የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የበርካታ ገዳማት ባለቤት ነች፡፡
በፈቃደ እግዚአብሔር ከ5ተኛው መቶ ክፍለ ዘመን ጀምሮ በመላው ሀገሪቱ እየተስፋፉና እያደጉ የመጡት እነዚሁ ገዳማት የምናኔና የጸሎት እንዲሁም ድኀነተ ሥጋ ወነፍስ የሚገኝባቸው ቦታዎች ናቸው፡፡
ለቤተ ክርስቲያናችን ዘርፈ ብዙ አገልግሎት ከመስጠት ጎን ለጎን የሊቃውንት መፍለቂያና የበርካታ ቅዱሳን ምንጭ በመሆንም ሲያገለግሉ እንደኖሩ ይታወቃል፡፡
በሀገሪቱ ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ማኀበራዊ እንቅስቃሴዎች ውስጥ አዎንታዊ ተፅዕኖ ከመፍጠራቸውም በላይ የሀገሪቱ የትምህርትና የሥልጣኔ ማእከላት በመሆን አገልግለዋል ፡፡ ገዳማት የቤተክርስቲያን ስውር ጓዳዎችና የሚስጥር መዝገቦች ናቸው ፤ ገዳማት የመማፀኛ ከተማ ናቸው ፤ ገዳማውያን ለእግዚአብሄር የሚቀርቡ አስራት በኩራት ናቸው ።
ይህ በዚህ እንዳለ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ገዳማት በተለያዩ አዝማናት በሀገሪቱና በቤተ ክርስቲያኒቱ ላይ በደረሱ ውጪያዊና ውስጣዊ የጥፋት ዘመቻዎች ቀጥተኛ ተጠቂዎችም ነበሩ፡፡
ተፈጥሮአዊ በሆኑ ችግሮችም እንደየአካባቢው መልክአ ምድራዊ አቀማመጥ ተጋላጭ ሆነው ኖረዋል፡፡ አጽራረ ቤተ ክርስቲያንም በየጊዜው በተለያየ ስልት የገዳማውያኑን አኗኗር፣ ሥርዓትና ትውፊት ለመበረዝ ሲንቀሳቀሱና ገዳማቱን ሲዋጉ እንደኖሩ ግልጽ ነው፡፡
በማዕከላዊ ጎንደር ዞን ምስራቅ በለሳ ወረዳ የሚገኘው ሙትአንሳ ማር ቅዱሰ ሚካኤል አንድነት ገዳም ከዘጠና በላይ ገዳማውያን መነኮሳት ያሉበት ልዩ ስፍራ ነው፡፡ ከዓለት መሀል በመነኮሳት ፀሎት ብቻ በሚቆረጥ የማር እምነትና ድውያንን የሚፈውስ ድንቅ ጸበል ያለበት፤ ስለ ዓለምና ስለ ሀገራችን ሌት ተቀን የሚጸልዩበት ቅዱስ ስፍራ ነው፡፡
በተደጋጋሚ ባደረግነው ጥሪ መሠረትም የዘረጋችሁት እጃችሁ ድንቅ ነገር ሰርቷል፡፡ የእናት ገዳማውያን መኖሪያ ባማረና በዘመነ ሁኔታ ተሰርቶ፣ የሶላር ኃይል ተገጥሞለት ጭምር ተጠናቋል፡፡ ለዚህም ባወጣችሁት አብዝቶ ይተካ፣ በዘረጋችሁት እጅ ማለቂያ የሌለው በረከት ያሳፍሳችሁ ለማለት እንወዳለን ፤ አመስጋኝ ልብ የአንድ አማኝ ቀዳሚ መለያ ባህሪ ነውና በመልዓኩ በቅዱስ ሚካኤል ስም ከልብ እናመሰግናለን ፡፡
አሁን እየተሰሩ ካሉ ስራዎች አኳያ ገዳሙ የሚያስፈልገውን ያህል ባይሆንም " ጋን በጠጠር ይደገፋል " እንዲሉ የተቻለውን አገልግሎት ለመስጠት ጥረት ሲደረግ ቆይቷል አሁንም ይህ ልግስናችሁ ተጠናክሮ ይቀጥል፡፡ አንድ ትልቅ ምዕራፍ ብንጓዝም ለመስራት ከታሰበው ግማሽ ያህል እንኳ አልተጠናቀቀምና ገዳማውያኑ ልገሳችሁን ይሻሉ፡፡ ከላይ እንዳልነው ገዳማውያን ለእግዚአብሄር የሚቀርቡ አስራት በኩራት ናቸውና አሁንም ከጎናቸው በመቆም አለን እንበላቸው ፡፡
ድጋፍ ለማድረግ:- ሙትአንሳ ማር ቅዱሰ ሚካኤል አንድነት ገዳም
ኢትዮጲያ ንግድ ባንክ
1000442598391
ወይም
አቢሲኒያ ባንክ
141029444
የገዳሙ ስልክ ቁጥር:-0918077957 ወይም 0938644444