በኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት በላስልጣን እና በኢትዮጵያ ፋርማሲስቶች እና የፋርማሲቲካል ሳይንቲስቶች ማህበር በዲያስፖራ (EPPAD) መካከል በጋራ ለመስራት የስምምነት ሰነድ ተፈራረሙ፡፡
ጥር/20/2017 አዲስ አበባ፡ ባለስልጣኑ መቀመጫውን በቨርጂንያ አሜሪካን ካደረገው የትውልደ ኢትዮጵያውያን የመድኃኒት ባለሙያዎችና ሳይንቲስቶች ማህበር (EPPAD) ጋር የመግባቢያ ሰነድ ተፈራርመዋል፡፡
በፊርማ ስነ-ስርዓቱ ወቅት የእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግር ያደረጉት የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር ሔራን ገርባ እንደተናገሩት ባለስልጣኑ የአፍሪካ የልህቀት ማዕከል ለመሆን እያደረገ ባለው ጥረት ማህበሩ ከዚህ ቀደም የቁሳቁስ ድጋፍ ማድረጉን ገልፀው ተቋሙ ፋርማሲስቶች እና የፋርማሲቲካል ሳይንቲስቶች ማህበር አባላት ያላቸውን አቅም ፣ውቀትና ልምድ በሀገር ውስጥ የቁጥጥር ዘርፉን ለማጠናከር በሚደረገው ጥረት ቴክኒካዊ ድጋፍ እንዲያደርጉ እድል የሚፈጥር ነው ብለዋል፡፡
ባለስልጣኑ ከሙያ ማህበሩ ጋር የስምምነት ሰነዱ በተፈረመበት ወቅት ባለስልጣኑ የአለም ጤና ድርጅት ማቹሪቲ ሌቭል 3 ቤንችማርክ ለመደረግ ዝግጅት እያደረገ ባለበት ወቅት መሆኑ መልካም አጋጣሚ መሆኑን በማስረዳት በቀጣይ የምግብና የጤና ግብዓት ቁጥጥር ከታች እስከ ላይ ለማጠናከር በሚሰራው ስራ የማህበሩ አባለት የካበተ እውቀትና ልምድ ሀገር ውስጥ ለሚገኙ ባለሙዎች በማካፈል ሚናቸውን እንዲወጡ ስምምነቱ በር ከፋች መሆኑ አስታውቀዋል፡፡
የማህበሩ የሬጉላቶሪ ቡድን መሪ የሆኑት አቶ አሌክስ አካሉ በበኩላቸው ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ትውልደ ኢትዮጵያውያን ሐገራቸውን በሙያቸው እንዲያግዙ ላመቻቸው እድል አመስግነው በጋራ መግባቢያ ሰነዱ መሰረት ድጋፍ ማድረግ በሚቻልበት መንገድ ንግግር አድርገዋል፡፡