ኢትዮ Tips 👨‍💻🔥


Kanal geosi va tili: Efiopiya, Inglizcha


Похожие каналы

Kanal geosi va tili
Efiopiya, Inglizcha
Statistika
Postlar filtri


ኢትዮጵያ በግዛቷ የሚያልፉ ሳተላይቶችን መረጃ መቀበል የሚያስችል ቴክኖሎጂ መግጠሟን ገለጸች።

📌ኢትዮጵያ ከሶስት ዓመት በፊት ETRSS1 የተሰኘች ሳተላይት በቻይና አጋዥነት ወደ ህዋ ማምጠቋ ይታወሳል፡፡

📌ይህች ሳተላይት በቻይና እንድትመጥቅ ቢደረግም እንጦጦ በሚገኘው ማዕከል በኢትዮጵያዊያን ባለሙያዎች ቁጥጥር ሲደረግባት መቆየቱን የኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስ እና ጂኦ ስፓሺያል ኢንስቲትዩት አስታውቋል፡፡

📌ኢትዮጵያ የታላቁ ህዳሴ ግድብ ውሃ አያያዝን ጨምሮ የከርሰ ምድር ውሃ መጠንን ለማወቅ፣ የመሬት ላይ ሽፋን እና ለተለያዩ ጥናትና እና ምርምር ስራዎች የሚያግዙ ምስላዊ መረጃዎችን ከዚች ሳተላይት ማግኘቷ ተገልጿል፡፡

📌ኢትዮጵያ በግዛቷ በሚያልፉ ዓለም አቀፍ ሳተላይቶች መረጃዎችን መቀበል እና ተጨማሪ ገቢ ማስገኘት የሚያስችል ቴክኖሎጂ ገጠማን እያካሄደች መሆኑን  አስታውቃለች ።

📌የመረጃ መቀበያ ማዕከሉ ከዚህ በፊት የተገነባ ሲሆን አሁን እየተከናወነ ያለው ስራ ከሌሎች ሳተላይቶች መረጃ መቀበል የሚያስችል ቴክኖሎጂ ገጠማ ስራዎችን ማጠናቀቅ መሆኑንም ታውቅዋል ።

📌ይህ ተግባር በኢትዮጵያ ግዛት ውስጥ የሚያልፉ የሌላ ሀገራት እና ተቋማት ንብረት የሆኑ ሳተላይቶች በደቂቃ ተሰልቶ የሚገኝ ገቢ ሲሆን ከሳተላይቶቹ ባለቤቶች ጋር በመተባበር እና መረጃዎችን በመቀበል አገልግሎቱን ለተለያዩ ዓለም አቀፍ ኩባንያዎች እና ተቋማት በክፍያ ለመስጠት መታቀዱን ሰምተናል፡፡

📌በእንጦጦ ሳተላይት መቆጣጠሪያ ማዕከል የተገነባው ይህ መረጃ መቀበያ ማዕከል ምስሎችን በ7 ነጥብ 3 ዲያሜትር ርቀት ላይ በማንሳት ጥራት ያላቸውን መረጃዎች ለመንግስት ተቋማት በነጻ ለግል ተቋማት ደግሞ በክፍያ እያገኙ መሆኑንም ኢንስቲትዩቱ ገልጿል፡፡

══════❁✿❁═══════


✳️ ስለ ኢንተርኔት ምን አልባት የማታውቁት አስገራሚ እውነታዎች;-

⓵ አማዞን፣ በዋናነት ሲጀመር የታተሙ መፅሐፎችን የሚሸጥ ካምፓኒ ነበር፣ አሁን ግን ከታተሙት መፅሐፎች ይበልጥ ብዙ ኤሌክትሮኒክስ መፅሐፎችን እየሸጠ ነው።

⓶ ወደ 1.8 ቢሊዮን የሚሆኑ የአለማችን ህዝቦች በኢነትርኔታ የተሳሰሩ ሲሆን፣ ነገር ግን 450 ሚሊዮን የሚሆኑት ብቻ ኢንጊሊዘኛ ቋንቋን መናገር የሚችሉት።

⓷ ሲዊዲን በኢንተርኔት ተጠቃሚዎች ከፍተኛውን ፐርሰንትኤጅ ያላት ሀገር ስትሆን፥ እሱም 75% ህዝቦቻ የኢንተርኔት ተጠቃሚዎች ናቸው።

⓸ እስከ 50 ሚሊዮን ተጠቃሚዎችን ለማግኘት ሬዲዮ 38 አመታቶችን ወስዶበታል፣ እና ለቴሌቪዥን ደግሞ 13 አመታትን ሲወስድበት፥ ለወርልድ ዋይድ ዌብ ”World Wide Web” በ 4 ዓመቶች ውስጥ ብቻ 50 ሚሊዮን ተጠቃሚዎችን ለማግኘት ችሏል።

⓹ በየቀኑ 247 ቢሊዮን የኢሜል መለእክቶች ይላካሉ። ከነዚህ መልእክቶች 81% የሚሆኑት አላስፈላጊ መልእክቶች ወይም ለጥፋት ታስበው የሚላኩ ናቸው።

⓺ በእያንዳንዱ ደቂቃ ውስጥ፣ የአስር ሰዐቶች ርዝማኔ ያላው ቪዲዮ በዩቲዩብ”YouTube” ድረ ገፅ ላይ ይጫናል።

⓻ በአንድ ወር ውስጥ ከአንድ ሚሊዮን በላይ የድረ-ገፅ የመለያ ስሞች ወይም ዶሜኖች ይመዘገባሉ።

════❁✿❁ ═══════
https://t.me/ethiotipsevery


✳️ የፌስብክ አካውንታችንን እንዴት ማጥፋት እንችላለን ?

    
➲ 1. በመጀመሪያ ወደ Facebook አፕ ገብተን ወደ ሴቲንግ እንገባለን

➲ 2.ከዛ Your facebook information የሚለዉ ጋር Access and control የሚል Option አለ እሱን ንኩት

➲ 3.Deactivation and deletion የሚል አለ ከሱ በታች እንደዚ የሚል ታገኛላቹ Temporarily Deactivate or Permanently Delete your account እሱን በመንካት በቀላሉ መደለት ትችላላቹ ማለት ነዉ።


══════❁✿❁ ═════════                                           https://t.me/ethiotipsevery                                 ══════════❁✿❁══════════
    


Good morning 🌄🥰


✅የአለማችን አንጋፋ የ Bitcoin ባለቤት ሃገሮች👀

💵💵💵💵💵💵💵💵💵👀
1. America🇺🇸 የአለምን Economy በአንደኝነት በመምራት የምትታወቀው America ወደ 213, 246 የሚጠጋ Bitcoin  በመያዝ በCrypto አለመም ሃያልነቷን አስቀጥላለች።

2. China🇨🇳 ከ America በመቀጠል የአለመችንን Economy  የምትመራው China በCrypto ም  190,000 BITCOIN በመያዝ ሁለተኛ ደረጃን ይዛለች።

3. United  Kingdom🇬🇧 61,000 BTC በመያዝ ሶስተኛ ደረጃን ይዛለች።

4. EI Salvador🇸🇻 5,800 BTC በመያዝ አራተኛ ላይ ትገኛለች።

5. Ukrain🇺🇦 1,334.6 BTC በመያዝ አመስተኛ ጀረጃ ላይ ተቀምጣለች።
══════❁✿❁═══════                                                             
https://t.me/ethiotipsevery


በ1996 አንድ ቀን አንደኛው ልጄ ከትምህርት ቤት ግራ ተጋብቶ ተመለሰ።ተሰላችቶና ማጥናትም አስጠልቶት ነበር።በእውነተኛው ዓለም ላይ ተግባራዊ የማላደርገውን ዕውቀት በማጥናት ጊዜዬን የማጠፋበት ምክንያት ምንድን ነው? ሲል ጠየቀኝ

እኔም ብዙም ማሰብ ሳያስፈልገኝ ❝ምክንያቱም ጥሩ ውጤት ካላመጣህ ወደ ኮሌጅ መግባት አትችልም❞ አልኩት

❝ኮሌጅ ብገባም ባልገባም ሀብታም መሆኔ አይቀርም❞ ሲል መለሰልኝ

"“ከኮሌጅ ካልተመረቅህ ጥሩ ስራ አታገኝማ"” አልኩት በእናት ጭንቀት።ታዲያ ጥሩ ስራ ካላገኘህ ሀብታም ለመሆን የምታስበው እንዴት ነው?" ብዬ ጠየኩት

ልጄ ባለመርካት ስሜት ውስጥ ሆኖ ጭንቅላቱን ነቀነቀ።እንዲህ ዓይነቱን ምልልስ ከዚህ በፊትም ደጋግመን ፈፅመነዋል።አንገቱን ደፍቶ ዓይኖቹን አቁለጨለጨ።የእናትነት ምክሬ ዛሬም እንደሁልጊዜው ሰሚ አላገኝም ማለት ነው ብዬ አሰብኩ

"እማ" ሲል ጀመረ።አሁን ማደመጥ የእኔ ተራ ሆነ።ከጊዜው ጋር እንራመድ እንጂ!እስኪ ዞር ዞር ብለሽ ተመልከቺ።ሀብታሞቹ ሀብታም የሆኑት በትምህርታቸው የተነሳ አይደለም።ማይክል ጆርዳንና ማዶናን ተመልከቺ!ቢልጌት የሃርቫርድ ትምህርቱን አቋርጦ ነው ማይክሮሶፍትን መስርቶ ገና በሰላሳዎቹ ዕድሜው የአሜሪካ ሀብታም ሰው ለመሆን የቻለው።በትምህርቱ ሰነፍ የተባለ ነገር ግን በዓመት ከ4 ሚሊየን ዶላር ገቢ የሚያገኝ የቤዝ ቦል ተጫዋችም አውቃለሁ።"

በመካከላችን ረዥም ዝምታ ሰፈነ።ለልጄ የምሰጠው ምክር ወላጆቼ ለእኔ ይሰጡኝ ከነበረው ጋር አንድ ዓይነት መሆኑ እየተገለጠልኝ ነበር።በዙሪያችን ያለው ዓለም ተቀይሯል፤ምክሩ ግን አልተቀየረም።ጥሩ ውጤት ማስመዝገብ ለስኬታማነት ማረጋገጫ መሆኑ አክትሟል።

📓ርዕስ፦የሀብት መንገድ
✍️ደራሲ፦ሮበርት ኪዮሳኪ
https://t.me/ethiotipsevery


✔️ቴሌግራም የተጠቃሚዎቹን መረጃ ለመንግስታት አሳልፎ ሊሰጥ ነው!

-ቴሌግራም የተጠቃሚዎቹን መረጃ ህግን በተከተለ መልኩ ሲጠየቅ ለመንግስት ተቋማት አሳልፎ ሊሰጥ እንደሚችል አስታወቀ።ውሳኔው ድርጅቱ ለረጅም ዓመታት ይዞት የነበረውን የደንበኞቹን መረጃ አሳልፎ ያለመስጠት ፖሊሲ የሻረ መሆኑ ተገልጿል።

-በዚህም ድርጅቱ ህግን የተከተለ ጥያቄ ሲቀርብለት የተጠቃሚዎቹን አይ ፒ አድራሻ፣ ስልክ ቁጥር እና ሌሎች መረጃዎችን አግባብ ላላቸው የመንግስት አካላት እንደሚሰጥ አስታውቋል።

-ቴሌግራም እዚህ ውሳኔ ላይ የደረሰው መስራቹና ዋና ስራ አስፈጻሚው ፓቬል ዱሮቭ ባለፈው ነሐሴ ወር በፈረንሳይ መንግስት መታሰሩን ተከትሎ መሆኑ ተጠቅሷል።

-በመተግበሪያው ላይ የሚሰራጩ ፅንፈኛ አቋም ያላቸው ይዘቶችን አልተቆጣጠረም በሚል ክሱ የተመሰረተበት ዋና ስራ አስፈጻሚው በዋስ ተፈቶ ከአገር እንዳይወጣ መታገዱ ይታወሳል።ውሳኔውን አስመልክቶ ፓቬል ዱሮቭ ይፋዊ የቴሌግራም ቻናሉ ላይ ባሰፈረው መረጃ  “የቴሌግራምን ህግ የሚጥሱ ተጠቃሚዎች የስልክ ቁጥርና አይፒ አድራሻ ህግን ተከትለው ጥያቄ ላቀረቡ አካላት አሳልፈን እንደምንሰጥ ግልፅ አድርገናል” ብለዋል።


══════❁✿❁═══════                                                                           https://t.me/ethiotipsevery


✔️መነቃቃታችን እናንተ ናችሁ።ተነሳሽነታችን እናንተ ናችሁ።የእናንተ ደስታ የእኛም ደስታ ነው።ለእናንተ ጥሩና መልካም ነገር ማቅረብ የእኛ የሁልጊዜም ፍላጎት ነው።

-በየቀኑ ጣፋጭ ሀሳቦችና የታላላቅ ሰዎች አባባሎች፤እንዲሁም ምርጥ ምርጥ የአማርኛ መጽሐፎችን እንድናቀርብ በሁሉም ፖስቶቻችን ላይ ሪያክት ማድረግ አትርሱ።

እኛ ልክ እንደ ቤተሰቦች ነን።ቤተሰብቻሁን መደገፍ ደግሞ ለእናንተም ደስታ ነው ለእነሱም እርካታ ነው።ይሄ ሁሉ ለሁላችንም ትልቅ ሀይልና ብርታት ነው።

-ለምሳሌ፦ዛሬ 4 ፖስት ካለንና ሪያክቱ ትንሽ ከሆነ ነገ 3 ፖስት ይኖረናል።ከነገ ወዲያ 2....ከዛ ምንም ነገር የማንፖስትበት ጊዜ ሊመጣ ይችላል።ስለዚህ እንዳንደክምባችሁ በደምብ አበረታቱን።ሪያክት ማድረግ ብር አይቆርጥም።ጥቅል አይቀንስም።ነገር ግን ለእኛ ከፍተኛ ተነሳሽነትና ከፍተኛ ንቃት ይሰጠናል።

ከአሁን ጀመሩ!
ከዛ እንቀጥላለን..

📚https://t.me/ethiotipsevery


Have a Nice Day to You all❤️👍


ዝም ያለ ሁሉ ምላሽ መስጠት የሚችል አይደለም። ሌሎችን ላለመጉዳት ዝም ያሉም አሉ፤ በሥቃይ ውስጥ ስላሉ ዝም ያሉም አሉ። ቢናገሩ ማውራት እንደማይጠቅም የሚያውቁ አሉ! ሲናደዱ ዝም የሚሉም አሉ።ምክንያቱም ንግግራቸው ሕመማቸውን ያበዛል ወይም ሌሎችን ያሳምማል።

🗣- ማርኪስ


ያለፈውን ጊዜህን ያለጸጸት ተቀበል፤ አሁን ያለህበትን ጊዜ በልበሙሉነት ተቆጣጠር፤ እና የወደፊትህን ጊዜ ያለ ፍርሃት ፊት ለፊት ተጋፈጥ!

🗣ታላቁ ደራሲ ዴል ካርኒጌ የተናገረው


🎉DV2026 ዛሬ እኩለ ሌሊት ይጠናቀቃል‼️

👨‍💻ዲቪ ለመሙላት የመጨረሻ ቀናትስትጠብቁ ለነበራቹህ ሰዎች ለዘንድሮ ዲቪ ለማመልከት ጥቂት ሰዓታት ብቻ ቀርተውታል።

⚠️ዲቪ ለማመልከት ምንም አይነት ክፍያ አያስፈልግም።

ለማመልከት ይህን ሊንክ ይጠቀሙ 👇
https://dvprogram.state.gov/


➡️https://t.me/ethiodenkadeneth


⚠️ ማሳሰቢያ ⚠️

♟️ሰሞኑን በቴሌግራም መልዕክት የተለያዩ ሊንኮች እየተላኩ የብዙ ሰዎች የቴሌግራም አካውንት እየተጠለፈ ሲሆን ራሳችሁን እነዚህን ማስፈንጠሪያ ሊንኮች ባለመንካት ጠብቁ፤ እነዚህ ማስፈንጠሪያ ሊንኮች የቴሌግራም Login Page በማስመሰልና ስልክ ቁጥራችሁን እና ሌሎች መረጃችሁን በመቀበል አካውንታችሁን እስከመጨረሻው ይወስዱታል፡፡


———————————

⚠️ Warning ⚠️

Recently, many people's Telegram accounts are being hacked by sending various links via Telegram message chats. These hacking links will impersonate the Telegram Login Page and take your phone number also other information to take over your account.

https://t.me/ethiodenkadeneth

✔️ ቤተሰብ ከታች ጋር Mute ያደረጋችሁ Unmute✅ በማድረግ መረጃዎች ቶሎ ቶሎ እንዲደርሳችሁ ማድረግ ትችላላችሁ ።


⁉️ በ SAFARICOM SIM የምትጠቀሙ TELEGRAM ይሰራል?

አዎ 👍.
አይ 🙏.


እኔ በ VPN ነው ሚሰራልኝ


✅እጅግ አስገራሚ የFacebook እውነታዎች:-

➡️ Mark Zuckerbergን በ ፌስቡክ ብሎክ ማድረግ አይቻልም።

➡️ በየቀኑ 600,000 የፌስቡክ አካውቶች ላይ የሰበራ
(hack ) ሙከራዎች ይደረጋሉ።

➡️Mark Zuckerberg እንደ ፌስቡክ ዋና ሃላፊነቱ በአመት የሚቀበለው ደሞዝ 1$ ነው።

➡️የ like የሚለው ምልክት የመጀመርያ መጠርያው awesome ነበር።

➡️ዘመናዊ ስልክ ተጠቃሚዎች ፌስቡክን በቀን 14 ጊዜ ይጎበኙታል።

➡️ጥቂት የማይባሉ ግለሰቦች በፌስቡክ ጏደኞቻቸውን
unfriend በማድረጋቸው ምክንያት ተገለዋል።

➡️አሜሪካዊ ፌስቡክ ተጠቃሚ በአማካይ በቀን 40
ደቂቃ ፌስቡክ ላይ ያጠፋል።
በተደረገው ጥናት መሰረት ከፌስቡክ ተጠቃሚዎች
1:3 ( ከሶስቱ አንዱ) ፌስቡክን ከተጠቀሙ ቡሃላ

➡️በህይወታቸው እርካታን አይሰማቸውም።
ፌስቡክ ከመጀመርያው ቀን ጀምየሚጠቀመው
ሰማያዊ ቀለም ነው።

➡️ይህም የሆነው ባለቤቱ (Mark
Zuckerberg ) የቀይና አረንጏዴ ቀለም የማየት ችግር
(red-green color blindness) ስላለበት ነው።

➡️ፌስቡክ ውስጥ 30,000,000 የሞቱ ሰዎች
አካውንት አለ።

➡️Facebook,Twitter እና The New York
Times ከ2009 ጀምሮ በቻይና ብሎክ ተደርገዋል።

➡️8.7% የፌስቡክ አካውንቶች የውሸት (fake )
ናቸው።
➡️በየደቃቂው 1.8 ሚሊየን like ይደረጋሉ።

➡️MySpace ፌስቡክን በ2005 ለመግዛት ጠይቆ በ Mark Zuckerberg 75 ሚሊየን ዶላር በማቅረቡ
ውድ ነው በሚል ሳይሸጥ ቀርቷል።

➡️ፌስቡክ ከሞቱ ቡሃላ አካውንቶትን ማን እንደሚጠቀምበት (እንደ ወራሽ) ማድረግ
የሚያስችል አገልግሎት አለው።

➡️Whats App ከመሰረቱት ውስጥ አንዱ የሆነው

➡️Brian Action በ2009 ፌስቡክ ስራ ጠይቆ አላገኘም
ነበር። ከ5 ዓመት ቡሃላ ፌስቡክ WhatsAppን በ19 ቢሊዮን ዶላር ገዝቶታል።
══════❁✿❁═══════                                                                       
❤️ ቤተሰብ ከታች ጋር Mute😭 ያደረጋችሁ Unmute✅ በማድረግ ገራሚ ገራሚ መረጃዎች ቶሎ ቶሎ እንዲደርሳችሁ ማድረግ ትችላላችሁ ።


✅የዓለማችን ትልቁ 3ዲ ማተሚያ

➡️ፋክትሪ ኦፍ ዘ ፊዩቸር (Factory of the Future) የተሰኘ የዓለማችን ግዙፍ 3ዲ ማተሚያ በአሜሪካው ሜይን ዩኒቨርሲቲ ይፋ ሆኗል፡፡ መሣሪያው በ2019 በዚሁ ዩኒቨርሲቲ ከተሰራዉና ማስተር ፕሪንት (MasterPrint) ከተሰኘዉ 3ዲ ማተሚያ በአራት እጥፍ የሚልቅ ነዉ፡፡

➡️ማተሚያው 29 ሜትር ርዝመት፣ 10 ሜትር ስፋት እና 5 ሜትር ቁመት ያላቸውን ቁሳቁሶች ማተም የሚችል ነው። በተጨማሪም በሰዓት 227 ኪሎ ግራም የማተም አቅም አለው።

➡️በትላልቅ የግንባታ ፕሮጀክቶች ላይ የሚሳተፈዉ ይህ መሣሪያ እንደ ድልድይ ግንባታ ፣ የንፋስ ኃይል ማመንጫ እና መርከብን የመሳሰሉ ግዙፍ ቁሶችን በማምረት ሂደት ለአካባቢ ተስማሚ የሆነ የማምረቻ አማራጭ ይዞ መምጣቱን ከዩኒቨርሲቲው ድረ-ገጽ የተገኘው መረጃ ያመላክታል፡፡


══════❁✿❁═══════                                                                          


Application ጥቆማ 👉 crookcatcher

ስልካቹ ቢሰረቅ ወይም የሆነ ቦታ አስቀምጣቹ ብቴዱና የሆነ ሰው ወይም ከጠሰረቀ ሌባው ስልካቹን ለመክፈት በሚሞክርበት ሰአት የተሳሳተ Pattern or Password ሲያስገባ በፊለፊት ካሜራው ፎቶ በማንሳት በ Email በኩል ይልክላችዋል

በተጨማሪም ስልካቹ Mobile Data on ሆነ ከተሰረቀ የተሳሳተ  pattern or Password ሲያስገባ  ፎቶ አንስቶ ይያለበትን አድራሻ ጭምር በ E-mailቹ  ይልክላችዋል

አጠቃቀሙ አፑን ካወረዳቹ በዋላ ስልካቹ ላይ ጭናቹ የሚተይቃቹን ሁሉንም Promotion ሰታቹ ከዛ ኢሜላቹን ታስገቡለታላቹ

እንደ ድንገት እንኳን ስልካቹ ቢሰረቅ በላላ ስልክ ኢሜላቹን አስገብታቹ የሰረቀውን ሌባ እስከነ አድራሻው ማወቅ ትችላላችሁ

Download Application

══════❁✿❁══════                                                                        


Lite apps

Lite app ማለት የአንድ አፕልኬሽን lighweignt version ነው። ማለትም lite app design ሲደረግ ትንሽ storageና በትንሽ network connection ይሰራል። እንዲሁም ከnormal መተግበሪያው ጋር ሲነፃፀር ለLow end hardware configuration ላላቸው ስልኮች (ለትናንሽ ስልኮች) በትንሽ performance እንዲሰራ ተደርጎ design ይደረጋል።

አብዛኛውን ጊዜ የregular app size
40-80mb መቀነሱ የlite app ደግሞ 1-4mb ሊኖረው ይችላል።

ይህንን version አብዛኛውን ጊዜ እንደ tiktok, instagram, Facebook የመሳሰሉ social media apps lite version አላቸው።

ነገርግን አንድ lite app በnormal or regular app ላይ ያለው feature በሙሉ ላይኖረው ይችላል።

══════❁✿❁═══════                                                                           


---------------------------------

👋 everyone we are back✔️ በአዲስ እና ጠቃሚ በሆነ content ከነገ ጀምሮ actively ለእናንተ ይዘን እንቀርባለን
------------------------------- እስከዛ እናንተም
በ reaction አለን በሉን
።🥰


"Yoo miira kee too'achuu baatte warra miira isaanii too'atetu akka kubbaatti siin taphata."

@OroInspireCenter
@Gaggeessummaa

20 ta oxirgi post ko‘rsatilgan.