የሳጥናኤል ጎል ኢትዮጵያ PDF


Kanal geosi va tili: Efiopiya, Amharcha
Toifa: ko‘rsatilmagan


Похожие каналы

Kanal geosi va tili
Efiopiya, Amharcha
Toifa
ko‘rsatilmagan
Statistika
Postlar filtri












መጽሐፈ ነገሥት ካልዕ
6:8-23

"የሶርያም ንጉሥ ከእስራኤል ጋር ይዋጋ ነበር፤ ከባሪያዎቹም ጋር ተማክሮ። በዚህ ተደብቀን እንሰፍራለን አለ።፤ የእግዚአብሔርም ሰው። ሶርያውያን በዚያ ተደብቀዋልና በዚያ ስፍራ እንዳታልፍ ተጠንቀቅ ብሎ ወደ እስራኤል ንጉሥ ላከ።
፤ የእስራኤልም ንጉሥ የእግዚአብሔር ሰው ወደ ነገረው ስፍራ ሰደደ፤ አንድ ጊዜም ሳይሆን፥ ሁለት ጊዜም ሳይሆን በዚያ ራሱን አዳነ።
 ፤ የሶርያም ንጉሥ ልብ ስለዚህ እጅግ ታወከ፤ ባሪያዎቹንም ጠርቶ። ከእኛ ዘንድ ከእስራኤል ንጉሥ ጋር የተወዳጀ እንዳለ አትነግሩኝምን? አላቸው።
 ፤ ከባሪያዎቹም አንዱ። ጌታዬ ሆይ፥ እንዲህ እኮ አይደለም፤ ነገር ግን በእልፍኝህ ውስጥ ሆነህ የምትናገረውን በእስራኤል ዘንድ ያለ ነቢይ ኤልሳዕ ለእስራኤል ንጉሥ ይነግረዋል አለ።
 ፤ እርሱም። ልኬ አስይዘው ዘንድ ሄዳችሁ ወዴት እንደ ሆነ እዩ አለ። እነርሱም። እነሆ፥ በዶታይን አለ ብለው ነገሩት።
፤ ወደዚያም ፈረሶችንና ሰረገሎችን እጅግም ጭፍራ ሰደደ፤ በሌሊትም መጥተው ከተማይቱን ከበቡ።
፤ የእግዚአብሔር ሰው ሎሌ ማለዳ ተነሥቶ በወጣ ጊዜ፥ እነሆ፥ በከተማይቱ ዙሪያ ጭፍራና ፈረሶች ሰረገሎችም ነበሩ። ሎሌውም። ጌታዬ ሆይ፥ ወዮ! ምን እናደርጋለን? አለው።
 ፤ እርሱም። ከእኛ ጋር ያሉት ከእነርሱ ጋር ካሉት ይበልጣሉና አትፍራ አለው።
 ፤ ኤልሳዕም። አቤቱ፥ ያይ ዘንድ ዓይኖቹን፥ እባክህ፥ ግለጥ ብሎ ጸለየ። እግዚአብሔርም የብላቴናውን ዓይኖች ገለጠ፥ አየም፤ እነሆም፥ በኤልሳዕ ዙሪያ ያሉት የእሳት ፈረሶችና ሰረገሎች ተራራውን ሞልተውት ነበር።
፤ ወደ እርሱም በወረዱ ጊዜ ኤልሳዕ። ይህን ሕዝብ ዕውር ታደርገው ዘንድ እለምንሃለሁ ብሎ ወደ እግዚአብሔር ጸለየ። ኤልሳዕም እንደ ተናገረው ቃል ዕውር አደረጋቸው።
፤ ኤልሳዕም። መንገዱ በዚህ አይደለም፥ ከተማይቱም ይህች አይደለችም፤ የምትሹትን ሰው አሳያችሁ ዘንድ ተከተሉኝ አላቸው፤ ወደ ሰማርያም መራቸው።
፤ ወደ ሰማርያም በገቡ ጊዜ ኤልሳዕ። አቤቱ፥ ያዩ ዘንድ የእነዚህን ሰዎች ዓይኖች ግለጥ አለ፤ እግዚአብሔርም ዓይኖቻቸውን ገለጠ፥ እነርሱም አዩ። እነሆም፥ በሰማርያ መካከል ነበሩ።
 ፤ የእስራኤልም ንጉሥ ባያቸው ጊዜ አልሳዕን። አባቴ ሆይ፥ ልግደላቸውን? ልግደላቸውን? አለው።
፤ እርሱም። አትግደላቸው፤ በሰይፍህና በቀስትህ የማረክኸውን ትገድል ዘንድ ይገባሃልን? እንጀራና ውኃ በፊታቸው አኑርላቸው፥ በልተውና ጠጥተውም ወደ ጌታቸው ይሂዱ አለው።
 ፤ ብዙም መብል አዘጋጀላቸው፤ በበሉና በጠጡ ጊዜም አሰናበታቸው፥ እነርሱም ወደ ጌታቸው ሄዱ። ከዚያም በኋላ የሶርያ አደጋ ጣዮች ወደ እስራኤል አገር አልመጡም።"


ወደ ኤፌሶን ሰዎች 6:9-18

"የዲያብሎስን ሽንገላ ትቃወሙ ዘንድ እንዲቻላችሁ የእግዚአብሔርን ዕቃ ጦር ሁሉ ልበሱ።
መጋደላችን ከደምና ከሥጋ ጋር አይደለምና፥ ከአለቆችና ከሥልጣናት ጋር ከዚህም ከጨለማ ዓለም ገዦች ጋር በሰማያዊም ስፍራ ካለ ከክፋት መንፈሳውያን ሠራዊት ጋር ነው እንጂ።
ስለዚህ በክፉው ቀን ለመቃወም፥ ሁሉንም ፈጽማችሁ ለመቆም እንድትችሉ የእግዚአብሔርን ዕቃ ጦር ሁሉ አንሡ።
እንግዲህ ወገባችሁን በእውነት ታጥቃችሁ፥ የጽድቅንም ጥሩር ለብሳችሁ፥ በሰላም ወንጌልም በመዘጋጀት እግሮቻችሁ ተጫምተው ቁሙ፤
በሁሉም ላይ ጨምራችሁ የሚንበለበሉትን የክፉውን ፍላጻዎች ሁሉ ልታጠፉ የምትችሉበትን የእምነትን ጋሻ አንሡ፤
የመዳንንም ራስ ቁር የመንፈስንም ሰይፍ ያዙ እርሱም የእግዚአብሔር ቃል ነው።
በጸሎትና በልመናም ሁሉ ዘወትር በመንፈስ ጸልዩ፤ በዚህም አሳብ ስለ ቅዱሳን ሁሉ እየለመናችሁ በመጽናት ሁሉ ትጉ፤"


ትናንት አባቶቹ እናቶቹ ያቆዩት ባህል ቅርስ ሲወድም ሲረክስ እያየህ እንዳላየህ እየተመለከትህ አሁን በምን ወኔህ ነው ማይክ ይዘህ የምታቅራራው የምትፎክረው???? አስመሳይ ምስለኔ መንጋ አድርባይ ሁላ !!!!! እመነኝ አድዋ አንተን አያውቅህም አንተም አድዋን አታውቀውም።


‹‹በነጭ ፈረስ ላይ ተቀምጦ በግልጽ ሲዋጋን የነበረው ቅዱስ ጊዮርጊስ ነበር››

‹‹አግበራ በምትባል አውራጃ በቅዱስ ጊዮርጊስ ስም የታጸች አንዲት ቤተ ክርስቲያን ነበረች፡፡ በድላይ የተባለ አንድ አረማዊ ገዥ ወደ እርሷ በደረሰ ጊዜ ወደ ቤተ ክርስቲያኒቱ ውስጥ በአመጽ ገብቶ ከሚስቱ ጋር ከሴሰነ በኋላ በእሳት አቃጠላት፡፡ ዳግማዊ ቆስጠንጢኖስ የተባለ ንጉሣችን ዘርዐ ያዕቆብም ይህን በሰማ ጊዜ በሰማዕቱ፣ በእመቤታችንና በተወዳጅ ልጇ ኃይል ይህን አረመኔ በድላይን ለመውጋት ተዘጋጀ፡፡

ከሃዲው በድላይም በበኩሉ ዐፄ ዘርዐ ያዕቆብን ለመውጋት ተነሣ፡፡ ውጊያውንም ለመጀመር በተነሡ ጊዜ በነጭ ፈረስ ላይ የተቀመጠ ፈረሰኛ ሰው በበድላይ የጦር ሠራዊት ውስጥ ታየ፡፡ ከኋላ ሆኖ ይነዳቸዋል፣ በሌላ ጊዜም ከፊት ሆኖ ይመራቸው ነበር፡፡ ከንጉሥ ዘርዐ ያዕቆብ አጠገብ ባደረሳቸው ጊዜ ግን ያ ነጭ ፈረሰኛ ከበድላ ሠራዊት ተለይቶ የበድላይን ጦር ለመውጋት ከንጉሣችን ዘርዐ ያዕቆብ ሠራዊት ጋራ ተቀላቀለ፡፡ በክርስቲያኖቹና በአረማውያኑ መካከል ጦርነቱ በበረታ ጊዜ አረማውያኑ ተሸነፉ፡፡ አለቃቸው በድላይም በጦርነቱ መካከል በጦር ተወግቶ ወድቆ ሞተ፡፡

በድላይም ክፉ አሟሟት ሲሞት ባዩት ጊዜ ከሠራዊቱም መካከል ብዙዎቹ ‹‹በድላይ ከልቡ ትዕቢት የተነሣ ክፉ አሟሟት ሞተ፣ እግዚአብሔር ለእሥራኤል ይዋጋለቸው ነበርና በንጉሥ ሕዝቅያስ ዘመን ሰናክሬም እንደተዋረደ፣ በዮዲትም ዘመን ሆሎፎርኒስ እንደተዋረደ በድላይም ዛሬ ክፉኛ ተዋረደ›› ተባባሉ፡፡ ንጉሥ ዘርዐ ያዕቆብም በእመቤታችንና በሰማዕቱ በቅዱስ ጊዮርጊስ ተራዳኢነት የአረማውያንን ሬሣ ምድርን እስኪሸፍናት ድረስ በጦርነቱ አሸናፊ ሆነ፡፡ የሞቱትና ተማረኩትም ብዛታቸው በቁጥር አይታወቅም ነበር፡፡ ዘመናዊ የሆኑት የጦር መሣሪያዎቻቸውም እጅግ ብዙ ነበሩ፡፡ ራሱ ንጉሡ በድርሳኑ እንደገለጸው ‹‹ወደ ቤተ መግሥቴ የገባው የራሳቸው የሰዎቹና የፈረሶቻቸው ጌጥ በያይነቱ ሊናገሩት የማይቻል እጅግ አስደናቂ ነበር›› አለ፡፡ ሰማዕቱ ቅዱስ ጊዮርጊስም አረማውያንን ስለመውጋቱ አረማውያኑ ራሳቸው ሲመሰክሩ ‹‹በነጭ ፈረስ ላይ ተቀምጦ በግልጽ ሲዋጋን የነበረው ቅዱስ ጊዮርጊስ ነበር›› አሉ፡፡ ክርስቲያኖቹም ‹‹ሰማዕቱ እረዳን›› በማለት ተደሰቱ፡፡

በዚያም የጦርነቱ ቀን ሌሊቱን ቅዱስ ጊዮርጊስ በስሙ በታነጸች ወደ አንዲት ሌላ ቤተ ክርስቲያን ሄደና የጦር መሣሪያ በታጠቀ አርበኛ ወይም ወታደር ተመስሎ ለአንድ ቄስ ተገለጠለት፡፡ ጦሩን በእጁ ይዟል፣ ፈረሱም በጣም አልቦት ነበር፡፡ የጦር መሣሪያ በታጠቀ አርበኛ አምሳል ለቄሱ የተገለጠለትም ‹‹ዛሬ ከበድላይ ጋር ጦርነት ውዬ መጣሁ›› አለው፡፡ ስለዚህም እኛ የክርስቶስ ወገኖች የቅዱስ ጊዮርጊስን የተአምራቱን ማረጋገጫ ምስክር ከራሱ አገኘን፡፡ የቅዱስ ጊዮርጊስ ጸሎቱ በረከቱ የረድኤቱም ሀብት የተዋሕዶ ልጆች የሆንን ሁላችን ይጠብቀን፡፡››
የዓሥራት ሀገሩን ቅድስት ኢትዮጵያን ከዘመኑ ጠላቷቿና ከሰፈሩባት የሰይጣን ልጆች ይጠብቅልን!!!
✞  ✞  ✞

(ምንጭ፡- የተስፋ ገብረሥላሴ እትም ገድለ ቅዱስ ጊዮርጊስ-ተስፋ ገብረ ሥላሴ፣ 1991 ዓ.ም)


የሳጥናኤል ጎል ኢትዮጵያ PDF dan repost
Video oldindan ko‘rish uchun mavjud emas
Telegram'da ko‘rish
"ቅዱስ ጊዮርጊስ ነው የተዋጋልን" መምህር ተስፋዬ መቆያ


የሀገራችን ጥቁር ጥልያኖች ከነዚያ ጣልያኖች የከፉ ሁነውብን እያለ ከነጮች ከአረቦች ትዕዛዝ እየተቀበሉ እርስበርስ እያበላሉን ምን ያስደነፋሃል???? ### እስቲ እውነት የአድዋ አባቶች ልጅ ከሆንህ እስቲ ከተገፋው ከተበደለው ጦርነት ከታወጀበት ህዝብ ጎን ቁመህ እንይህ.... አለበለዚያ ግን ማይክ ይዘህ በከንቱ አትደንፋብን ....### ይልቁንስ የውስጥህን ጥቁር ጥልያኖች በዳዊት መንገድ ተጉዘህ አውርዳቸው።


ለምን ነባር ሀይማኖቶች ተዘመተባቸው ትክክለኛ ለእውነት ለሀቅ ለኢትዮጵያዊነቱ የሚለው ፋኖስ ለምን ተዘመተበት
false flag ቁማር ተሰርቶ ለምን ተዘመተበት?
መልስ= /ነጭ የከተበው ካልሆነ ስለማይገባችሁ ብዬ ነው/
http://www.sweetliberty.org/issues/hoax/bluebeam.htm


ለውጥ ማምጣት ከፈለግህ ለውጡ የሰውን አምዕሮ አስተሳሰብ ከመገንባት ይጀምራል የመጀመሪያ ምዕራፍ ይህ ነው። መጀመሪያ ትውልዱን አምዕሮውን አስተሳሰቡን አንቀው የያዙትን ጫት ቤት ሲጋሬ ሱስ ቤቶችን እየተከታተልህ አስወግዳቸው /እናስወግዳቸው/ ጭፈራ ቤቶች መወገድ አለባቸው!!!!!!! ዝሙት ቤቶች መወገድ አለባቸው!!!! ቤቲንግ ቤት ቁማር ቤቶች መወገድ አለባቸው!!!! በቅዱሳን ስም የሚሸጡ አስካሪ መጠጦች ከገበያው መወገድ አለባቸው ለምሳሌ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቢራ ቅዱስ ዮሐንስ ቢራ ሐበሻ (የመላዕክት ፎቶ አለበት)ቢራ...። .... !!!! ከዘረኝነት ከጎጠኝነት መንፈስ መውጣት አለብን! ነጭን ከማምለክ መውጣት አለብን!!!.....!! እግዚአብሔርን የሚያስቀይም ስራ እየሰራን ለገንዘብ ለጥቅማችን ስንል ትውልድ እየገደልን ሰላም ይመጣል ብለን ማሰብ ጅልነት ነው። !


️ ንስር አማራ🦅 dan repost
Video oldindan ko‘rish uchun mavjud emas
Telegram'da ko‘rish
🔥#ወሎ_አማራ💪

ዋርካው ምሬ ወዳጆ ውሳኔውን አሳውቋል!!በቀጠናው ያለውን እውነታ ተናግሯል!!ወንድሞቻችን ጋር
#አንታኮስም ብሏል‼️

#ወጥር_አማራ‼️
#ድል_ለአማራ_ፋኖ💪
#ድል_ለአማራ_ህዝብ💪

05/12/16 ዓ.ም

@NISIREamhra


Fearless one videos + information dan repost
Video oldindan ko‘rish uchun mavjud emas
Telegram'da ko‘rish
*Message: This is How the Cookie Crumbles...*


አዳምጥ!!!!!


Fearless one videos + information dan repost
Video oldindan ko‘rish uchun mavjud emas
Telegram'da ko‘rish
*Freedom*

17 ta oxirgi post ko‘rsatilgan.