በ1996 አንድ ቀን አንደኛው ልጄ ከትምህርት ቤት ግራ ተጋብቶ ተመለሰ።ተሰላችቶና ማጥናትም አስጠልቶት ነበር።በእውነተኛው ዓለም ላይ ተግባራዊ የማላደርገውን ዕውቀት በማጥናት ጊዜዬን የማጠፋበት ምክንያት ምንድን ነው? ሲል ጠየቀኝ
እኔም ብዙም ማሰብ ሳያስፈልገኝ ❝ምክንያቱም ጥሩ ውጤት ካላመጣህ ወደ ኮሌጅ መግባት አትችልም❞ አልኩት
❝ኮሌጅ ብገባም ባልገባም ሀብታም መሆኔ አይቀርም❞ ሲል መለሰልኝ
"“ከኮሌጅ ካልተመረቅህ ጥሩ ስራ አታገኝማ"” አልኩት በእናት ጭንቀት።ታዲያ ጥሩ ስራ ካላገኘህ ሀብታም ለመሆን የምታስበው እንዴት ነው?" ብዬ ጠየኩት
ልጄ ባለመርካት ስሜት ውስጥ ሆኖ ጭንቅላቱን ነቀነቀ።እንዲህ ዓይነቱን ምልልስ ከዚህ በፊትም ደጋግመን ፈፅመነዋል።አንገቱን ደፍቶ ዓይኖቹን አቁለጨለጨ።የእናትነት ምክሬ ዛሬም እንደሁልጊዜው ሰሚ አላገኝም ማለት ነው ብዬ አሰብኩ
"እማ" ሲል ጀመረ።አሁን ማደመጥ የእኔ ተራ ሆነ።ከጊዜው ጋር እንራመድ እንጂ!እስኪ ዞር ዞር ብለሽ ተመልከቺ።ሀብታሞቹ ሀብታም የሆኑት በትምህርታቸው የተነሳ አይደለም።ማይክል ጆርዳንና ማዶናን ተመልከቺ!ቢልጌት የሃርቫርድ ትምህርቱን አቋርጦ ነው ማይክሮሶፍትን መስርቶ ገና በሰላሳዎቹ ዕድሜው የአሜሪካ ሀብታም ሰው ለመሆን የቻለው።በትምህርቱ ሰነፍ የተባለ ነገር ግን በዓመት ከ4 ሚሊየን ዶላር ገቢ የሚያገኝ የቤዝ ቦል ተጫዋችም አውቃለሁ።"
በመካከላችን ረዥም ዝምታ ሰፈነ።ለልጄ የምሰጠው ምክር ወላጆቼ ለእኔ ይሰጡኝ ከነበረው ጋር አንድ ዓይነት መሆኑ እየተገለጠልኝ ነበር።በዙሪያችን ያለው ዓለም ተቀይሯል፤ምክሩ ግን አልተቀየረም።ጥሩ ውጤት ማስመዝገብ ለስኬታማነት ማረጋገጫ መሆኑ አክትሟል።
📓ርዕስ፦የሀብት መንገድ
✍️ደራሲ፦ሮበርት ኪዮሳኪ
https://t.me/ethiotipsevery