በፍትሀብሄር የክርክር መዝገብ ላይ የእስር ትእዛዝ የሚታዘዝበተ ሁኔታወች
1ኛ) በፍ/ስ/ህ/ቁ 156 ላይ አንደተደነገገው ተከሳሹ በፍርድ ቤት የተሰጠውን የማገጃ ትእዛዝ ያላከበረ ወይም በትእዛዞቹ ላይ የተሰጡት ውሳኔዎች ያልጠበቀና እግዱን የጣሰ ከሆነ ፍርድ ቤቱ የእስር ትእዛዝ ሊሰጥ እንደሚችል ያስቀምጣል፡፡
2ኛ) በፍ/ስ/ህ/ቁ 161(2) መሰረት
ፍ/ቤቱ ከፍርድ በፊት ክርክር የተነሳበትን ንብረት እንዳይበላሽ ለመጠበቅ የሚሰጠውን ማንኛውም ዓይነት ትእዛዝ የማይፈጽም አካል ላይ የእስር ትእዛዝ እንደሚሰጥ መረዳት ይቻላል፡፡
3ኛ) በፍ/ስ/ህ/ቁ 267 እና 268 ላይ እንደተገለጸው አንድ ምስክር ወይም ተከራካሪ ወገን በችሎት ቀርቦ እንዲመሰክር ወይም በእጁ ወይም በስልጣኑ ስር ማንኛውም ማስረጃ እንዲያቀርብ የፍርድ ቤት መጥሪያ ደርሶት ያለ በቂ ምክንያት ትእዛዙን ያልፈጸመ ወይም የማይፈጽምበትን ምክንያት ቀርቦ ያላስረዳ ከሆነ ፍ/ቤቱ የእስር ትእዛዝ እንደሚያወጣ ያስቀምጣል፡፡
4ኛ) በፍ/ስ/ህ/ቁ 386(4) ላይ እንደተመለከተው የአፈጻጸም ማመልከቻው የቀረበው አንድ የተወሰነን ገንዘብ ለማስከፈል ወይም የተፈረደው ፍርድ እንዲፈጸም ሆኖ የአፈጻጸም ተከሳሽ በመጥሪያው መሰረት ያልቀረበ ከሆነ ፍ/ቤቱ ታስሮ እንዲቀርብና እንደፍርዱ የማይፈጽምበትን ምክንያት ለመጠየቅ ይችላል በማለት ተደንድጓል፡፡
5ኛ) በፍ/ስ/ህ/ቁ 387 መሰረት የፍርድ ባለእደው ፍርዱ እንዳይፈጸም መሰናክል የፈጠረ ወይም የፍረዱን አፈጻጸም ለማዘግየት ንብረቱን ከፍርድ ቤቱ ስልጣን ክልል ውጪ ለማሸሸ፤ ለመደበቅ ወይም እራሱ ለመሰወር ያቀደ መሆኑን የሚያረጋገወጥ በቃለ መሀላ የተደገፈ አቤቱታ ከቀረበ ፍ/ቤቱ ባለእዳው በቀጥታ እንዲታሰር ትእዛዝ ሊሰጥ እንደሚችል ያስገነዝባል፡፡
6ኛ) በፍ/ስ/ህ/ቁ 389(1) ላይ እንደተመለከተው የፍርድ ባለእዳው ያለ በቂ ምክንያት ፍርዱን የማይፈጽም መሆኑ ሲረጋገጥ ወይም መፈጸም እየቻለ ለመፈጸም ፈቃደኛ ያልሆነ መሆኑን ሲረጋገጥ ፍ/ቤቱ የፍርድ ባለእደውን እስከ 6ወር ሊደርስ የሚችል እስራት ሊፈርድበት ይችላል፡፡
7ኛ) በፍ/ስ/ህ/ቁ 481 ላይ እንደተገለጸው ማንም ሰው የችሎት ስራ ዳኛው በሚሰራበት ጊዜ ዳኛው ስራውን እዳይሰራ ያወከው ከሆነ ወይም በችሎት የተከለከሉ ተግባራት የፈጸመ ወይም ሀሰተኛ የምስክርነት ቃል የሰጠ መሆኑን የተረጋገጠ በአጠቃላይ ችሎት ደፍሮ ከተገኘ እስከ 3 አመት እንደሚቀጣ ተደንግጓል፡፡👇👇
https://t.me/ethiolawtips