#FactCheck ረዳት ፕሮፌሰር ጌትነት አልማው የተባለ ግለሰብ ያሰራጨው ሀሰተኛ ምስል
በአማራ ክልል ሰሜን ጎጃም ዞን ደቡብ አቸፈር ወረዳ በተፈጸመ የድሮን ጥቃት ህጻናትን እና ነፍሰ ጡር ሴቶችን ጨምሮ በርካታ ሰዎች መገደላቸውን ቢቢሲ ዛሬ የሰራውን ዘገባ በማንሳት "ስትዋሹም እየተናበባችሁ" በማለት ግለሰቡ መረጃ ማጋራቱን ተመልክተናል።
ግለሰቡ ቢቢሲ ለአማራ ክልል ዜናው የተጠቀመበት ምስል በትግራይ ጦርነት ወቅት ትግራይ ቴሌቭዥን የተጠቀመበት መሆኑን በመጥቀስ ይህን ያሳያል ያለውን ምስል ከቢቢሲ ዘገባ ጋር በማመሳከር አቅርቧል።
"ውሸትን እንደትግል መሳሪያ መጠቀም የነበረ፣ ያለና የሚኖር ሃቅ ነው። ነገርግን ፕሮፓጋንዳ ሳይንስ እና የላቀ ጥበብ የሚሻ እንጂ ተዘርፍጠ'ው የሚሰሩት ቀላል ስራ አይደለም" ያለው ረዳት ፕሮፌሰሩ አክሎም "በሰሜኑ የሃገራችን ክፍል በነበረው ጦርነት ከሁለት ዓመት በፊት ለፕሮፓጋንዳ ፍጆታ የዋለን ምስል ተጠቅሞ ፕሮፓጋንዳ መስራት አንድም ፕሮፓጋንዳን መናቅ ሁለትም ጅላንፎ'ነት ስለሆነ ማስተካከያ ልታደርጉና ተናባችሁ ልትዋሹ ይገባል" በማለት 77 ሺህ ገደማ ተከታይ ባለው የፌስቡክ ገፁ ላይ መረጃ አጋርቷል።
በዚህ ዙርያ ኢትዮጵያ ቼክ ማጣራት ያደረገ ሲሆን ግለሰቡ ያሰራጨው ምስል በቅንብር የቀረበ እና ሀሰተኛ መረጃ መሆኑን ማየት ችለናል።
ትግራይ ቴሌቭዥን በወቅቱ፣ ማለትም ኦክቶበር 24/2022 ባወጣው ዘገባው ረዳት ፕሮፌሰር ጌትነት የተጠቀመውን ምስል ሳይሆን ሌላ የድሮን ጥቃትን ያሳያል የተባለ መሆኑን ማየት ችለናል (ምስሉ ላይ በስተቀኝ አያይዘነዋል)።
ስለዚህ ግለሰቡ ቢቢሲ ለአማራ ክልል ዘገባው የቆየ የትግራይ ምስል እንደተጠቀመ አድርጎ ያሰራጨው መረጃ ሀሰተኛ መሆኑን አረጋግጠናል።
ኢትዮጵያ ቼክ
@EthiopiaCheck