ኢትዮ ጥቅሳ ጥቅስ


Kanal geosi va tili: Efiopiya, Amharcha


#𝑞𝑢𝑜𝑡𝑒
#𝑚𝑜𝑡𝑖𝑣𝑎𝑡𝑖𝑜𝑛
#𝑖𝑛𝑠𝑝𝑖𝑟𝑎𝑡𝑖𝑜𝑛

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Kanal geosi va tili
Efiopiya, Amharcha
Statistika
Postlar filtri


ይች አለም ከዋናው ይልቅ ለኮፒው ክብር ትሰጣለች!

በአንድ ወቅት ታላቁ ኮሜዲያን ቻርሊ ቻፕሊን ፈረንሳይ ውስጥ ሲዘዋወር ቻርሊ ቻፕሊንን(እሱን) የማስመሰል ውድድር እንደተዘጋጀ ይመለከታል።

ይህኔ ቻፕሊን ለምን በዚህ እኔን በማስመሰሉ ውድድር ላይ አልሳተፍም ይልና ስም ቀይሮ ይመዘገባል። በዚሁም መሰረት ከ12 ተወዳዳሪዎች ጋር ተወዳደረ።

ራሱን በማስመሰሉ ውድድር ስንተኛ እንደወጣ ታውቃላችሁ? በ6 እስመሳዮች ተበልጦ 7ኛ ደረጃን ይዞ አጠናቋል።

ከዚያም ቻፕሊን ይህች ዓለም ከዋናዎች ይልቅ ለአስመሳዮች ክብርና ሽልማት እንደምታጎርፍ ተገነዘበ።

@ethio_tksa_tks


ያንተ ተስፋ ማነው?!

እንደ አንተ ጭንቀትና ሀሳብ ቢሆን ዛሬን ማየት የማይታሰብ ነበር፤ ያንን ጊዜ ማለፍ ቅዠት ነበር፤ ግን አለፍከው፤ ያልገመትከው ሁሉ ሆነ አንተ ተስፋ ቆርጠህ ስትጨርስ ፈጣሪ ጀመረ። ያንተ ተስፋ የዚህ አለም ተለዋዋጭ ነገር አይደለም! ያንተ ተስፋ የማይለወጠው፣ በዘመናት የማያረጀውና የማያልፈው ፈጣሪህ ነው!

መልካም ቀን ተመኘን🙏

SHARE||@ethio_tksa_tks


ከእርስዎ ጋር ምን ይቆያል?

What Will Stay With You?


ዓይነ ስውር ሰው ለመጀመሪያ ጊዜ ሲያይ የሚጥለው ነገር በህይወቱ ሙሉ የረዳውን ዱላ ነው።"😐


SHARE||@ethio_tksa_tks


🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
እኛ እኮ ኢትዮጵያውያን ነን! እንደሌሎቹ የነፃነት ቀን ሳይሆን የድል ቀን አድዋን እናከብራለን። ክብር! አጥንታቸውን ለኢትዮጵያ ለገበሩ አርበኞች አባትና እናቶቻችን ይሁን።

SHARE||@ethio_tksa_tks


"በጥጋባቸው ዓድዋ ላይ ተዋግተው ድል ሆኑ። እኔ ግን በድንቁርናቸው ብዛት የእነዚያን ሁሉ ሰዎች ደም በከንቱ መፍሰሱን እያየሁ ድል አደረግሁ ብዬ ደስ አላለኝም"


    አፄ ምኒልክ ለአውሮፓዊው ዲፕሎማት ሙሴ ሸፍኔ በመጋቢት 23 ቀን 1888 ዓ.ም. በጻፉት ደብዳቤያቸው ከገለጹት


SHARE||@ethio_tksa_tks


ከአድዋ ድል ጋር የማገናኘው ሁሌ የሚያሳዝነኝ አንድ ታሪክ አለ፡፡

#Ethiopia  | አሜሪካን ጨምሮ የነጮች የበላይነት ሰፍኖ የኖረበትን  የዘር ስርዓት ሳስብ ህይወታቸውን ከፍለው ከጥቁርና ነጭ ቀለም የገዢ ተገዢነት ትርክትና ሰቀቀን የታደጉንን ጀግና አባቶቻችንን አከብራለሁ፡፡ አድዋ ላይ ተሸንፈን ቅኝ ተገዝተን ቢሆን ኖሮ r  የኢትዮጵያና የህዝቦቿ ታሪክ ፣ የኛም ስነልቡና ዛሬ ያለው ቅርጽ አይኖረዉም ነበር፡፡

ከቀለም ፖለቲካ አዛሳኝ ታሪኮች አንዱን እነሆኝ!

በአሜሪካ ምናልባትም በዓለም የ20ኛው ክፍለዘመን የፍርድ ውሳኔ ታሪክ በእድሜ ትንሹ የሞት ፍርደኛ  የ14 ዓመቱ ጆርጅ ስቲኔይ ጁኒየር ነው፡፡

ጆርጅ ስቲኔ ፍርድ ቤት የቀረበው የ11 እና የ7 ዓመት ዕድሜ ያላቸው ቤቲና ሜሪ የተባሉ ሁለት ነጭ ህጻናትን ገድለሃል ተብሎ ነው፡፡

የሟቾቹ አስከሬን በመኖሪያ ቤታቸው አቅራቢያ እንደተገኘ  ትንሹ ጆርጅ ገዳይ ተብሎ ተጠረጠረና ፍርድ ቤት ቀረበ፡፡

ጉዳዩን ይመለከቱ የነበሩ ሁሉም ዳኞች ነጮች ሲሆኑ የሞት ፍርድ ሲወስኑበትም አጠቃላይ የፍርድ ሂደቱ ሁለት ሰዓት ብቻ ነበር የወሰደው፡፡ የመጨረሻው ቀን የፍርድ ውሳኔውን ያስተላለፈው ችሎት በተጀመረ በ10 ደቂቃ ተጠናቀቀ፡፡

ምስኪኑ ጆርጅ የተከሳሽ ሳጥኑ ውስጥ ቆሞ ሲያለቅስ ወላጆቹ አጠገቡ ቀርበው አይዞህ እንዳይሉት እንኳን በፍርድ ቤቱ ፖሊሶች ተከልክለዋል፡፡ ዳኞቹ በዚህ ምስኪን ጥቁር ህጻን ላይ ሞት ፈረዱበት፡፡

ጆርጅ ብቸኛ መጽናኛው በእጁ የያዘው መጽሃፍ ቅዱስ ብቻ ነበር፡፡ ደጋግሞ መጽሃፍ ቅዱሱን እያሳየና እየማለ “እኔ አልገደልኳቸውም፣ ምንም ወንጀል አልፈጸምኩም” እያለ ቢማጸንም የሚሰማው አላገኘም፡፡

ጆርጅ ከፍርድ በኋላ ከሚኖርበት ከተማ 50 ማይል ርቆ ወደሚገኝ ወህኒ ቤት ሲወሰድ እናትና አባቱ ደግሞ በግድ ከመኖሪያቸው ለቀው ወደሌላ ከተማ እንዲሰደዱ ተደረጉ፡፡ ጆርጅ የሞት ፍርዱ አስኪፈጸምበት በእስር ቤት በቆየባቸው 81 ቀናት እናትና አባቱ ለስንብት እንኳን አንድም ቀን አይኑን እንዲያዩት አልተፈቀደላቸውም፡፡

የሚደንቀው ነገር ምስኪን ጆርጅ የፍርድ ውሳኔው ከተላለፈበት ቀን ጀምሮ ግድያው እስኪፈጸምበት ቀን ድረስ መጽሃፍ ቅዱሱ ከእጁ አልተለየም፡፡ የሚናገረውም አንድ ነገር ብቻ ነው፡፡

“እኔ ማንንም አልገደልኩም፣ ምንም አላጠፋሁም፣ እባካችሁ ልቀቁኝ”
በመጨረሻው ቀን ጆርጅ ስታኔይ ጁኒየር በ14 ዓመቱ ገዳይ ወንጀለኛ ተብሎ 5ሺህ 330 ቮልት ሃይል ያለው ኤሌክትሪክ ከእግር እስከጭንቅላቱ ድረስ ተለቆበት ተገደለ፡፡

ምሰኪን ጆርጅ ከተገደለ ከ70 ዓመታት በኋላ ግን አስደንጋጭ ታሪክ ተሰማ፡፡ የደቡብ ካሮላይና ፍርድ ቤት ዳኛ ያ ህጻን የተባለውን የግድያ ወንጀል እንዳልፈጸመ አረጋግጠው ንጽህናውን አወጁ፡፡

ነጮቹን ህጻናትን የገደላቸው 18 ኪሎ የሚመዝን የብረት ምሰሶ መሆኑንና ለንድ የ14 ዓመት ህጻን ይህን ያህል ክብደት ያለው ብረት ሰው ላይ መሰንዘር ቀርቶ ከመሬት አንስቶ ለመሸከም እንኳ የማይታሰብ መሆኑ በምርመራ ተረጋግጧል፡፡

በመጨረሻም ጆርጅ ላይ የተካሄደው ምርመራ ሆን ተብሎ የሟቾችን ገዳይ አገኘን ለማለት የተፈበረከ የሃሰት ክስ መሆኑም ታወቀ፡፡ “በጊዜው ምስኪኑን ጆርጅ ለሞት ያበቃው ብቸኛ ጥፋት ጥቁር መሆኑ ብቻ ነበር” ተባለ፡፡

ይህ አሳዛኝ ታሪክ ኋላ ላይ ስቴፈን ኪንግ የተባለው ደራሲ አድናቆት ያገኘውን "The Green Mile" መጽሃፍ እንዲጽፍ ምክንያት ሆኖት ነበር፡፡

ስቴፈን በመጽሃፉ ምን ይላል?  “ቀደም ባለው ዘመን የነበረውም ይሁን አሁን ያለው የሰው ልጅ ጨካኝ ነው፡፡ ልዩነቱ ያኔ ጭካኔ ተደብቆ ይኖር ነበር ዛሬ ደግሞ የሚደበቅ ነገር ምንም የለም፣ ሁሉም ያውቀዋል”

‘’People were cruel then, just as they are now. The only difference is that before, cruelty was hidden, whereas now it is exposed for everyone to see’’

ስቴፈን እንዳለው "ዛሬ የሰው ልጅ የራሱን ጥቅም ከሰው ህይወት በላይ ለምን ያስቀድማል?" ብሎ መጠየቅ ልፋት ነው፡፡ ድሮም የሰው ልጅ እንዲያ ነበር፡፡ ልዩነቱ ያኔ ብዙ ነገር ተደብቆ ይኖር ነበር፡፡ ዛሬ የቱም የሰው ልጅ ጭካኔ ድርጊት በደቂቃዎች ልዩነት ጸሃይ ይሞቀዋል፡፡

እኔ ግን እላለሁ፡፡ በምድር ላይ በነጮች በተገዙ ጥቁሮች ላይ ከደረሰው በደል በላይ በሰው ልጅ የደረሰ ታሪክ የመዘገበው አስከፊ በደል የለም፡፡ 

እንኳን ለአንጸባራቂው የአድዋ ድል በዓል አደረሰን!!

Via መላኩ ብርሃኑ🙏🙏🙏🙏

Share @ethio_tksa_tks




አድዋ የኢትዮጵያ የአፍሪካውያን እና የመላው ጥቁር ህዝብ ድል 🇪🇹

እንኳን ለ129ኛው የአድዋ ድል በዓል አደረሳችሁ።

@ethio_tksa_tks


«-መቃብሬን ስትጎበኝ የምትገዛቸው አበባዎች ለእኔ አይጠቅሙኝም እና በራሴ ላይ እንድታለቅስም አልፈልግም፤ ብቻ ሳንድዊች ገዝተህ ለመቃብር ጠባቂ ስጠው።

«

« ለተወሰነ ጊዜ ብቻህን ለመሆን ሞክር የሰው ልጅ ሁል ጊዜ የስነልቦና ችግሮቹን በበላይነት ከማድከም በስተቀር በእውነት ከንቱ ሆኖ ታገኘዋለህ!

« -ክፍልህ ውስጥ የገደልከው ሸረሪት እድሜውን ሙሉ አንተን የክፍል ጓደኛው እንደሆንህ ቢያስብህስ!?

« -የሃሳብ ትኩሳት አለብኝ! ምን እንደተፈጠረ ምን እንደሚሆን እና ምን ሊሆን እንደሚችል አስባለሁ! ያልተከሰቱ ነገሮች አስባለሁ፤ እና ቢከሰቱ ምን ሊፈጠር ይችላል..

«-በውስጣችሁ ያለውን እሳት እውቅና አትስጡት፤ ግን ፈገግ በሉ እና በፓርቲ ውስጥ ለምበላው ጥብስ የተዘጋጀ እሳት ነው በሉ።

« -ህልማቸውን በልጃቸው ትከሻ ላይ ከሚጥሉ እና በአረጋውያን መንከባከቢያ ውስጥ ከእንቅልፉ ሲነቃ ከቆየ ሰው የከፋ ነገር የለም!

« -ወዳጄ ሆይ ይህን ጥንካሬ አትመን፤ ውስጤ ተሰባሪ ነው ጥሩም አይሰማኝም።

”-ሰው ብዙ ሰዎችን (መንጋን) መምሰል የለበትም ብቻህን ብትሆንም ተለየ ሁን።

«-ሰዎች ብርቱዎችን ይጠላሉ ይታዘዛሉ፤ ደካሞችንም ይወዳሉ ይንቋቸዋልም!

« -እንዴት አመስጋኝ ልሁን? ማንንስ ላመስግን? መጥፎ ጊዜዎቼን ለብቻዬ ኖሪያለሁ!

ፊዮዶር ፡ ዶስቶቭስኪ

የቱ ተመቻቹ? comment ላይ ፃፉልን




"ከማን ጋር እንደሳቅክ ልትረሳ ትችላለህ፣ ነገር ግን ከማን ጋር እንዳለቀስክ በፍጹም አትረሳም። ህመም ከደስታ ይልቅ በነፍስ ላይ በጠራ ምላጭ ይቀርጻል፣ በሀዘን የተፈጠሩ ትስስሮችም ብዙውን ጊዜ በደስታ ከተፈጠሩት የበለጠ ጠንካራ ናቸው። ምክንያቱም በዝምታ ጊዜ ልቦች ከቃላት በላይ የሆነ ቋንቋ ይናገራሉ።"

©ካህሊል ጂብራን

SHARE||@ethio_tksa_tks


ለመላው #የእስልምና እምነት ተከታዮች በሙሉ.... 🕌
እንኳን ለ1446 ኛው ታላቁ የረመዳን ጾም በሰላም አደረሳችሁ፡፡

መልካም ጾም


ከቻልክ መልካም ነገር ሁሉ የሚገባበት በር ሁን።
ካልሆነም ብርሃን የሚገባበት መስኮት ሁን።
ካልሆነም የደከማቸው የሚደገፉበት ግድግዳ ሁን።

ሁሌም ቢሆን መልካም ነገር ይዞ መንቀሳቀስን አትርሳ። ✨




Choose wisely 😌 😉 👌 😏 💯 ☺️


ነጻ ስጦታዎች!

✅“እጅግ የላቀው ብልጽግና ጥበብ ነው፡፡
✅ ጠንካራ የተባለው መሳሪያ ትእግስት ነው፡፡
✅አለ የተባለው ጥበቃ በፈጣሪ ላይ ያለን እምነት ነው፡፡
✅ ፈዋሽ የተባለው መድሃኒት ሳቅ ነው፡፡
✅ እጅግ አስገራሚ የሆነው እውነታ ደግሞ እነዚህ የጠቀስናቸው ሁሉም ነገሮች ሙሉ በሙሉ ነጻ መሆናቸው ነው"

እነዚህን ስጦታዎች ከተጠቀለሉበት ከፍተን እናውጣቸው! እንጠቀምባቸው!

መልካም ቀን ለሁላችሁ!

SHARE||@ethio_tksa_tks


በሚያታልል ውሸት ተኝቶ ከመኖር ይልቅ በሚያም እውነት መቀስቀስ ይሻላል።"


©ዶ/ር ፊል ማክግሮ

SHARE||@ethio_tksa_tks


ክፋቀን ሊያስተዛዝበን እንጂ ሊገለን አይመታም 😪 ቀንያልፋል እስኪያልፍ ያለፋል


መሪነት በአንድ ወቅት ጡንቻ ማለት ነው ብዬ አስብ ነበር ዛሬ ግን ከሰዎች ጋር መግባባት ማለት ነው

©Mahatma Gandhi

SHARE||@ethio_tksa_tks

20 ta oxirgi post ko‘rsatilgan.