በማዕከላዊ ቀጠና የተደለደለው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትምህርት ቤቶች ስፖርታዊ ውድድር በመካሄድ ላይ ነው፤
-----------------------------
በተለያዩ ቀጠናዎች ተከፋፍሎ እየተካሄደ የሚገኘው የትምህርት ቤቶች ስፖርት ሊግ በማዕከላዊ ቀጠና የተደለደለው የአዲስ አበባ አስተዳደር ት/ቤቶች ስፖርት ውድድርም መካሄዱን ቀጥሏል።
በአንደኛ፣ መካከለኛና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች በሚካሄደው በዚህ ውድድር የእግር ኳስ፣ የቮሊቦል፣ የአትሌቲክስ፣የጠረዼዛ ቴኒስ፣ የባህል ስፖርት እና የቼስ ስፖርቶች አይነቶች ተካተዋል።
የእጅ ኳስ፣ የውሃ ዋና፣ የፓራ ኦሎምፒክ፣ የቅርጫት ኳስ ስፖርት አይነቶች ደግሞ በሁለተኛ ደረጃ ት/ቤቶች ብቻ እየተከናወኑ መሆኑ የት/ቢሮው መረጃ ያስረዳል።
በቀጣይም መጋቢት 05 /2017 ዓ.ም በዲስትርክት ደረጃ ውድድሩን ለማካሄድ መርሃ- ግብር የተዘጋጀ ሲሆን ከዚህ ጎን ለጎን የመምህራን ስፖርታዊ ውድድሮች በእግር ኳስ ፣ በቮሊቦል፣ በጠረዼዛ ቴኒስ፣ በቼስ እና በባህል ስፖርት (ገመድ ጉተታ) በመካሄድ ላይ መሆናቸው ተጠቅሷል።
ትምህርት ሚኒስቴር ስፖርትን በሁሉም የሀገራችን ትምህርት ቤቶች ተደራሽ፣ አካታችና አሳታፊ በሆነ መልኩ መተግበር እንዲቻል አዲስ የውድድር ስርዓት መዘርጋቱ ይታወሳል።