የትምህርት ሚኒስቴር የሚያከናውናቸውን አዳዲስ የለውጥ ስራዎች የሚደግፍ የመግባቢያ ስምምነት ተፈረመ፡፡
--------------------------------------
(ጥር 20/2017 ዓ.ም) በትምህርት ሚኒስቴር እና በኢንፎ ማይንድ ሶሊሽን መካከል የተፈረመው የመግባቢያ ስምምነት ሰነድ በትምህርት ሚኒስቴር እየተተገበሩ ያሉ አዳዲስ የለውጥ ስራዎችን በመደገፍ ተቋማትና ተማሪዎች በየጊዜው አቅማቸውን እንዲገነቡ የሚያደርግ መሆኑ ተገልጿል።
የኢፊዲሪ ትምህርት ሚኒስቴር የከፍተኛ ትምህርት ልማት ዘርፍ ሚንስትር ዴኤታ ክቡር አቶ ኮራ ጡሽኔ በፊሪማ ስነስርዓቱ ላይ እንደገለጹት ስምምነቱ በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ውስጥ ማዕከላትን በማቋቋም እንዲሁም የተለያዩ የአቅም ግንባታ ስራዎች ላይ በመሳተፍ ተማሪዎች የተሻለ አቅም እንዲፈጥሩ የሚያግዝ በመሆኑ ለተግባራዊነቱ ቁርጠኛ መሆን ይገባል ብለዋል።
ስምምነቱ ተማሪዎች በህይወት ጉዞአቸው ወዴትና እንዴት መሄድ እንዳለባቸው የሚያመላክት ስራዎችን ከማከናወን ባለፈ ትምህርታቸውን ጨርሰው ወደ ስራው አለም በሚቀላቀሉበት ወቅት የሚያጋጥሟቸውን ችግሮች ከወዲሁ ለመቅረፍ የሚያስችል መሆኑን ሚንስትር ዴኤታው አያይዘው ገልጸዋል፡፡
የኢንፎ ማይንድ ሶሊሽን ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ የሱፍ ረጃ በበኩላቸው በሰጡት ማብራሪያ የስምምነቱ መፈረም የተማሪዎችን አቅም ከመገንባት ባለፈ ሚኒስቴር መስያ ቤቱ በቀጣይ ለሚያከናወናቸው የጥናትና ምርምር ስራዎች መረጃዎችንም ጭምር ለማግኘት የሚያስችል ነው ብለዋል ፡፡