የተመጣጠነ የምግብ ችግርን ለመቅረፍ የተመረጡ ምግቦችን በንጥረ ነገሮች ለማበልፀግ አስገዳጅ መመሪያ መዘጋጀቱ ተገለፀ
መጋቢት 23/2017፡- የኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ባለስልጣን በንጥረ ነገሮች የበለፀጉ የዘይትና ዱቄት ምርቶችን ለመመዝገብ የሚያስችል አስገዳጅ መመሪያ ማዘጋጀቱን ተከትሎ በመመሪያው ላይ አስተያየት እንዲሰጡበት በሐዋሳ ቅርንጫፍ የኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ባለስልጣን በተዘጋጀው መድረክ ላይ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የቅርንጫፉ የምግብ ተቋማት ህግ ማስፈፃምና ኢንስፔክሽን ዴስክ ኃላፊ አቶ ብሩህ አለማየሁ እንደተናገሩት የተመጣጠነ የምግብ እጥረተ የህብረተሰብ ጤና ችግር መሆኑን ገልፀው መንግስት የህዝብን የአመጋገብ ስርዓት ለማሻሻል የተለያዩ ስራዎችን እየሰራ እንደሚገኝ አስረድተዋል፡፡
እንደአቶ ብሩህ ንግግር ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ በአዋጅ በተሰጠው ስልጣን መሰረት ምግቦችን በማዕድን፣ ቫይታሚን እና ሌሎች ንጥረ ነገሮች ለማበልፀግ አስገዳጅ መመሪያ ማዘጋጀቱንና ይህ መድረክም ባለድርሻ አካላት በዋነኝነት የዘይትና የዱቄት አምራቾች አስተያየት እንዲሠጡበት የተዘጋጀ ነው ብለዋል፡፡
በመድረኩ በምግብ ማበልፀግ አስፈላጊነት እና የዱቄትና የዘይት አምራች ተቋማት ሊዘረጉት ስለሚገባው የዉስጥ ጥራት ዝርጋታ ፅሁፎች የቀረቡ ሲሆን ባለስልጣኑ ያዘጋጀው አስገዳጅ የምግብ ማበልፀግ መመሪያ ለውይይት ቀርቦ ሠፊ ውይይት ተደርጓል፡፡ በውይይቱ በሐዋሳ ቅርንጫፍ ዱቄትና ዘይት ማምረቻ ፈቃድ ወስደው እየሰሩ ያሉ ተቋማት የተሳተፉ ሲሆን ከተሳታፊዎች ለተነሱ ጥያቄዎችም የኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ባለስልጣን ሐዋሳ ቅርንጫፍና ከዋናው ቢሮ በተገኙ ባለሙያዎች ማብራሪያ ሲሰጥ የቅርንጫፉ ኃላፊ አቶ ፍቃዱ ንማኔ እንደተናገሩት የምግብ ማበልፀጉን ተግባራዊ የማያደርጉ ተቋማት ላይ እርምጃ መውሰዱ ይቀጥላል ብለዋል።