የውጭ ኢንቨስተሮች ወደ ሀገር ሲመጡ ለጉብኝት የሚወሰዱት ወደ ኢንደስትሪ ፓርኮች፣ አየር መንገድ፣ ሀይል ማመንጫዎች እና የመሳሰሉ ፕሮጀክቶች ጋር ነበር።
አሁን አሁን ደግሞ ጉብኝቱ ወደ ጫካ ፕሮጀክት እና አድዋ ሙዚየም ሆኗል፣ ለምሳሌ በቅርቡ ወደ ኢትዮጵያ የመጡት የሳውዲ ኢንቨስተሮች እነዚህን እንዲጎበኙ ተደርገው ነበር።
ይህ በራሱ ኢንቨስተሮችን ግር የሚያሰኝ ሊሆን ይችላል የሚል አስተያየት የሚሰጡ አሉ፣ ምክንያቱም አንድ ኢንቨስተር የሙዚየም፣ የመዝናኛ እና የቤተ መንግስት ግንባታ አይቶ የአንድ መንግስትን ለኢንቨስትመንት የሰጠውን ትኩረት ሊያይ ስለማይችል።
ሁለተኛው ጉዳይ ደግሞ፣ የጫካ ፕሮጀክትን የትኛው የኮንስትራክሽን ኩባንያ በስንት ብር/ዶላር የፕሮጀክት ወጪ (አንድ ትሪሊየን ብር የሚሉ ግምቶች አሉ)፣ መቼ በተካሄደ ጨረታ እና ከየት በተገኘ ገንዘብ እየገነባው እንዳለ አይታወቅም።
ይህ እንዳለ ሆኖ፣ በርካታ የውጭ ዜጎች እና አንዳንድ የመንግስት ሰራተኞች የጫካ ፕሮጀክትን በተደጋጋሚ እንዲጎበኙት ከተደረገ የኢትዮጵያ ህዝብ በቴሌቭዥን መስኮት እንዲያው ለምን አልተፈለገም የሚሉ ድምፆችም አሉ? ባለኝ መረጃ ለጉብኝት የሚሄዱ ሰዎች ፕሮጀክቱን የሚያሳዩ ፎቶዎች አንስተው እንዳያጋሩ ክልከላ ተጥሏል።
@EliasMeseret