በኢነርጂ ፍጆታ እና ልዩ ልዩ አገልግሎቶች ተጨማሪ እሴት ታክስ አተገባበር ላይ የተሰጠ ማብራሪያ
ወርሀዊ የኤሌክትሪክ ፍጆታቸው ከ200 ኪሎ ዋት ሰዓት በላይ በሚጠቀሙ የመኖሪያ ቤት ደንበኞች እንዲሁም በሁሉም የንግድና የኢንዱስትሪ ደንበኞች በተጠቀሙት ፍጆታ ሂሳብ ላይ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተግባራዊ መደረጉ ይታወሳል፡፡
የገንዘብ ሚኒስቴር ከተጨማሪ እሴት ታክስ ነፃ የሚሆነውን መኖሪያ ቤት የኤሌክትሪክ ኃይልና የውኃ የፍጆታ መጠን ለመወሰን ባወጣው አዋጅ ቁጥር 1341/2016 እና አዋጁን ለማስፈፀም በወጣው መመሪያ ቁጥር 1021/2016 መሠረት ክፍያው ከመስከረም ወር ጀምሮ በእነዚህ አገልግሎቶች ላይ ተግባራዊ ተደርጓል፡፡
የተጨማሪ እሴት ታክስ ገንዘብ ስብሰባው ሂደት የድህረ ክፍያ ተጠቃሚ ደንበኞች ከመስከረም ወር ጀምሮ ያለባቸውን የኋላ ክፍያ በታህሳስ ወር በወጣው ቢል ላይ ተጨምሮ እንዲከፍሉ ተደርጓል፡፡
በተመሳሳይ የቅድመ ክፍያ ተጠቃሚ ደንበኞችም ከመስከረም ወር ጀምሮ ባላቸው የፍጆታ መጠን መሠረት የተጨማሪ እሴት ታክስ እንዲከፍሉ የሚጠበቅባችው ሲሆን፤ ተግባራዊ መደረግ የጀመረው ደግሞ በጥር ወር ኢነርጂ ሲገዙ ወይም ካርድ ሲሞሉ ነው፡፡
የቅድመ ክፍያ አገልግሎት ተጠቃሚ ደንበኞች ላይም ይህ የተጨማሪ እሴት ታክስ እንደ ድህረ ክፍያ ደንበኞች በተመሳሳይ ጊዜ ተግባራዊ መደረግ ቢኖርበትም፤ በሲስተም ላይ ለመጫን ጊዜ በመውሰዱ ምክንያት እስከ ታህሳስ ወር ድረስ ሳይጫን ቆይቷል፡፡
ለዚህም ይቅርታ እየጠየቅን፤ አሁን ላይ ከሲስተም ጋራ የተያያዙ ችግሮች ተፈተው ከ200 ኪሎ ዋት ሰዓት በላይ በየወሩ በሚጠቀሙ የመኖሪያ ቤት እና በሁሉም የንግድ የቅድመ ክፍያ አገልግሎት ተጠቃሚ ደንበኞች ላይ በታህሳስና ጥር ወር መከፈል የሚገባቸው ተጨማሪ እሴት ታክስ በየካቲት ወር ኢነርጂ ሲገዙ ( ካርድ ሲሞሉ) እንዲከፍሉ እየተደረገ ይገኛል፡፡
በቀጣይም የቅድመ ክፍያ አገልግሎት ተጠቃሚ ደንበኞች በኤሌክትሪክ ፍጆታ ሂሳባችው ላይ ያልተከፈለ የመስከረም፣ የጥቅምትና የህዳር ወር ተጨማሪ እሴት ታክስ በመኖሩ፤ በቀጣይ ካርድ ሲሞሉ ውዝፉ እየተጫነ የማቀናነስ ሥራ እንደሚሰራ እየገለፅን፤ ክቡራን ደንበኞቻችን ይህንን እንድትገነዘቡና ከዚህ ስሌት ውጪ ተጨማሪ ክፍያ የማይፈፀም መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
ከመስከረም 1 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ ተግባራዊ እንዲደረግ የተወሰነው የተጨማሪ እሴት ታክስ፤ ተቋማችን ከላይ በተገለፀው አግባብ ሰብስቦ በየወሩ ለገቢዎች ሚኒስቴር ገቢ ያደርጋል፡፡
በተመሳሳይ የተጨማሪ እሴት ታክስ ከወርሃዊ የፍጆታ ሂሳብ በተጨማሪ ደንበኞች ለተቋማችን በሚከፍሉት የአገልግሎትና ሌሎች ልዩ ልዩ ክፍያዎች ላይም በአዋጁ መሠረት ተግባራዊ እየተደረገ ይገኛል፡፡
በሌላ በኩል የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን (ኢቲቪ) በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አዋጅ ቁጥር 1278/2015 ዓ.ም በተሰጠው ስልጣን መሰረት ዓመታዊ የቴሌቪዥን አገልግሎት ክፍያ የሚሰበስብ መሆኑ የሚታወቅ ሲሆን፤ በዚሁ መሠረት ተቋማችን የቴሌቭዥን አገልግሎት ክፍያ ወርኃዊ የኤሌክትሪክ የፍጆታ መጠናቸው ከ50 ኪሎ ዋት ስዓት በላይ የሆኑ ደንበኞች 10 ብር ከወርሃዊ ኤሌክትሪክ ፍጆታ ሂሳብ ላይ በመጨመር እየሰበሰበ ለኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን (ኢቲቪ) ገንዘቡን ገቢ ያደርጋል፡፡
እንዲሁም በወርሃዊ የፍጆታ ሂሳብ መሠረት ከሁሉም ደንበኞች ለተቆጣጣሪ ባለስልጣን ማለትም ለነዳጅና ኢነርጂ ባለስልጣን 0.5 በመቶ (Regulatory Fee) በመሰብሰብ በየወሩ ለባለስልጣኑ ገቢ ያደርጋል፡፡
ስለሆነም ውድ ደንበኞቻችን ከዚህ ቀደም ባሳወቅነው መሰረት ከወርሃዊ የፍጆታ ሂሳብ ጋር የተጨማሪ እሴት ታክስና ሌሎች ተያያዥ ክፍያዎች ተግባራዊ እየተደረገ የሚገኘው በዚህ መልኩ መሆኑን እንድትረዱ በአክብሮት እናስገነዝባለን፡፡
#የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት