በቂ የትራንስፎርመር አቅርቦት ያለ በመሆኑ አዲስ ኃይል ጠያቂ ደንበኞች ከተቋሙ መውሰድ ይችላሉ
በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት በቂ የትራንስፎርመር አቅርቦት ያለ በመሆኑ ደንበኞች ከተቋሙ በመውሰድ አገልግሎቱን ማግኘት እንደሚችሉ የተቋሙ ኢንጂነሪንግ ዳይሬክተር አቶ ተፈራ ደርቤ ገለፁ፡፡
ኃይል ለማቅረብ የሚያስፈልገው የትራንስፎርመር ግብዓት በተቋሙ ውስጥ የሚገኝ ከሆነ ደንበኞች ማቅረብ እንደማይጠበቅባቸው የጠቀሱት ዳይሬክተሩ በአንፃሩ የሚፈለገው ግብዓት በተቋሙ አለመኖሩ ሲረጋገጥ ደንበኞች እንዲያቀርቡ እየተደረገ አገልግሎቱን እንዲያገኙ ሲደረግ እንደነበር ጠቅሰዋል፡፡
በተለይ ከአሁን በፊት የትራንስፎርመር አቅርቦት ችግር ስለነበር ደንበኞች በራሳቸው ትራንስፎርመር እንዲያቀርቡ ፍቃድ ተሰጥቷቸው በተቋሙ ፍተሻ ከተደረገ በኋላ የጠየቁት ኃይል ባቀረቡት ትራንስፎርመር እንዲገናኝላቸው ይደረግ እንደነበር አስረድተዋል፡፡
ይህ አሠራር ደንበኞች እንዲጉላሉ እና ላላስፈላጊ ወጪ እንዲዳረጉ ከማድረጉም ባሻገር አንዳንድ የትራንስፎርምር አምራቾች የጥራት ችግር ሲገኝባቸው በግል ጥራት የሌለው ትራንስፎርመር ለደንበኞች በመሸጥ ዙሮ ወደ ተቋሙ መሰረተ ልማት እንዲገባ በማድረግ ለሃይል መቆራረጥ መንስኤ እየሆነ በመምጣቱ ለጊዜው ደንበኞች ከአምራቾች መግዛት እንዲያቆሙ መደረጉን ዳይሬክተሩ ጠቁመዋል፡፡
በአሁኑ ወቅት ተቋሙ በአገር ውስጥ ካሉና በስታንዳርዱ መሠረት ማምረት ከሚችሉ አምራቾች ጋር ውል በመያዝ ትራንስፎርመሮችን እየተረከበ እንደሆነ ተናግረው በሌላ በኩል አምርቼ ተቋሙ ሳይገዛኝ ቀረ ወይም ለመግዛት ፍቃደኛ አይደለም የሚል አምራች ካለ ጥያቄውን በግልፅ ማቅረብ ይቻላል ብለዋል፡፡
ተቋሙ ከአብዛኞቹ የሃገር ውስጥ የትራንስፎርምር አምራቾች ጋር በቅርበት እየሠራንና እያበረታታ መሆኑን የጠቆሙት ዳይሬክተሩ ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው አምራቾች ድጋፍ ለማድረግ ዝግጁ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
በመጨረሻም ዳይሬክተሩ ለአገልግሎት አሰጣጡ አስፈላጊ የሆኑ ግብዓቶችን ከሃገር ውስጥም ሆነ ከውጪ ሃገር አምራቾች እንደሚገዛና በሃገር ውስጥ የማይመረቱ ትራንስፎርመሮችን ከውጪ የሚያስገባ መሆኑን ገልፀዋል፡፡
በዚህ አጋጣሚ ተቋሙ የሃገር ውስጥ አምራቾችን ላለማበረታታ ከሃገር ውስጥ የትራንስፎርምር አምራቾች ግዥ አልፈፅምም እንዳለ ተደርጎ በተለያዩ ማህበራዊ ሚዲያ ተቋማት የቀረበው መረጃ ስህተት መሆኑን ለመግለፅ እንወዳለን፡፡
#የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት