የትምህርት ሚኒስቴር ሰራተኞችና አመራሮች 129ኛውን የአድዋ ድል በዓል አከበሩ፡፡
-------------------------------------
የካቲት 21/2017 ዓ.ም) «ዓድዋ የጥቁር ሕዝቦች ድል! » በሚል መሪ ቃል ዘንድሮ ለ129ኛ ጊዜ የሚከበረውን የአድዋ ድል በዓል የትምህርት ሚኒስቴር ሰራተኞችና አመራሮች በፓናል ውይይት አክብረዋል፡፡
የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ በመርሃ- ግብሩ ላይ በመገኘት ባስተላለፉት መልዕክት የአድዋ ድል የመላው ጥቁር ህዝቦች ድልና የነጻነት አርማ በመሆኑ የድሉን እሴቶችና ቱሩፋቶች ለይቻላል መንፈሰ ማጎለበቻነት በመጠቀም በያዝናቸው የሥራ ዘርፎች ላይ የሚጠበቅብንን ስኬት ማስመዘግብ እንደሚገባ ተናገግረዋል፡፡
ፕሮፌሰር ብርሃኑ ጨምረውም የአድዋን ድል ከማክበርና ቱሩፋቶቹንም ከመጠቀም በተጨማሪ እኛ መሥራት ያለብንን የቤት ሥራ በወቅቱ በማከናወን የሀገራችን ልማት ማፋጠን ይኖርብናል ብለዋል።
በትምህርት ሚኒስቴር በአጠቃላይ ትምህርት ልማት ዘርፍ የማህበራዊ ሳይንስ ስርዓተ ትምህርት ዴስክ ሃላፊ አቶ ኡመር ኢማም የውይይት መነሻ ያቀረቡ ሲሆን የህዝቦች አብሮ የመኖርና የመልማት እንዲሁም የሀገርን ሉዓላዊነትን የማስከበር ጉዳዮች ላይ ይህ ትውልድ ከቅድመ አያቶቹ ብዙ መማር እንደሚገባው አንስተዋል፡፡
አቶ ኡመር አክለውም የአድዋ ድል ቅድመ አያቶቻችን ብሄራቸው፣ ቋንቋቸው፣ ሀይማኖታቸው፣ባህላቸውና ሌሎች ልዩነቶቻቸው ሳይገድባቸው የሀገርን ሉዓላዊነትና አንድነት ያስከበሩ መሆኑን አብራርተው አሁን ያለው ትውልድ ከዚህ መማር እንደሚገባው ገለጸዋል።
======////======