የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በጎፋ ዞን ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖች የ5 ሚሊዮን ብር ድጋፍ አደረገ
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በጎፋ ዞን ገዜ ጎፋ ወረዳ ኬንቾ ሻቻ ጎዝዲ ቀበሌ በደረሰው የመሬት ናዳ ሳቢያ ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖች የ5 ሚሊዮን ብር ድጋፍ አድርጓል፡፡
ባንኩ ዛሬ ያደረገው የገንዘብ ድጋፍ የባንኩ የሥራ ኃላፊዎች እና ሠራተኞች በግላቸው እያደረጉ ካለው ድጋፍ በተጨማሪ መሆኑን አስታውቋል፡፡
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በሀገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች በተፈጥሮም ሆነ በሰው ሠራሽ አደጋዎች ለተጎዱ ወገኖች ፈጥኖ በመድረስ ማኅበራዊ ኃላፊነቱን እየተወጣ እንደሚገኝም ገልጿል፡፡በጤናው ዘርፍ፣ በትምህርት፣ በአካባቢ ጥበቃ፣ በአረንጓዴ ልማት፣ በሰብዓዊ ሥራ ድጋፍ እና በሌሎችም ዘርፎች ማኅበራዊ ኃላፊነቱን ለመወጣት ባለፉት አምስት ዓመታት ከ3 ነጥብ 4 ቢሊዮን ብር በላይ ድጋፍ እንዳደረገም ከባንኩ ያገኘነው መረጃ አመላክቷል።
T.me/ethio_mereja
ኢትዮ-መረጃ