የትክክለኛ ቤዛ መስፈርቱ ይኸው!
በአጭር ቃል ስብከት፣ "... እኛ ግን የተሰቀለውን ክርስቶስን እንሰብካለን፤" (1ቆሮ. 1፥23) እና "ኃጢአተኞችን ሊያድን ክርስቶስ ኢየሱስ ወደ ዓለም መጣ የሚለው ቃል የታመነና ሁሉ እንዲቀበሉት የተገባ ነው፤" 1ጢሞ. 1፥15) የሚለው ብቻ ነው። ቅዱሳን ሐዋርያትም፣ የስብከታቸው ማዕከል፣ "መዳንም በሌላ በማንም የለም፤ እንድንበት ዘንድ የሚገባን ለሰዎች የተሰጠ ስም ከሰማይ በታች ሌላ የለምና።" (ሐ.ሥ. 4፥12) የሚል ነበር።

ከዚህም ባሻገር በቅዱሳት መጻሕፍት የተጠቀሱት ደቀ መዛሙርት ኹሉ የሰበኩት የተሰቀለውን ክርስቶስን ብቻ ነው።
"ፊልጶስም ወደ ሰማርያ ከተማ ወርዶ ክርስቶስን ሰበከላቸው።" (ሐ.ሥ. 8፥5)
"... ወዲያውም ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ እርሱ የእግዚአብሔር ልጅ እንደ ሆነ በምኵራቦቹ[ጳውሎስ] ሰበከ።" (ሐ.ሥ. 9፥20)
"ማንም ሳይከለክለው[ጳውሎስን] የእግዚአብሔርን መንግሥት እየሰበከ ስለ ጌታ ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ እጅግ ገልጦ ያስተምር ነበር።" (ሐ.ሥ. 20፥28)
አዎን፤ "በስሙም ንስሐና የኃጢአት ስርየት ከኢየሩሳሌም ጀምሮ በአሕዛብ ሁሉ ይሰበካል" (ሉቃ. 24፥47) ተብሎ እንደ ተነገረ፣ ከኢየሱስ በቀር ሌላ ስብከት የለም። ቅዱስ ጴጥሮስም፣ "ለሕዝብም እንድንሰብክና በሕያዋንና በሙታን ሊፈርድ በእግዚአብሔር የተወሰነ እርሱ እንደ ሆነ እንመሰክር ዘንድ አዘዘን።" (ሐ.ሥ. 10፥42) ብሎ እንደ ተናገረው፣ እንድንሰብክ የታዘዝነው፣ ከክርስቶስ በቀር ሌላ የለም።
ምክንያቱም፣ ክርስቶስ የመላለሙ ቤዛ ነውና፣ ሰዎች አምነው ይድኑበት ዘንድ እንሰብከዋለን። ጌታ ኢየሱስን እመኑና ዳኑ እንላለን። ጌታ ኢየሱስን በማመንና በመቀበል የዘላለም ሕይወት አለ ብለን እንሰብካለን። "በልጁ[በክርስቶስ] የሚያምን የዘላለም ሕይወት አለው፤ በልጁ የማያምን ግን የእግዚአብሔር ቍጣ በእርሱ ላይ ይኖራል እንጂ ሕይወትን አያይም።" (ዮሐ. 3፥36)
በርግጥም በቅዱሳት መጻሕፍትም የታዘዘው ይኸው ነው። ለመስበክና ለማወጅ የክርስቶስ ትንሣኤው ኃይላችን ነው። ከክርስቶስ በቀር ሊታወጅ በሞት ላይ የሠለጠነ ሌላ የለም።
ካለ "እልፍ ቤዛ" ወዳዶቹ የትክክለኛና ከኀጢአት የሚቤዠው ቤዛ መስፈርቱ ይህ ነው! መስፈርቱም፦ ማርያምም ኾኑ ሙሴ፣ አምላክ ኾነው ሳለ ክብራቸውን ጥለው በበረት ተወልደው፣ በገሊላና በኢየሩሳሌም አደባባዮች በኪደተ እግራቸው ተመላልሰው፣ ተወቅሰውና ተተችተው፣ ስለ በደላችን ቤዛ ለመኾን አንዳች በደልና ነቀፋ፣ ነውርና ዕድፈት ሳይገኝባቸው መከራን ተቀብለው፣ ተሰቅለው፣ ተቀብረው፣ አብን ፍጹም አርክተው በሦስተኛው ቀን ከሙታን መካከል ከተነሡና ዐርገው፣ በአብ በግርማው ቀኝ መቀመጥ ከቻሉ ምናልባት "ቤዛ ብለን" እንሰብካቸው ይኾናል።
ነገር ግን ከክርስቶስ በቀር ሌላ ቤዛ የለምና ርሱን ብቻ እንሰብከዋለን! እንኪያስ እንደ ደቀመዛሙርቱ እንዲህ እንላለን፣
"ወንድሞች ሆይ፥ በእርሱ በኩል የኃጢአት ስርየት እንዲነገርላችሁ፥ በሙሴም ሕግ ትጸድቁበት ዘንድ ከማይቻላችሁ ሁሉ ያመነ ሁሉ በእርሱ እንዲጸድቅ በእናንተ ዘንድ የታወቀ ይሁን።" (ሐ.ሥ. 13፥38-39)
“ጌታችንን ኢየሱስ ክርስቶስን በማይጠፋ ፍቅር ለሚወድዱ ሁሉ ጸጋ ይሁን።” (ኤፌ. 6:24) አሜን።
Blog link - https://abenezerteklu.blogspot.com/2025/04/blog-post_26.html?m=1