#ዳግማዊ ምኒልክ ጦርነቱ ነገር እርግጥ ሲሆን የእግዚአብሔር ርዳታ እንዳይለያቸው ሽተው ብዙ ተጉዘዋል፡፡ ወደእየ ገዳማቱ እና አድባራቱ ጧፍ፣ ዕጣን እና መገበሪያ አስይዘው ጸሎተ ዕጣን እንዲደረስ ላኩ፤ በጸሎት አስቡኝ አሉ፤ በኪደተ እግር ወደ አራዳው ጊዮርጊስ ጎራ ብለው ተሳሉ፡፡
“ጦርነቱን ካሸነፍኩ በልዩ ሁኔታ
ቤትህን አሳንጻለሁ” ብለው፡፡ ዕለቱን ካህናቱ ጸሎት፣ ንጉሡም የጦርነት ዝግጅቱን ጀመሩ፡፡
ምታ ነጋሪት ክተት ሠራዊት ተባለ፡፡
በዚህም ካህናት ተነሡ “ሃገር ሲኖር፣ ንጉሥ ሲኖር፣ ሕዝብ ሲኖር አይደል እንዴ ቤተ ክርስቲያን የምትኖረው” አሉ፡፡ ምህላው እና ሱባኤው በየአድባራቱ እና ገዳማቱ ተጀመረ፡፡
ከመሃከላቸው አባቶችን መረጡ፡፡ ከአዲስ አበባ ዐድዋ ድረስ ታቦተ ሕጉን አክብረው ይዘው ከሄዱት መካከል ለያውም በባዶ እግራቸው የሄዱ ናቸው ተብሎ ተጽፎላቸዋል የግቢ ገብርኤሉ ካህን መምሬ ካሣሁን፡፡ ታቦተ ጊዮርጊስን ያዙ፤ ሊቃውንት ከበሮ፣ ጸናጽል፤
ካህናት መስቀል፣ ዕጣን፣ ወንጌል ያዙ፡፡ ዘመቻ ተጀመረ ወደ አድዋ፡፡
ሙሉ ቀን ጉዞ ሆኖ ዕረፍት ሲሆን ድንኳን ይተከላል፡፡ ታቦቱ በድንኳን፣ ሕዝቡ በውጪ ይሆንና የሠርክ ጸሎት፣ ምህላ ይደረጋል፡፡ ታቦት ካለ ዝማሬ፣ ጸሎት አለ፡፡ ለያውም ወደ ጦርነት ወደ ሞት እየተሄደ፡፡ ሌሊት መነሣት፣ ጸሎት ማድረግ፣ ምኅላ ማድረስ የካህናቱ፣ የንጉሡ እና የዘማቹ መደበኛ ሥራ ሆነ፡፡
የማያልቅ የሚመስለው መንገድ አለቀ፡፡ የማይደረስ የሚመስለው ተደረሰበት፡፡ ትግራይ ገቡ፡፡ ቀድመው ተዘጋጅተው በምህላ እና በጸሎት የሰነበቱት የትግራይ ካህናት እና ሊቃውንት ሕዝቡን ጨምሮ ተቀበሏቸው፡፡ የጋራ ሱባኤ ታዘዘ፣ ምህላ ታወጀ፡፡ አጤው እና
እቴጌይቱ እንዳ አባ ገሪማ ሱባኤ ያዙ፡፡ መኳንቱ እና መሣፍንቱ ተራውን ወታደር ጨምሮ ሱባኤ ገባ፡፡
ሌት ጸሎት፤ ጧት ማታ ምኅላ፤ ቀን ቅዳሴ ፡፡ ጦርነት ካለ ሞት አለ፡፡ ሞት ካለ ደግሞ ፍትሐት አለ፡፡ ስለዚህ ወዶ ዘማቹ በጦርነት መሐል ቢሞት እንኳ ለሃገሩ፣ ለሃይማኖቱ፣ ለሚስቱ፣ ለልጁ እንደሆነ እና በሃይማኖቱ የሚደረጉ ሥርዓቶች እንደማይቀሩበት የኅሊና
ዕረፍት ይሰማውም ዘንድ የሰባት ቀን ምኅላ እና የቁም ፍትሐት ታወጀ፡፡
“እግዚአ ሕያዋን፡ ሕይወተ ሙታን፡ ተሥፋ ቅቡጻን፡ ረዳኤ ምንዱባን፡ ወመንጽኄ ኃጥአን…፡፡ የሕያዋን ጌታ፣ የሙታን ሕይወት፣ ተስፋ ለቆረጡት አለኝታ፣ የተቸገሩትን የሚረዳ፣ ኃጥአንን የሚያነጻ…"
የካቲት 22 ምሽት የመጨረሻው ምህላ የተደረሰበት፡፡ እንደ ወትሮው ምህላው ተደረሰ፡፡
ውስጣቸው ጠርጥሮ ነበርና በበነጋው የካቲት 23 ቅዳሴው ከወትሮው ቀደም ብሎ በሌሊት
እንዲገባ እና ከሌሊቱ 10 ሰአት እንዲያልቅ መከሩ፡፡ ከንጉሡ ጀምሮ በየ ራሱ፣ በየ ደጃዝማቹ፣ በየ ጎበዝ ዐለቃው ድንኳን እና ማደሪያ ምክር እና የጦር ወሬ፣ የጀግንነት ተረክ ሲነገር አመሸ፡፡ ጦርነቱ ሲጀመር የነበረውነረ ኹነት ብላቴን ጌታ
ኅሩይ በኢትዮጵያ ታሪክ መጽሐፋቸው “ሊቀ ጳጳሱ አቡነ ማቴዎስም ከየደብሩ አለቆች እና
ከድንባሮ ማርያም ካህናት ጋር ባንድ ስፍራ ቆመው ወደጦርነቱ የሚገባውን ወታደር እግዚአብሔር ይፍታህ እያሉ ይናዝዙ ነበር፡፡" ሲሉ ገልጸውታል።
ከድሉ በኋላ አፄ ምኒልክ አራዳ የሚገኘውን ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን በቃላቸው መሠረት
አንፀዋል። ጅማሮውን ያስጨረሱት ንግሥት ዘውዲቱ ናቸው።
ኢትዮጵያውያን አድዋን ባነሱ ቁጥር ስሙን ደጋግመው ያነሱታል፡፡ ስለ አድዋ ስዕል
ቢስሉም መሐል ላይ በነጭ ፈረስ ሆኖ ጦርነቱ መሐል አድርገው ይስሉታል፡፡ በዕለተ ቀኑ
ድል ጠላትን ድል ስላደረጉ፡፡
#የጥቁር_ህዝብ_ኩራት
#ዓድዋ_129
#የኢትዮጵያውያን_ድል
“የምኒልክ ተስፋው እግዚአብሔር ነው "
#መልካም ቀን
#ባለ ማዕተቦችን ወደዚህ
ግሩፕ ይጋብዙ
ለመቀላቀል 👉
https://t.me/enabib