ ጥበብ ያልነበራቸውን ዓሳ ወጋሪ የነበሩ ሐዋርያትን መረጠ።

ኃያላን ነገሥታት የመሰሉ መሪ ዳዊትን የመሰሉ ነገሥታትን የወለዱ የከበሩ እናቶች ሞልተዋል።

👉የነገሥታትን ንጉሥ ክርስቶስን የወለደች እናት ግን አንድ ብቻ ናት።

ይህችውም ከሴቶች መካከል ተለይታ የተባረከችው ድንግሊቱ 👉 ማርያም ናት 👈

           
ስብሐት ለእግዚአብሔር!

#ድምፀ_ተዋህዶ

https://t.me/dmtse_tewaedo

23k 5 133 111

➣ አንተኑ ሚካኤል ዘአውረድከ መና ➢

    ሊቁ ቅዱስ ያሬድ

✝ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ✝

🙏 እንኳን ለሊቀ መላእክት ለቅዱስ ሚካኤል ሕዝበ እስራኤል ነጻነት ያወጣበትን ዕለት አደረሰነ 🙏

✤ ኅዳር ፲፪(12) ሚካኤል ወአስተርእዮተ ዮሐንስ መጥምቅ ውስተ ደብረ ማኀው ወፊላታዎስ ሊቀ ጳጳስት ወበእደ ማርያም ንጉሥ ዘኢትዮጵያ ✤

✤ ዘነግህ ምስባክ ✤

እግዚኦ በኃይልከ ይትፌሣሕ ንጉሥ
ወብዙኀ ይትሐሠይ በአድኀኖትከ
ፍትወተ ነፍሱ ወሀብኮ

✤ ትርጉም ✤

አቤቱ በኃይልህ ንጉሥ ደስ ይለዋል
በማዳንህ እጅግ ሐሤትንና ያደርጋል
የልቡን ፈቃድ ሰጠኸው

            መዝ ፳-፩
                 20   1

✤ ወንጌል ✤

ሉቃ ም ፲፱ ቁ ፲፩-፳፰
           19    11  28

✝ የቅዳሴ ምንባባት ✝

ሮሜ ም ፱ ቁ ፲፯-፳፬
ይሁዳ ም ፩ ቁ ፱-፲፬
ግብ.ሐዋ ም ፳ ቁ ፳፰-፴፩

❖ ምስባክ ❖

ይትዐየን መልአከ እግዚአብሔር ዐውዶሙ
ለእለ ይፈርህዎ ወያድኀኖሙ
ጠዐሙ ወታእምሩ ከመ ኄር እግዚአብሔር

🙏 ትርጉም 🙏

የእግዚአብሔር መልአክ በሚፈሩት ሰዎች ዙርያ ይሰፍራል ያድናቸውማል
እግዚአብሔር ቸር እንደሆነ ቅመሱ እዩም

              መዝ ፴፫-፯
                     33   7

❖ ወንጌል ❖

ማቴ ም ፲፰ ቁ ፲፭-፳፩
            18     15  21

❖ ቅዳሴ

ያዕቆብ ዘሥሩግ አው ባስልዮስ

" አቤቱ የሚያረጅ የሚጠፋ ይህ ተስፋ ዓለም ለእኛ ለክርስቲያን ወገኖችህ አይደለም፤የሚመጣውን ተስፋ እናደርጋለን ደጅም እንጠናለን እንጂ "
     ቅዳሴ ያዕቆብ ዘሥሩግ
              ም ፩ ቁ ፹፯
                  1      87

✝ በዓሉ በዓለ ምህረት በዓለ ፀጋ በዓለ በረከት ያድርግልን ቸሩ መድኃኔዓለም በቸርነቱ ይማረን እመ አምላክ እግዝእትነ ማርያም በምልጇዋ ትጠብቅ በዕፀ መስቀሉ ይባረክን ቅድስት ቤተክርስቲያን በረድኤት ይጠብቅልን በየሰዓቱ በየደቂቃው ጠባቂ መላዕክት አያሳጣን ከሊቀ መላዕክቱ ከቅዱስ ሚካኤል በረከት ይክፈልን በቅዱሳኑ ፀሎት ሁላችንም ይማረን ለቅዱሳኑ ሁሉ የተለመነች እመቤታችን ማርያም ለሁላችንም በረከት በምህረት ትለመነን ለሃገራችን ለህዝባችን ስላም ይስጥልን ደም ሰማዕታት ቅዳሴ መላዕክት ዝማሬ ዳዊት የተቀበለ አምላክ ቅዱሳን የኛንም ፆም ፀሎት ምሕላ ምስጋና ይቀበልልን ሁላችንም ለንስሐ ሞት ያብቃን ✝️

#ድምፀ_ተዋህዶ

https://t.me/dmtse_tewaedo


ጾም በእግዚአብሔር ታዟል፤ተፈቅዷልም ።
++++++++++++++++++++++++++
ጌታችን አምላካችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ጾምን እንድንጾም ባርኮ የሰጠን እሱ ነው ።ለዚህም ማረጋገጫ ፦
"ኢየሱስም እንዲህ አላቸው፦ሚዜዎች ሙሽራው ከእነርሱ ጋር ሳለ ሊያዝኑ ይችላሉን? ነገር ግን ሙሽራው ከእነርሱ የሚወሰድበት ወራት ይመጣል፥ በዚያ ጊዜም ይጦማሉ።"
ማቴ 9:15
በዚህ መሰረት ፦
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የራሷ የሆነ የጾም ህግና ስርዓት አላት ።
"ነገር ግን ሁሉ በአግባብና በሥርዓት ይሁን ።"እንዲል
1ኛ ቆሮ 14፥40
በቤተክርስቲያናችን ህግና ሥርዓት ተሰርቶላቸው
ከሚጾሙ 7 የአዋጅ አጽዋማት መካከል አንዱ ጾመ ነብያት ይባላል ።የጾሙ ጊዜ ከህዳር 15-እስከ ጌታ ልደት ታህሳስ 28 ድረስ ያለው ነው ።ይህን ጾም የምንጾመው ነቢያት በየዘመናቸው ስለክርስቶስ መምጣት ንጽህት ከምትሆን ከእመቤታችን ከቅድስት ድንግል ማርያም መወለዱን በናፍቆት ይጾሙና ይጸልዩ ስለነበር የእነርሱን አርአያ ተከትለን የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስን ልደት ከማክበራችን ቀደም ብለን ይህን ጾም እንድንጾም በሐዋርያዊት ቤተክርስቲያን ሥርዓት ተሰርቷል። (ፍት.መ.ን.አንቀጽ 15)
ስለሆነም እኛም ክርስቲያኖች ይህን ተከትለን ብልቶቻችንን ሁሉ(አይን ይጹም ፤እጅ ይጹም፤ እግር ይጹም ፤አንደበት ይጹመ...እንዳለ ቅዱስ ያሬድ) ከኃጢአት ጠብቀን፤እግዚአብሔርን ከማያስደስቱ ማናቸውም ነገሮች ራሳችንን አርቀንና ፤በወንድሞቻችን በማናቸውም ላይ ቂም በቀልን በማስወገድ ይቅርም በመባባል ፤ጸሎትን ስግደትን ምጽዋትንም በመጨመር በንጹህ ልቦና መጾም ይገባናል።ይህን ካደረግን ዘወትር የሚዋጉንና የሚፈታተኑን የአጋንንት ሰራዊት በሙሉ ይደመሰሳሉ፤ኃይላቸውም ይደክማል ።ከእግዚአብሔር ከአምላካችን ፍቅርን ሰላምና በረከትንም እንቀበላለን ።
"የጌታ ቃል የታመነ ነውና።"ቲቶ 3:8
".....ይህ ዓይነት ግን ከጸሎትና ከጦም በቀር አይወጣም አላቸው።"
ማቴ 17:21

#ድምፀ_ተዋህዶ

        📹📹📹📹
   ✨ፊላታዎስ ሚዲያ✨
               👇👇
https://youtu.be/PYhgHxupzLI?si=pQaqogjyj_DUcNXW


ከአባቶች አንደበት
       
      ➕
፩ "ፀሎት የሚያፈቅር ሰው ብታይ
     ምንም ዓይነት በጎ ነገር በውስጡ እንደሌለ ትረዳለህ ፤ ወደ እግዚያአብሔር የሚፀልይ ከሆነ መንፈሳዊነቱን ሞቷል ህይወትም የለውም "
           ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ

፪ "ፀሎት ችላ የሚል ሰው እንዲሁም ለንስሐ የሚያበቃ ሌላ በር አለ ብሎ የሚያስብ በዲያቢሎስ ተሸንግሎአል "
              ማር ይሳቅ

፫ "ፀሎት አእምሮን ወደ እግዚያአብሔር ማቅረብ ነው "
              ማር ይሳቅ

፬ "ፀሎት ፀጋን ይጠብቃል ፤ ቁጣንም ያሸንፋል ትቢትንም የመከላከል ዝንባሌ ያሳድርብናል "
                ከአባቶች

✝️፭ "የመንፈስ ፍሬዎች ያለ ፀሎት ገንዘባችን ልናደርጋቸው አንችልም "
          ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ

፮ "ፀሎት የማያረጅ ትዕግስትን ገንዘብ የምናደርግባት ታላቅ የጦር መሣሪያ ነው"
                ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ

#ድምፀ_ተዋህዶ

        📹📹📹📹
   ✨ፊላታዎስ ሚዲያ✨
               👇👇
https://youtu.be/PYhgHxupzLI?si=pQaqogjyj_DUcNXW

20 ta oxirgi post ko‘rsatilgan.