ከ356 ሺሕ በላይ አዳዲስ ደንበኞች የኤሌክትሪክ ተጠቃሚ ሆኑ
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት በተጠናቀቀው ዘጠኝ ወራት ውስጥ 356 ሺሕ 935 አዳዲስ ደንበኞችን የኤሌክትሪክ ኃይል ተጠቃሚ ማድረግ ችሏል፡፡
ሰሜን አዲስ አበባ 4 ሺሕ 440፣ ባሌ ሮቤ 9 ሺሕ 219 እና ሆሳዕና 14 ሺሕ 83 ደንበኞች አዳዲስ ደንበኞችን የኤሌክትሪክ ተጠቃሚ በማድርግ ከእቅዳቸው በላይ ያሳኩ ናቸው፡፡
ባለፉት ዘጠኝ ወራት የኤሌክትሪክ ተጠቃሚ የሆኑ አዳዲስ ደንበኞች ቁጥር ከአምናው ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር 20 በመቶ በብልጫ አሳይቷል፡፡
በተመሳሳይ በተጠናቀቀው በጀት አመት ዘጠኝ ወራት 107 አዳዲስ የገጠር ከተሞች የኤሌክትሪክ ተጠቃሚ ማድረግ የተቻለ ሲሆን 102 ከዋናው የኃይል ቋት 5 ደግሞ ከፀሐይ ኃይል ማመንጫ ያገኙ ናቸው፡፡
ባለፉት ዘጠኝ ወራት የ15 ሺሕ 295 ኪ.ሜ የማሳራጫ መስመር ማስፋፊያ እና 3 ሺሕ 42 አዲስ ትራንስፎርመር ተከላ ስራ ተከናውኗል፡፡
የብልሹ አሰራርና የሙስና ጥቆማ መቀበያ መተግበሪያ በሥራ ላይ መዋሉ፣ የዲጂታል ክፍያ ተጠናክሮ መቀጠሉ፣ በኮሪደር ልማት ላይ የተከናወነ የመልሶ ግንባታ ስራዎች በጠንካራ ጎን የተነሱ ሲሆን የመሰረተ-ልማት ሥርቆት፣ የፕሮጅክት አፈፃፀም መዘግየት እና የሲስተም መቆራረጥ በውስንነት የታዩ ናቸው፡፡
የተቋሙ አጠቃላይ ደንበኞች ቁጥር ወደ 5 ሚለየን 81 ሺሕ 405 የደረሰ ሲሆን ከነዚህ ውስጥ 81 በመቶ የድህረ ክፍያ፣18 በመቶ የቅድመ ክፍያ 1 በመቶ የሚጠጉት የዘመናዊ ቆጣሪ ደንበኞች ናቸው ተብሏል፡፡
የተቋሙ ከፍተኛ ማኔጅመንት አባላት የአገልግሎቱን የ9 ወር ዕቅድ አፈጻፀም እየገመገመ ይገኛል፡፡
#የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት