የመጀመሪያው ምዕራፍ 92 በመቶ የደረሰው የአርባ ምንጭ ስታዲየም በተያዘለት ጊዜ ለማጠናቀቅ ርብርብ እየተደረገ ነው።
#FastMereja I የአርባ ምንጭ ስታዲየም የመጀመሪያ ምዕራፍ የግንባታ ሂደት 92 በመቶ መድረሱን የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ አስታወቀ፡፡
ግንባታው እየተከናወነ ያለው በሕብረተሰብ ተሳትፎ፣ በመንግሥት እና በልማት አጋሮች ድጋፍ መሆኑ ተገልጿል።
የመጀመሪያው ምዕራፍ የግንባታ ሂደት ሲጠናቀቅ ሁለተኛው ምዕራፍ እንደሚቀጥል ተነግሯል።
ዲዛይኑ በአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን (ካፍ) ስታንዳርድ መሰረት የተነደፈው ስታዲየሙ፤ ከዓለም አቀፉ እግር ኳስ ማኅበር የበላይ ጠባቂ (ፊፋ) ስታንዳርድ የተወሰደ መሆኑ ተገልጿል።
ግንባታው ሲጠናቀቅ፤
📌 የወንዶች አፍሪካ ዋንጫ (እስከ ሩብ ፍፃሜ)፣
📌 የሴቶች አፍሪካ ዋንጫ (እስከ ፍፃሜ)፣
📌 የፊፋ የዓለም ዋንጫ ማጣሪያዎች፣
📌 የወንዶች አፍሪካ ዋንጫ (ቻን) እና
📌 የሴቶች ሻምፒየንስ ሊግ ፍፃሜ ጨዋታዎችን ማስተናገድ እንደሚችል አብራርተዋል፡፡
ስታዲየሙ የስፖርት ሜዳ፣ የተመልካች አካባቢ፣ የሚዲያ እና ደጋፊ አገልግሎቶች እንዲሁም የቡድን እና የባለስልጣኖች ክፍሎች እንደሚኖሩት አመላክተዋል፡፡
በቅርቡ የገቢ ማሰባሰቢያ መርሀግብር በሸራተን አዲስ ሆቴል የሚካሄድ ሲሆን በዚህም የገቢ ማሰባሰቢያ ላይ የተለያዩ ሚኒስትሮች የክልል መስተዳደሮችና ባለሀብቶችን ጨምሮ ከ350 በላይ እንግዶች እንደሚገኙ ተገልጿል።
ከዚህ በተጨማሪም ለስቴድየሙ ቋሚ ገቢ ለማሰባሰብ የቶምቦላ ሎተሪ እጣ ሽልማት የሚካሄድ ሲሆን ይህም ሎተሪ በአርባምንጭ ከተማ ሰፊ የካሬ መሬት፣ የኤሌክትሪክ ባጃጅ፣ የሞተር ሳይክል፣ የእንግሊዝ ሀገር ደርሶ መልስ ትኬትና የ5 ቀን የኳስ እይታና ምሽት እንዲሁም ሌሎች ሽልማትን የያዘ እንደሆነ የገቢ አሰባሳቢ ኮሚቴ እሺ ሚዲያ ገልጾልናል።
ስቴድየሙ ግንባታው ተጠናቆ ሲያልቅ እስከ 30ሺ ሰው የመያዝ አቅም እንዳለው ተነግሯል።
#ስፖርት