"በዓላት ከመንፈሳዊ ለዛ እያፈነገጡ ተራ ሰርግ እየመሰሉ ነው ፤ ለዚህም ተጠያቂዎቹ እኛው ካህናቱ ነን" ሲሉ ብፁዕ አቡነ ኤርምያስ ተናገሩ።
ጥር 16 ቀን 2017 ዓ.ም (ተ.ሚ.ማ /አዲስ አበባ
በብፁዕ አቡነ ኤርምያስ መሪነት የሰሜን ወሎ መንበረ ጵጵስና ሀገረ ስብከት ቤተክህነትና የወልድያ ከተማ አስተዳደር ቤተክህነት የሥራ ኀላፊዎች፣ የአድባራት አስተዳዳሪዎችና የሰበካ ጉባኤያት ምክትል ሊቃነመናብርት በተገኙበት የከተራ፣ የጥምቀትና የቃና ዘገሊላ በዓላት አከባበር ትናንት ጥር 15 ቀን 2017 ዓ.ም ተገምግሟል።
በውይይት መድረኩ ዓቢይ ኮሚቴው ኀላፊነት ከተሰጠው ጊዜ ጀምሮ የከተራ፣ የጥምቀትና የቃና ዘገሊላ በዓላትን በድምቀት ለማክበር ያከናወናቸውን ተግባራት ሪፖርት አቅርቧል።
“ጥምቀትን በወልድያ” ሥርዓትና ትውፊቱን ጠብቆ በድምቀት ለማክበር በተደረገው እንቅስቃሴ በዓላቱን ከእስከ አሁኑ በተሻለ ማክበር መቻሉንና የሰበካ ጉባኤያት፣ የሊቃውንተ ቤተክርስቲያን፣ የሰንበት ትምህርት ቤቶች፣ የምእመናንና የወጣቶች ተሳትፎና ትብብር በጥንካሬ ተነሥቷል።
የዘንድሮው የበዓል አከባበር ካለፉት ዓመታት የተሻለ ቢሆንም ከተፈለገው መንፈሳዊ ግብ ለመድረስ መስተካከል ያለባቸው ክፍተቶችንና የገጠሙትን ተግዳሮቶች ዓቢይ ኮሚቴው በሪፖርቱ አመላክቷል።
ብፁዕ አቡነ ኤርምያስ የሰሜን ወሎ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ባስተላለፉት ቃለ ምእዳን ኹሉም በተሰጠው ጸጋ
የድርሻውንና መንፈሳዊ ኀላፊነቱን በመወጣቱ በዓላቱን በሰላምና በጥሩ ሁኔታ አክብረናል ብለዋል።
ብፁዕነታቸው ለውይይቱ ተሳታፊዎች በተለይም በካህናት ኀላፊነቶች ዙሪያ ባደረጉት አጭር ገለጻ በዓላት በቤተመቅደስም ይሁን በዐደባባይ ሲከበሩ በዘልማድ ሳይሆን በጥንቃቄ እንዲሆን የካህናት ድርሻ ከፍተኛ ነው ብለዋል።
በበዓላቱ ላይ የኦርቶዶክሳውያን ሥርዓትና ትውፊት ያልሆኑ ከመንፈሳዊ ለዛ ያፈነገጡ እንቅስቃሴዎች መስፋፋትና የአባቶችን መመሪያ አለመቀበል እየተለመደ መምጣቱ የግንዛቤ ክፍተት መሆኑን የገለጹት ብፁዕነታቸው በዓላት የሚከበሩበትን ዓላማ በማስተማርና በማስገንዘብ ኀላፊነታችንን አለመወጣታችን ያስከተለው ችግር ነው ብለዋል።
ሕዝቡ በዓላትን ሲያከብር ከሥጋዊ ስሜት ወጥቶ እግዚአብሔርን የሚያነግሥበት እንዲሆን ዓላማውን ለማሳካትና ችግሮችን ለመቀነስ የቅድመ ዝግጅት ሥራዎችን የሚሠራ ከሀገረ ስብከት፣ ከወልድያ ከተማ አስተዳደር ቤተክህነትና ከአድባራት የተውጣጣ ባለሙያዎችን ያካተተ የጋራ ዓቢይ ኮሚቴ በቅርብ ቀናት ይቋቋማል ተብሏል።
©የሰሜን ወሎ ሀገረ ስብከት