🏃የኢትዮጵያ ቱሪዝም ሚኒስቴር ከታላቁ ሩጫ ጋር በመሆን በሐዋሳ ከተማ ያከናወኑት የ2017 ሶፊማልት ሐዋሳ ሃይቅ ግማሽ ማራቶን እና የ8 ኪሜ ውድድር ተካሂዷል።
በዚህም በወንዶች የግማሽ ማራቶን ውድድር አስቻለው ብሩ 1፡02.26 በመግባት ቀዳሚ ሆኖ ሲያጠናቅቅ መለሰ ኩሜ 1፡02.27 በሆነ ሰዓት ሁለተኛ እንዲሁም አላዛር ተፈራ በ 1፡02.30 በመግባት ሶስተኛ ደረጃን ይዞ ፈጽሟል።
በሴቶችየግማሽ ማራቶን ውድድር ምህረት ገመዳ 1፡13.22 በመግባት ቀዳሚ ሆና ውድድሯን ስትፈጽም ተውባ ደምሴ 1፡13.27 በመግባት ሁለተኛ ደረጃን ይዛለች። ትህቭስት ወርቁ ደግሞ በ1፡13.28 በመግባት በሶስተኛነት ውድድሩን አጠናቃለች።
በዚህ ውድድር አሸናፊ ለሆኑ አትሌቶች እንደየደረጃቸው የገንዘብ የዋንጫ እና የሜዳልያ ሽልማት ተበርክቶላቸዋል።
ለ13ኛ ጊዚ በተካሄደው በዚህ ውድድር ላይ ኢትዮጵያን ጨምሮ ከስድስት አህጉራት የተውጣጡ የ25 ሀገራት ዜጎች ተሳታፊ ነበሩበት።
#EBS
#EBSTVNEWS
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews