“ከታገቱ ተማሪዎችም መካከል የተወሰኑት የተጠየቀዉን ክፍያ ከፍለው ተለቀዋል” - ኢሰመጉ
የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ጉባዔ (ኢሰመጉ) ከአማራ ክልል ወደ አዲስ አበባ ሲጓዙ በታጣቂዎች ከታገቱ የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች መካከል “የተወሰኑት ተማሪዎች የተጠየቀዉን ክፍያ መክፈል በመቻላቸው መለቀቃቸውን” አስታወቀ።
ከታገቱ ተማሪዎችም መካከል የተወሰኑት “በተለያዩ ምክንያቶች” ከአጋቾች ማስለቀቅ መቻሉን ካሰባሰባቸው መረጃዎች መረዳቱን አመላክቷል፤ ምክንያቶቹን አላብራራም።
ብዛት ያላቸው ተማሪዎች አሁንም በአጋቾች ታግተው እንደሚገኙ ይህም ታጋቾችን ለከፍተኛ እንግልትና ስቃይ መዳረጉን ኢሰመጉ ካሰባሰባቸው መረጃዎች ለማወቅ መቻሉን ጠቁሟል።
የታገቱ ተማሪዎች ተለቀዋል በሚል የሚናፈሰውን መረጃ በተመለከተ ኢሰመጉ በመግለጫው “ታጋቾች በተያዙበት ወቅት አጋቾቹ ተማሪዎችን በቡድን በቡድን በማድረግ ወደ ተለያየ አቅጣጫ ይዘዋቸው መንቀሳቀሳቸውን” ጠቁሞ የተለቀቁ ተማሪዎች እየሰጡ ያለው መረጃም “እነሱ በነበሩበት ቡድን ውስጥ ስላለው ሁኔታ ብቻ ነው” ሲል ጠቁሟል።
ከታገቱት አጠቃላይ ተማሪዎች ውስጥ ምን ያህል እደተለቀቁ የሚያሳይ አለመሆኑን አስታውቋል።
በተጨማሪም የፌደራል እና የሚመለከታቸው የክልል መንግስታት የግዛት ወሰናቸው ባሉባቸው አካባቢዎች የሚፈጸሙ የእገታና አፍኖ የመሰወር ድርጊቶችን እንዲያስቆሙ፣ የእገታና አፍኖ የመሰወር ድርጊት የሚፈጽሙ ሰዎችን በሕግ ተጠያቂ እንዲያደርጉ እና ለዜጎች ተገቢውን ጥበቃ እንዲያደርጉ ኢሰመጉ ጥሪ አቅርቧል።
T.me/ethio_mereja
ኢትዮ-መረጃ